ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መስከረም:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥቅምት:- የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች። ተመላልሶ መጠየቅ የምታደርጉላቸው ሰዎች ፍላጎት ካሳዩ ኮንትራት ማስገባት ይቻላል። ከወሩ መገባደጃ ጀምሮ የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ማሰራጨት ይጀመራል። ኅዳር:- የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ስርጭት ይቀጥላል። ጉባኤዎች በክልላቸው ውስጥ ለሚገኝ ለእያንዳንዱ የቤት ባለቤት የመንግሥት ዜና ቁጥር 36ን አበርክተው ከጨረሱ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ወይም እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ለዘላለም መኖር ወይም ፍጥረት የተባሉትን መጻሕፍት ማበርከት ይቻላል። ታኅሣሥ:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍና እስከዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ሰው።
◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-23 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን።
◼ ማኅበሩ አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ማኅበሩ ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ነገሮች ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማስታወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙት የትኞቹ ጽሑፎች እንደሆኑ እባካችሁ አስታውሱ።