የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/00 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 11/00 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

ኅዳር 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 2 (4)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

13 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

22 ደቂቃ:- “በመንግሥት ዜና ቁ. 36 አማካኝነት የተቀሰቀሰው የሰዎች ፍላጎት እንዲያድግ ማድረግ።” ከ1-5 ያሉትን አንቀጾች በጥያቄና መልስ በሚደረግ ውይይት ሸፍን። እስከ አሁን ያልተሠራባቸው ክልሎች ካሉ ለመሸፈን ጉባኤው ያደረገውን ዝግጅቶች ተናገር። በአንቀጽ 7 እና 8 ላይ ተመላልሶ መጠየቅ ስለማድረግ የተጠቀሱትን አቀራረቦች ከልስና እያንዳንዳቸውን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትሎ የመርዳትንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር የመጣርን አስፈላጊነት አጉላ። በአንቀጽ 9 እና በጥቅሶቹ ላይ ውይይት በማድረግ ደምድም።

መዝሙር 30 (63) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 21 (46)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ ሁለት ላይ በቀረቡት ጥያቄዎች መሠረት ታኅሣሥ 4 በሚጀምረው ሳምንት ላይ በምናደርገው የአገልግሎት ስብሰባ መጽሐፍ ቅዱስ —⁠ትክክለኛ ታሪክና አስተማማኝ ትንቢት የሚለውን ቪዲዮ በሚመለከት ውይይት እንደሚቀርብ ተናገር። በዚያ ቀን ለሚኖረው ውይይት አስቀድሞ ለመዘጋጀት እንዲረዳ ቪዲዮውን የማየት አጋጣሚ ያላቸው ካሉ አይተው መምጣት ይችላሉ።

15 ደቂቃ:- የመንግሥት ዜና ቁ. 36 በማሰራጨት የተገኙ ተሞክሮዎች። የአገልግሎት ክልሉን በመሸፈን ረገድ የተገኘውን ውጤት ተናገር። በጉባኤው ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአገልግሎት የተካፈለ ሰው አለ? የቤት ባለቤቶች የሰጡትን ገንቢ አስተያየት ጥቀስ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ያስጀመሩ አስፋፊዎች አሉ? ካሉ እንዴት እንዳስጀመሩ እንዲናገሩ ወይም በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ተከታትለው እንዲረዱ ሁሉንም አሳስብ።

20 ደቂቃ:- “መስበካችሁን ቀጥሉ!” በንግግርና በቃለ ምልልስ የሚቀርብ። አንዳንዶች ከይሖዋ ድርጅት ጋር መተባበር ከጀመሩ በኋላ በስብከቱ ሥራ ጸንተው ኖረዋል። አዎንታዊ አመለካከት ይዘው ይህን በማድረጋቸው ደስታ አግኝተዋል። (እውቀት መጽሐፍ ገጽ 179 አን. 20ን እና ግንቦት 1, 1992 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21-2 አን. 14-15ን ተመልከት።) ለብዙ ዓመታት በንቃት ያገለገለ አንድ አስፋፊ የስብከቱን ሥራ በመሥራት የጸናው ለምን እንደሆነ እንዲናገር ጋብዝ።

መዝሙር 63 (148) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 34 (77)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች። አስፋፊዎች የኅዳር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው።

35 ደቂቃ:- የአውራጃ ስብሰባውን ፕሮግራም ጎላ ያሉ ነጥቦች ከልሱ።

መዝሙር 78 (175) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 12 (32)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “መጽሐፍ ቅዱስ —⁠ትክክለኛ . . .” የሚለውን ሣጥን አቅርብ።

15 ደቂቃ:- ቴሌቪዥን የማየት ልማዴን ልቆጣጠር የምችለው እንዴት ነው? አንድ ሽማግሌ ቴሌቪዥን በማየት ብዙ ሰዓት የሚያጠፋን አንድ ወጣት ወንድም ያነጋግረዋል። ወጣቱ ወንድም በመጀመሪያ ቴሌቪዥን ማየት ጉዳት የለውም ብሎ ይከራከራል። አንድ የመዝናኛ ዓይነት እንደሆነና ምንም ጉዳት እንዳላስከተለበት ይናገራል። ሽማግሌው ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ከሚለው መጽሐፍ ምዕራፍ 36 ላይ ዋና ዋና ነጥቦች ይጠቅሳል። ቴሌቪዥን በማየት ብዙ ሰዓት ማጥፋት የግል ጥናት ለማድረግ፣ አገልግሎት ለመሄድ ወይም ጉባኤውን በሚያስፈልገው ነገር ለመርዳት የሚያስችለንን ጠቃሚ ጊዜ እንደሚሻማ ይገልጽለታል። ወጣቱ ወንድም ስለተሰጠው ምክር የተሰማውን አድናቆት ይገልጽና በመንፈሳዊ ጥቅም ለማግኘት ሲል ቴሌቪዥን በማየት ልማዱ ላይ ማስተካከያ እንደሚያደርግ ይናገራል።

20 ደቂቃ:- “በትክክለኛው ጊዜ የተነገረ ቃል።” ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይትና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። ብዙዎች በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ልዩ ችሎታ እንደሚያስፈልጋቸው በማሰብ ውይይት በመጀመር ረገድ ብቃት እንደሌላቸው ይሰማቸዋል። አዳዲስ አስፋፊዎችንና ትንንሽ ልጆችን ጨምሮ ሁላችንም ተገቢውን ጥረት በማድረግ እንዴት ውይይት ማስጀመር እንደምንችል አስረዳ። ሐሳብ የተሰጠባቸውን አቀራረቦች ከልስ። አቀራረቦቹ ከባድ አለመሆናቸውን አጉላና ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቧቸው አድርግ። ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ተጨማሪ አቀራረቦች በመጋቢት 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ እንደሚገኙ ጠቁም። በአገልግሎት ተጨማሪ ደስታ እንዲያገኙ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው ሁሉንም አበረታታ።

መዝሙር 32 (70) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ