የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/00 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 11/00 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ኅዳር:- የመንግሥት ዜና ቁ. 36 ስርጭት ይቀጥላል። ጉባኤዎች በክልላቸው ውስጥ ለሚገኝ ለእያንዳንዱ የቤት ባለቤት የመንግሥት ዜና ቁ. 36ን አበርክተው ከጨረሱ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ወይም እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ለዘላለም መኖር ወይም ፍጥረት የተባሉትን መጻሕፍት ማበርከት ይቻላል። ታኅሣሥ:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት ወይም በምድር ላይ በገነት ውስጥ ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥር:- ከ1986 በፊት የታተመ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። እነዚህ መጽሐፎች የሌሏቸው ጉባኤዎች የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ (እንግሊዝኛ) የሚለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የካቲት:- ሕይወት እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት? (እንግሊዝኛ)፣ ራእይ —⁠ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል፣ ወይም ጉባኤው ያለው ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ።

◼ የመንግሥት ዜና የማሰራጨቱ ዘመቻ ካበቃ በኋላ የተረፈ የመንግሥት ዜና ቁ. 36 ያላቸው ጉባኤዎች አስፋፊዎች ከቤት ወደ ቤትም ሆነ በማንኛውም ቦታ ሌሎች ትራክቶች በሚያበረክቱበት መንገድ እንዲያበረክቱ ማበረታታት ይችላሉ። አመቺ ከሆነ አስፋፊዎች እቤታቸው ላልተገኙ ሰዎች በዚያ የሚያልፍ መንገደኛ እንዳያይ አድርገው አንድ የመንግሥት ዜና ትተው መሄድ ይችላሉ። በጣም አስፈላጊ መልእክት የያዘውን ይህን የመንግሥት ዜና ሙሉ በሙሉ ለማሰራጨት ጥረት መደረግ ይኖርበታል።

◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው ታኅሣሥ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነገር አለበት።

◼ ጉባኤዎች በኅዳር ወር ከሚልኩት የጽሑፍ ትእዛዝ ጋር የ2001 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። መጽሐፉ የሚገኘው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው። መጽሐፉ ደርሶን እስክንልክላችሁ ድረስ በጉባኤያችሁ የጽሑፍ መላኪያ ዝርዝር ላይ “በቅርቡ የሚደርስ” ተብሎ ይወጣል። የዓመት መጽሐፍ በልዩ ትእዛዝ የሚገኝ ጽሑፍ ነው።

◼ በሚቀጥለው ዓመት ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ውስጥ በሚደረገው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆነው ለማገልገል የሚፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች ወይም ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ቅርንጫፍ ቢሮው የማመልከቻ ቅጽ እንዲልክላቸው በጉባኤያቸው ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች በኩል መጠየቅ ይችላሉ። አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ሞልተው ማመልከቻውን እስከ ጥር 20, 2001 ድረስ ወደ እኛ መላክ እንዲችሉ ቅጽ ማዘዝ ያለባቸው እስከ ታኅሣሥ 31, 2000 ነው።

◼ በድጋሚ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦ አማርኛ:- የዳንኤል ትንቢት፣ አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?፤ አረብኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፤ እንግሊዝኛ:- የሰው ዘር ያደረገው ፍለጋ፣ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ ሰብሚሽን፣ መለኮታዊ ስም፣ አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?፣ የይሖዋ ምሥክሮች እና ትምህርት፣ እነሆ!፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፣ የውዳሴ መዝሙር (ትልቁ )፣ መጽሔት መያዣ ማኅደር። የቴፕ ክሮች:- መዝሙር፣ ዮሐንስ። የድራማ ክሮች:- ቢ ዌር ኦቭ ሉዚንግ ፌይዝ፣ ጅሆቫስ ኔም ቱ ቢ ዲክለርድ። የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር በCD ፣ የውዳሴ መዝሙር (8) በCD። የቪዲዮ ክሮች:- የይሖዋ ምሥክሮች፣ ኒው ዎርልድ ሶሳይቲ፣ ኖኅ፣ ስታንድ ፈርም።

◼ አዲስ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦ አረብኛ:- የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች፤ እንግሊዝኛ:- የ2001 ቀን መቁጠሪያ፤ የመንግሥቱ ጣዕመ ዜማዎች —⁠ቁ. 9 በCD፣ በCD የሚገኝ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ላይብረሪ 1999፤ ፈረንሳይኛ:- ትራክት ቁ. 73 የይሖዋ ምሥክሮች እነማን ናቸው?፤ በCD የሚገኝ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ላይብራ 1999፤ ትግርኛ:- የዳንኤል ትንቢት፣ ታላቅ ሰው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ