የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/00 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሰኔ 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 26 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 6/00 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም

ሰኔ 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 57 (136)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።

15 ደቂቃ:- ‘ድካማችሁ ከንቱ አይደለም።’ አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ክፍሉን በጥያቄና መልስ አቅርበው። በሰኔ 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 ላይ ከሚገኘው ተሞክሮ አንዳንድ ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ።

22 ደቂቃ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በተባለው ብሮሹር ጥናት ማስጀመር። በጥር 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ የወጣውን ርዕሰ ትምህርት በመከለስ የሚቀርብ ንግግር። አንቀጽ 6 ላይ የቀረበውን ሐሳብ ተመርኩዘህ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ጥናት በማስጀመር እንዲሁም ጥናቱ ከሳምንት ሳምንት ሳይቋረጥ እንዲቀጥል በማድረግ ረገድ ውጤታማ ሊሆኑ የቻሉበትን ምክንያት በአጭሩ እንዲናገሩ አድርግ።

መዝሙር 92 (209) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 8 (21)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና የሩብ ዓመቱ የሒሳብ ምርመራ ማስታወቂያ። ትምህርት ቤት ዝግ በሚሆንበት ጊዜ በአሥራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ወጣቶች በቤታቸው ልናገኛቸው የምንችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው። ስለዚህ ጉባኤው ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ወይም ወጣትነትህ የሚሉት መጽሐፎች ካሉት እነዚህን ጽሑፎች በአገልግሎታችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ልንጠቀምባቸው የምንችለው እንዴት እንደሆነ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

8 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

25 ደቂቃ:- “የሚመራኝ ሳይኖር . . . እንዴት ይቻለኛል?” በጥያቄና መልስ በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። እያንዳንዱን አንቀጽ ጎላ ብሎ በሚሰማ ድምጽ እንዲያነቡልህ አድርግ። እንዲሁም በአንቀጽ 3, 4, እና 7 ላይ የሚገኙትን ጥቅሶች አንብባቸው። አንቀጽ 6ን ስትሸፍን የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከአንድ ከተጠመቀ ሰው ጋር እንደገና የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መጀመር ያስፈልግ ወይም አያስፈልግ እንደሆነ በመወሰን በኩል የሚኖረውን ድርሻ አብራራ። በኅዳር 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን የወጣውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።

መዝሙር 41 (89) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 5 (10)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሰኔ የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በሐምሌ የሚበረከተውን ጽሑፍ ከልስ። በጉባኤው ውስጥ የሚገኙትን የቆዩ ብሮሹሮች አሳይና የእያንዳንዱን ብሮሹር ዓላማ በአጭሩ ጥቀስ። ከእነዚህ ብሮሹሮች መካከል አንዱን በአገልግሎታችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

17 ደቂቃ:- ‘ልትረዱና ልታካፍሉ የተዘጋጃችሁ ሁኑ።’ ጥያቄና መልስ። በኅዳር 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29-30 ላይ “የምንሰጥበት ምክንያት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር የተዘረዘሩትን አራት ምክንያቶች ጨምረህ አቅርብ።

18 ደቂቃ:- እንዴት እንደምትመልሱ እወቁ። (ቆላ. 4:​6) በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ቅዱስ ጽሑፋዊ ያልሆነ ክርክር የሚያነሳ ሰው ሲያጋጥማችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ብዙውን ጊዜ ማመራመር የተባለው መጽሐፍ በዘዴ መልስ ለመስጠት የሚያስችሉንን ተግባራዊ ሐሳቦች በማቅረብ ያግዘናል። ለምሳሌ ያህል፣ እኛ ሞትን በክርስቶስ ቤዛ አማካኝነት ድል እንደሚሆን ጠላት አድርገን ብንቆጥረውም ሌሎች በሪኢንካርኔሽን የሐሰት ትምህርት ሳይቀር በማመን ሞትን ምንም ነገር ሊያስወግደው እንደማይችል እርግጠኞች ሆነው ይናገራሉ። ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 103-4 እና 320 ላይ “አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-” በሚለው ርዕስ ሥር የተሰጡትን ምላሾች ተወያዩባቸው። ሁሉም ወደ መስክ አገልግሎት ሲሄዱ መጽሐፉን እንዲይዙ አበረታታ።

መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 95 (213)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎችና በመስክ አገልግሎት ያጋጠሙ ተሞክሮዎች። “ምሥራቹን ሁሉንም ዓይነት ቋንቋ ለሚናገሩ ሰዎች አካፍሉ” የሚለውንም አቅርብ።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በተግባር ላይ ማዋል የቤተሰብን ሕይወት ያጠናክራል። በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 253 በሚገኙት ስምንት ነጥቦች ላይ ተመስርቶ በሁለት ወንድሞች መካከል በውይይት የሚቀርብ። ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እንዲገነዘቡ መርዳት ያለውን አስፈላጊነት አብራራ። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ከተባለው ብሮሹር ትምህርት 8ን በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶችን መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ለመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ምላሽ የሚሰጥ ቤተሰብ እርስ በርሱ የሚቀራረብ ሲሆን የጠበቀ ፍቅርና አንድነት ስለሚኖረው ደስታው የላቀ ይሆናል። ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ከተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 13 አንቀጽ 1, 21-22 ላይ ያለውን ተሞክሮ ተናገር።

መዝሙር 35 (79) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ