ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሰኔ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በማስጀመር ላይ ትኩረት አድርጉ። ሐምሌና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ።
◼ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮ መደወል ስትፈልጉ የስልክ ቁጥሩ 612929 ነው። ይህንን ቁጥር ተጠቅማችሁ ስልኩ አልመልስ ካለ ግን 09213489 መሞከር ትችላላችሁ። ይሁን እንጂ በዚህ አዲስ ቁጥር መደወል የምትችሉት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2:00 እስከ 11:00 እና ቅዳሜ ከ2:00 እስከ 6:00 ባለው የሥራ ሰዓት ብቻ ነው። እባካችሁ በሌላ ጊዜ በዚህ ቁጥር አትጠቀሙ።
◼ በድጋሚ የደረሱን:- አማርኛ፦ መዝሙር መጽሐፍ።