የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
ማሳሰቢያ:- የመንግሥት አገልግሎታችን የአውራጃ ስብሰባ በሚደረግባቸው ወራት የሚኖረንን የእያንዳንዱን ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ይዞ ይወጣል። ጉባኤዎች “የአምላክ ቃል አድራጊዎች” በተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ማድረግ ይችላሉ። አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ከአውራጃ ስብሰባው በፊት ባለው ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ስታደርጉ 15 ደቂቃ ተጠቅማችሁ የአውራጃ ስብሰባውን አስመልክቶ ከወጣው ነሐሴ 2000 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ “የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች” ከሚለው ጠቃሚ ምክሮችን ከልሱ። በየዕለቱ ጠዋትና ከሰዓት በኋላ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ሁሉም ፕሮግራሙን አንድ በአንድ እንዲመለከቱና ምን ሊቀርብ እንዳለ በማሰብ በጉጉት እንዲጠባበቁ አበረታታ። እንዲህ ማድረጉ ፕሮግራሙን በቀላሉ በትኩረት መከታተል ከማስቻሉም በላይ አጭር ግን ትርጉም ያለው ማስታወሻ ለመያዝም ይረዳል። የአውራጃ ስብሰባው ካለፈ ከሁለት እስከ አራት ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ስብሰባውን በ30 ደቂቃ ለመከለስ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ፕሮግራም ይያዝለታል። ክለሳውን እንዲያቀርቡ የሚመደቡት ብቃት ያላቸው ሦስት ወንድሞች ክፍሉን ሲያቀርቡ እያንዳንዳችን ተዘጋጅተን አጠር ያለ ሐሳብ ለመስጠት ፈቃደኞች መሆን እንችላለን። የምንሰጠው ሐሳብ አንድ ሰው በአውራጃ ስብሰባው ላይ የተማራቸውን ነገሮች በግል ሕይወቱና በመስክ አገልግሎት ላይ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጋቸው የሚገልጹ ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ወይም ሁለት የተመረጡ አጭር ተሞክሮዎች መናገር ይቻላል። ይህን የአገልግሎት ስብሰባ ክፍል አስደሳችና ትምህርት ሰጪ እንዲሆን ለማድረግ ሁሉም በደንብ ተዘጋጅቶ መምጣቱ ወሳኝ ነው።
መስከረም 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 59 (139)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። እንዲሁም “አንተስ በዚያ ትገኝ ይሆን?” የሚለውን እያነበብህ ተወያዩበት።
15 ደቂቃ:- “የይሖዋ በረከት ባለጸጎች ያደርገናል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት።—ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ጥራዝ 2 ገጽ 804 ከአንቀጽ 6-7 ያለውን ተመልከት።
15 ደቂቃ:- “የሰዎችን ፍላጎት ለመቀስቀስ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ተጠቀሙ።” ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት እና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። በአካባቢው የሰዎችን ትኩረት ከሳቡ ወቅታዊ ሁኔታዎች መካከል የተወሰኑትን ጥቀስ። እነዚህ ወቅታዊ ሁኔታዎች በሕዝቡ ላይ ምን ስጋት ፈጥረዋል? በማመራመር መጽሐፍ ላይ ከገጽ 10-11 ያለውን ተጠቅመህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት ለመክፈት የሚያስችል መግቢያ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል ጥቂት ሐሳቦችን ተናገር። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ዝግጅት የተደረገባቸው ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 90 (204) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 27 (57)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ:- ያለፈው ዓመት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። የጉባኤውን የ2000 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት ጎላ ያሉ እንቅስቃሴዎች ከልስ። ስለተከናወኑት መልካም ነገሮች አመስግን። መሻሻል የሚያስፈልግባቸውን መስኮች ለይተህ ተናገር። ጉባኤው በተሰብሳቢዎች ቁጥር፣ በተመላልሶ መጠየቅ፣ ጥናቶችን በማስጀመርና በመምራት እንዲሁም በመስክ አገልግሎት ላይ አዘውታሪ በመሆን ረገድ ባደረገው እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት አድርግ። ለሚቀጥለው ዓመት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ግቦችን ጠቁም።
20 ደቂቃ:- “የሰዎች ሕይወት አደጋ ተጋርጦበታል!” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በርዕሱ ውስጥ የሚገኙትን ጥቅሶች አጉላ።
መዝሙር 71 (163) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 34 (77)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስከረም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። የጥያቄ ሣጥን የሚለውን ከልስ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
15 ደቂቃ:- መጽሔቶቻችን ዋጋማነታቸው አይቀንስም። የቆዩ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ሲከማቹባችሁ ምን ታደርጋላችሁ? አንዳንድ አስፋፊዎች ጊዜ እንዳለፈባቸው በመቁጠር መጽሔቶቹን ለማስወገድ ይፈልጋሉ። እንደዚህ በማድረግ ፈንታ በመስከረም 1993 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 ላይ የቆዩ ጥቂት መጽሔቶችን ይዘን በመውጣት አስፈላጊ በሆነ ጊዜ እንድናበረክት ማበረታቻ ተሰጥቶን ነበር። ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ የተማሩትን፣ አረጋውያንን እንዲሁም በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን የሚስቡ ወቅታዊ ርዕሶችን መምረጥ ትችላለህ። አጋጣሚውን ስታገኝ ለማበርከት መጽሔቶቹን ዝግጁ አድርገህ ያዝ። ርዕሶችን እንዴት መምረጥና ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። የቆዩ መጽሔቶችን በማበርከት ረገድ አስፋፊዎች የተሳካ ውጤት ያገኙባቸውን ተሞክሮዎች ተናገር።
መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 75 (169)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከሰኞ ጥቅምት 16 ጀምሮ እስከ ዓርብ ኅዳር 17 ድረስ የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ልዩ ስርጭት እንደሚደረግ ተናገር። ልጆችንና አዲሶችን ጨምሮ ሁሉም ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስብ። የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች በቡድናቸው ውስጥ ያሉት አስፋፊዎች በሙሉ በቅንዓት እንዲሳተፉ ከአሁን ጀምረው ማበረታታትና ማደራጀት ይገባቸዋል። ካለፈው የመንግሥት ዜና ስርጭት የተገኙ የሚያንጹ ተሞክሮዎችን ጨምረህ ተናገር።
15 ደቂቃ:- “መሄድ ይኖርብኝ ይሆን?” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ውሳኔ በማድረግ ረገድ አስተዋይ መሆን ለምን እንደሚያስፈልግ ተናገር። በምሳሌ 22:3 ላይ የሚገኘውን ምክር እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል አስረዳ። ነሐሴ 15, 1988 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22 ላይ የሚገኙትን ለጥንቃቄ የሚረዱ ሐሳቦች ጨምረህ ተናገር።
15 ደቂቃ:- ውይይት ስለ መጀመር የሚገልጹ ተሞክሮዎች። መስከረም 11 በሚጀምር ሳምንት ባደረግነው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ በመግቢያችን ላይ ወቅታዊ ሁኔታዎችን አንስተን የሰዎችን ፍላጎት በመቀስቀስ ውይይት እንድንጀምር ሐሳብ ቀርቦልን ነበር። እነዚህን ሐሳቦች ተጠቅመው ጥሩ ውጤት ያገኙ አስፋፊዎች ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 44 (105) እና የመደምደሚያ ጸሎት።