የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/00 ገጽ 1
  • ጽናት እያሳያችሁ ነውን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጽናት እያሳያችሁ ነውን?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “በጽናት የተቋቋመውን እሱን በጥሞና አስቡ”
    “ተከታዬ ሁን”
  • ጽናት ለክርስቲያኖች እጅግ አስፈላጊ ነው
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • “ጽናት ሥራውን ሙሉ በሙሉ ይፈጽም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ምንጊዜም ከይሖዋ ድርጅት ጋር ተቀራርባችሁ ኑሩ
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 8/00 ገጽ 1

ጽናት እያሳያችሁ ነውን?

1 ‘ልጆቼ በእውነት ሲሄዱ ከማየት የበለጠ ደስታ የሚሰጠኝ ነገር የለም።’ (3 ዮሐ. 4) መንፈሳዊ ልጆቹ ያሳዩት ጽናት ለዮሐንስ ታላቅ ደስታ አምጥቶለት ነበር። ወደፊት ልጆቹ የመሆን አጋጣሚ ያላቸው በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ‘በእውነት ሲሄዱ’ መመልከት የሰማዩ አባታችንን ምንኛ ያስደስተው ይሆን!​—⁠ምሳሌ 23:​15, 16፤ 27:​11

2 የአምላክ ሕዝቦች በጥቅሉ ሲታይ በክርስቲያናዊው አገልግሎት በቅንዓት መካፈላቸውን ቢቀጥሉም አንዳንዶች ግን ቀስ በቀስ በአገልግሎቱ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ቀንሰዋል። እነዚህ ሰዎች እውነትን በሰሙበት ወቅት ለአገልግሎቱ ከፍተኛ ቅንዓት የነበራቸው ሊሆኑ ቢችሉም ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ ይህ ቅንዓታቸው በመቀዝቀዙ ደቀ መዛሙርት በማፍራቱ ሥራ የሚያደርጉት ተሳትፎ በጣም አነስተኛ ወይም አልፎ አልፎ ብቻ የሚደረግ ሆኗል።

3 አንዳንዶች በአገልግሎት የሚያደርጉትን ተሳትፎ የቀነሱት ባለባቸው የአቅም ማነስ ወይም የዕድሜ መግፋት በሚያሳድርባቸው ተጽእኖ ምክንያት እንደሆነ ግልጽ ነው። ይሁን እንጂ እንዲህ ያሉት ሰዎች ላሳዩት ጽናት ምስጋና ይገባቸዋል። አሁንም ቢሆን የአቅማቸውን ያህል እየሠሩ ነው። ሆኖም ሕይወቱን ለአምላክ የወሰነ እያንዳንዱ ግለሰብ ራሱን እንዲህ እያለ መጠየቅ ይኖርበታል:- ‘በሕይወቴ ውስጥ ለመንግሥቱ ፍላጎቶች የምሰጠው ቦታ እየጠበበ እስኪመጣ ድረስ የግል ፍላጎቶቼን በመከታተል ብዙ ጊዜ አጠፋለሁን?’ ‘ለብ ያልኩ’ ሆኛለሁ ወይስ አሁንም ‘እየተጋደልኩ’ ነው?’ (ራእይ 3:​15, 16፤ ሉቃስ 13:​24) ይሖዋ ‘በጎ ሥራ የሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም እንደሚሆንላቸው’ የገባውን ቃል በማስታወስ ሁላችንም በመሥራት ላይ ያለነውን ነገር በጸሎት እናሰላስልበት። ከዚያም አስፈላጊውን ማስተካከያ እናድርግ።​—⁠ሮሜ 2:​10

4 መጽናት የሚቻልበት መንገድ:- ኢየሱስ እንዲጸና የረዳው ምን ነበር? ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጿል:- “እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” (ዕብ. 12:​1-3) ኢየሱስ ከገጠመው ጊዜያዊ ፈተና ይልቅ በፊቱ ይጠብቀው የነበረው ደስታ ይበልጥ ነበር። እኛም በፊታችን ያለውን ደስታ ማስታወሳችን ልክ እንደ ኢየሱስ ለመጽናት ይረዳናል። (ራእይ 21:​4, 7፤ 22:​12) በግል ጥናት፣ በስብሰባዎች ላይ አዘውትሮ በመገኘትና ዘወትር በመጸለይ ይሖዋ የሚሰጠውን ብርታት ለማግኘት የምንጥር ከሆነ የሰጠንን ሥራ በማከናወን መጽናት እንችላለን።

5 ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹ በሚያሳዩት ጽናት ይደሰታል። እንግዲያው ሳናቋርጥ ‘በእውነት መንገድ በመሄድ’ ደስታው እንዲጨምር እናድርግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ