ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሚያዝያና ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ነጠላ ቅጂዎች። ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ለማበርከት እንድትችሉ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር ይኑራችሁ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመርም ጥረት አድርጉ። ሰኔ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሐምሌና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር !፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
◼ “የአምላክ ቃል አድራጊዎች” የተባለው የአውራጃ ስብሰባ ጊዜያዊ ፕሮግራም:-
መስ. 29-ጥቅ. 1ድሬዳዋ
ጥቅምት 6-8ሻሸመኔ
ጥቅምት 13-15አዲስ አበባ
ጥቅምት 20-22አዲስ አበባ
ጥቅምት 27-29ደሴ
ኅዳር 3-5ጅማ
◼ ለ2000 የአውራጃ ስብሰባ ደረት ላይ የሚለጠፉት ካርዶች ከጽሑፎች ጋር ከነሐሴ ወር ጀምሮ ስለሚላኩላችሁ ማዘዝ አያስፈልግም። ጉባኤዎች ተጨማሪ ካርድ ካስፈለጋቸው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) ማዘዝ ይኖርባቸዋል። ጉባኤ ውስጥ ደረት ላይ የሚለጠፈውን ካርድ መያዣ ኘላስቲክ ማግኘት የሚፈልጉ ካሉ ማዘዝ ያስፈልጋችኋል።
◼ በብሪታንያ ታትመው በአየር ለሚላኩ የእንግሊዝኛ ወይም የፈረንሳይኛ የመጽሔት ኮንትራቶች በዓመት ለፖስታ አገልግሎት የምናደርገው መዋጮ ብር 77.50 ይሆናል። ይህ የጽሑፎቹን ዋጋ አይጨምርም። በካናዳ ታትመው በአየር ለሚላኩ የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሳይኛ ወይም የጣሊያንኛ የመጽሔት ኮንትራቶች በዓመት ለፖስታ አገልግሎት የምናደርገው መዋጮ ደግሞ ብር 133.00 ይሆናል።
◼ በሲዲ ሮም የተዘጋጀው የመጠበቂያ ግንብ ቤተ መጻሕፍት ለሕዝብ የሚሠራጭ፣ በትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍት የሚቀመጥ ወይም እንዲሁ ለይሖዋ ምሥክሮች አድናቆት እንዳለው ለገለጸ ሰው ሁሉ የሚታደል እንዳልሆነ አስታውሱ። የመጠበቂያ ግንብ ቤተ መጻሕፍት የተዘጋጀው ለጉባኤው አባላት ሲሆን ማግኘት የሚቻለውም በጉባኤው በኩል ብቻ ነው። ኮምፓክት ዲስኮች እስኪመጡና ከጽሑፎች ጋር እስኪላኩላችሁ ድረስ “ሲደርስ የሚላኩ” ተብለው በጉባኤው የእሽግ መግለጫ ላይ ይሰፍራሉ።
◼ በቅርቡ የደረሱን:-
እንግሊዝኛ:- የ2000 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ፣ የመጠበቂያ ግንብ ጥራዝ 1999፤ የቴፕ ክር:- የምትወዱት ሰው ሲሞት፤ አረብኛ:- የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች)
◼ በድጋሚ የደረሱን:-
እንግሊዝኛ:- እውቀት፤ ፈረንሳይኛ:- እውቀት፣ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም፣ ትራክት ቁ. 24