የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም
ሚያዝያ 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 51 (127)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። “የሰው ዘር ቤዛ ያስፈለገው ለምንድን ነው?” በሚል ርዕስ ሚያዝያ 16 የሚቀርበውን ልዩ ንግግር አስታውሱ። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2000 በተባለው ቡክሌት ላይ ከሚያዝያ 14-19 ላሉት ቀናት የተመደበውን የመታሰቢያ በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ሁሉም ተከታትለው እንዲያነቡ አበረታታ። በአባሪው በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ከልስ።
15 ደቂቃ:- “ክርስቶስ ላሳየው ፍቅር ምላሽ እየሰጣችሁ ነውን?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሀሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። ከግንቦት 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16-17 አንቀጽ 12-13 ላይ ተጨማሪ ሐሳብ አቅርብ። ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ ሁሉም ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
20 ደቂቃ:- “ሚያዝያ—መልካም ለማድረግ ቅንዓታችንን የምናሳይበት ወር!” ጥያቄና መልስ። በሚያዝያ ለማከናወን የምንፈልገውን ነገር የሚያብራራና ሞቅ ባለ ስሜት በውይይት የሚቀርብ ክፍል። የመጨረሻዎቹን ሦስት ወይም አራት ደቂቃዎች ተጠቅመህ “የሚበዙትን የሚያነሳሳ ቅንዓት” የሚለውን ከልስ።
መዝሙር 49 (114) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 24 (50)
13 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። የሚያዝያ ወር ሊጠናቀቅ የቀረው ሁለት ሳምንት ብቻ ስለሆነ ሁሉም ወሩ ከማለቁ በፊት በአገልግሎት እንዲካፈሉ አበረታታ። በቅርቡ የወጡትን መጽሔቶች ተጠቅመህ አጭር ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
16 ደቂቃ:- “የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ አላችሁን?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። መቅደም ለሚገባቸው ነገሮች ቅድሚያ መስጠት ይኖርብናል። በመንፈሳዊ ጥቅም የሚያስገኝልንን ነገር ማድረጋችንን ለመቀጠል የግል ተነሳሽነትና ራስን መግዛት ያስፈልጋል። ከኢየሱስ ምሳሌ ምን ልንማር እንደምንችል አብራራ።—ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) ጥራዝ 2 ገጽ 68 አንቀጽ 3-5ን ተመልከት።
16 ደቂቃ:- መጽሔቶችን ጥሩ ውጤት ሊያስገኙ በሚችሉበት ቦታ አበርክቱ። አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበት ንግግር። መጀመሪያ የቆዩ ጽሑፎችን እንዲያበረክቱ አበረታታ። ከዚያም በጥር 8, 1995 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 22-24 ያለውን ሐሳብ ከልስ። በመጽሔቶቻችን ላይ ለወጡ በአንድ የተለየ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ላተኮሩ ሐሳቦች ምላሽ ሊሰጡ የሚችሉ ሰዎችን መፈለግ ጥሩ የሆነው ለምን እንደሆነ ግለጽ። ከአሁን በፊት ከወጡ ጽሑፎች አንዳንድ ምሳሌዎችን ከጠቀስክ በኋላ እነዚህ ጽሑፎች በጉባኤው ክልል ውስጥ የሚገኙትን የትኞቹን ሰዎች፣ የንግድ ተቋማት እንዲሁም ድርጅቶች ሊማርኩ እንደሚችሉ ግለጽ። አድማጮች ይህንን ዘዴ በመጠቀም እንዴት ጥሩ ውጤት እንዳገኙ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 85 (191) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 36 (81)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጉባኤውን የመታሰቢያ በዓል ተሰብሳቢዎች ቁጥር ተናገር። ለመጀመሪያ ጊዜ በበዓሉ ላይ የተገኙት ሰዎች የሰጡትን አስተያየት አድማጮች እንዲናገሩ ጋብዝ።
17 ደቂቃ:- አዲሶች በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ እርዷቸው። እውቀት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 161-3 አንቀጽ 5-8 ላይ የተመሠረተ ንግግር። አዲሶች ለተወሰነ ጊዜ ካጠኑ በኋላ ወደ ስብሰባዎች መምጣት መጀመራቸው የግድ አስፈላጊ ነው። በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ማድረግ ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ሆኖም በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ለማነሳሳት ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ? ጥናት የሚመሩ ሁሉ በእውቀት መጽሐፍ ላይ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገረውን ሐሳብ ጊዜ ወስደው ከጥናቶቻቸው ጋር መከለስ አለባቸው። ከዚያም በእውነተኛው አምልኮ ከእኛ ጋር እንዲካፈሉ ለመርዳት ቁርጥ ያለ ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል።
18 ደቂቃ:- “አዘውታሪ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ናችሁን?” አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበት በጸሐፊው የሚቀርብ ንግግር። የአገልግሎት ሪፖርታችንን መመለስ ያለብን ለምን እንደሆነ አብራራ። (አገልግሎታችን የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 106-8ን ተመልከት።) ሪፖርታችንን በጊዜው ሳንመልስ ስንቀር የሚፈጠሩትን አንዳንድ ችግሮች ግለጽ። አድማጮች ሪፖርታቸውን በጊዜው ከመመለስ እንዳይዘናጉ ሲሉ ምን እንደሚያደርጉ እንዲናገሩ ጋብዝ። በዚህ በኩል የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት መሪዎች ምን እርዳታ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ ጠቁም። የሚያዝያ ወር ሊያልቅ የቀረው አንድ ሳምንት ብቻ ስለሆነ ሁሉም በአገልግሎት መካፈላቸውና በወሩ መጨረሻ ላይ ሪፖርታቸውን መመለሳቸው ያለውን አስፈላጊነት ጎላ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 95 (213)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የሚያዝያ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። ሁሉም የአገልግሎት ሪፖርቶች ተሰብስበው እስከ ግንቦት 6 ድረስ እንዲላኩ የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች በቡድናቸው ውስጥ ያለው እያንዳንዱ አስፋፊ ሪፖርት ማድረጉን ማረጋገጥ አለባቸው። የጥያቄ ሣጥኑን ለአካባቢያችሁ ተግባራዊ ሊሆን በሚችል መንገድ ከልስ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
18 ደቂቃ:- “ተመልሳችሁ መሄድ እንዳለባችሁ አትዘንጉ!” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ተመላልሶ መጠየቅ ሳናደርግ የምንቀርባቸውን አንዳንድ ምክንያቶች ግለጽ። ትክክለኛ ማስታወሻ መያዛችንና ተመልሰን ለመሄድ ፈቃደኛ መሆናችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ አብራራ። በየሳምንቱ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ የተወሰነ ጊዜ መመደብ እንደሚያስፈልግ ሐሳብ ስጥ። በአገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 88-89 ላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ ከልስ። በ1995 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 45 ላይ የቀረበውን ተሞክሮ ጨምረህ ተናገር።—1 ቆሮ. 3:6, 7
መዝሙር 41 (89) እና የመደምደሚያ ጸሎት።