ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የጽሑፍ ክለሳ
እባክህ ለትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ስጠው
ለቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የጽሑፍ ክለሳ የተዘጋጀ የመልስ ወረቀት። ክለሳው የተውጣጣው ከአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ [የ1954 እትም ]፣ ከመጠበቂያ ግንብ [W-am ]፣ “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” (የ1990 እትም) [Si ] ከተባለው መጽሐፍ እንዲሁም ከመስከረም 4 እስከ ታኅሣሥ 18, 2000 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ ከሚሸፈነው ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ነው።
መመሪያዎች፦ እያንዳንዱ ተሳታፊ በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ለክለሳው የወጡትን ጥያቄዎች መያዝ አለበት። ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የመልስ መጻፊያ ወረቀት ያላቸው መሆኑን አረጋግጥ። ከዚያ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች እንዲጀምሩ መንገር ይኖርበታል። ክለሳው 25 ደቂቃ የሚወስድ ሲሆን ሰዓቱ ሲሞላ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ጥያቄዎቹንና መልሶቹን ለአድማጮች ያነብላቸዋል (ወይም በአንዳንዶቹ ጥያቄዎች ላይ አድማጮች እንዲሳተፉ ይጠይቃል)። ይበልጥ ከባድ በሆኑ ጥያቄዎች ላይ በማተኮር ተሳታፊዎቹ ሁሉ መልሶቹ ግልጽ እንዲሆኑላቸው ይረዳቸዋል። እያንዳንዱ ተማሪ የራሱን ወረቀት ሊያርም ይችላል። የመልስ ወረቀቶች አይሰበሰቡም። መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን አማራጮች በሙሉ በመልስ ወረቀቱ ላይ ማስፈር ስለማይቻል ማንኛውም መልስ በዚህ የመልስ ወረቀት ላይ ባይገኝም እንኳ ተስማሚ ከሆነና አሁን ካለን ግንዛቤ ጋር የሚሄድ ከሆነ ተቀባይነት ይኖረዋል። ክለሳው ከመደረጉ በፊት ይህን የመልስ ወረቀት ጉባኤው እንዲያነበው አይደረግም። ይሁን እንጂ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከክለሳው በፊት ባሉት ሳምንታት በስብሰባው ላይ መጉላት ያለባቸውን ነጥቦች ለማጉላት ሊጠቀምበት ይችላል። በክለሳው ጊዜ መጠቀም የሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው።
[ለትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካቾች የተሰጠ ማሳሰቢያ:- ጥያቄው ከየትኛው ጽሑፍ እንደተወሰደ ከመገለጹ በፊት ያለው በሰያፍ የተጻፈ ቁጥር ባለፈው ጊዜ ከተደረገው ክለሳ ጀምሮ በመቁጠር ትምህርቱ በስንተኛው ሳምንት ላይ እንደተጠና የሚያመለክት ነው።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር እውነት ወይም ሐሰት እያልክ መልስ:-
1. አቢሳ ሳሚን እንዳይገድለው ዳዊት የከለከለው ሳሚ በዳዊት ላይ የሰነዘረው ክስ ትክክል ስለነበረ ነው። (2 ሳሙ. 16:5-13) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w99 5/1 ገጽ 32 አን. 3ን ተመልከት።]
2. ንጹሕና በተገቢ መንገድ የሰለጠነ ሕሊና ከአምላክ ጋር የጠበቀ የግል ዝምድና እንድንመሠርት የሚረዳን ከመሆኑም በላይ ለደህንነታችንም የግድ አስፈላጊ ነው። (ዕብ. 10:22፤ 1 ጴጥ. 1:15, 16) [w98 9/1 ገጽ 4 አን. 4]
3. የአንደኛ ነገሥት ዘገባ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ በእስራኤልና በይሁዳ ከገዙት 14 ነገሥታት መካከል በይሖዋ ዓይን ትክክል የሆነውን ያደረጉት 2 ብቻ መሆናቸውን ስለሚገልጽ ከታሪካዊ ይዞታው ባሻገር ለአንድ ክርስቲያን የሚሰጠው ጥቅም የለውም። [si ገጽ 64 አን. 1]
4. የኢየሱስ የሺ ዓመት ግዛት ሰላምና ብልጽግና ሰፍኖበት ከነበረው ከሰሎሞን የ40 ዓመት ግዛት ጋር ሊነጻጸር ይችላል። (1 ነገ. 4:24, 25, 29) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w11-111 ገጽ 6 አን. 5ን ተመልከት።]
5. አብያ በክብር መቀበሩ ከኢዮርብዓም ቤተሰብ ውስጥ በታማኝነት ይሖዋን ያመለከው እርሱ ብቻ እንደነበር በግልጽ ያሳያል። (1 ነገ. 14:10, 13) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 4/1 ገጽ 12 አን. 11ን ተመልከት።]
6. አንድ ሰው ክርስቲያናዊ የጥምቀት እርምጃ መውሰዱ የጎለመሰ የአምላክ አገልጋይ መሆኑን ያሳያል። [w98 10/1 ገጽ 28 አን. 2]
7. ይሖዋ ለኤልያስ ከሰው የተለየ ድፍረት የሰጠው ከመሆኑም በላይ ጨርሶ ፍርሃት እንዳይሰማው አድርጎታል። (1 ነገ. 18:17, 18, 21, 40, 46) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w98 1/1 ገጽ 31 አን. 2ን ተመልከት።]
8. የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ትኩረት የሚስብ ሕንፃ የሆነው በግርማውና በውበቱ ብቻ ሳይሆን እጅግ ከፍተኛ ክብር ለተላበሰው ለይሖዋ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ጥላ ስለነበረም ነው። [si ገጽ 69 አን. 26]
9. የሶርያ ወታደሮች ኤልሳዕን እያዩ ማንነቱን መለየት አለመቻላቸው እሱ በተናገረው ቃል አማካኝነት በሶርያ ወታደራዊ ኃይል ላይ የደረሰው ዕውርነት የአእምሮ መታወር እንጂ ቃል በቃል እውር እንዳልሆኑ ከሁኔታው መረዳት እንችላለን። (2 ነገ. 6:18, 19) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ si ገጽ 70-1 አን. 10ን ተመልከት።]
10. ሁለተኛ ነገሥት 11:12 ላይ ተጠቅሶ የሚገኘው ‘ምሥክሩን’ የመስጠት ሥርዓት ንጉሡ በአምላክ ቃል ላይ የሚሰጠው ማብራሪያ የመጨረሻና በተግባር መፈጸም ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ምሳሌያዊ ሥርዓት ነበር። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w91 2/1 ገጽ 31 አን. 6ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ:-
11. ከ1 ዮሐንስ 2:15-17 ጋር በሚስማማ መንገድ አምላካዊ ፍርሃት ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸው ተስማሚ የሆነ ዓለማዊ ሥራ እንዲመርጡ አመራር በሚሰጧቸው ጊዜ ከምን ነገር እንዲርቁ ማሳሰብ አለባቸው? [w98 7/15 ገጽ 5 አን. 3]
12. በ2 ሳሙኤል 18:8 ላይ “ሰይፍ ከዋጠው ሕዝብ ይልቅ ዱር ብዙ ዋጠ” የሚለው አባባል ትርጉም ምንድን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE87 3/15 ገጽ 31 አን. 2ን ተመልከት።]
13. በዛሬው ጊዜ፣ የጎልያድ ዘመድ ከሆኑት ከራፋይም ጋር ሊመሳሰሉ የሚችሉት እነማን ናቸው? ምንስ ለማድረግ ይጥራሉ? (2 ሳሙ. 21:15-22) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w1-110 ገጽ 14 አን. 8ን ተመልከት።]
14. ከ2 ሳሙኤል 6:6, 7 የምንማረው ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት ምንድን ነው? [si ገጽ 63 አን. 30]
15. የሰንበትን ሕግ በመጣሱ ሞት የተፈረደበትን ሰው ከሚመለከተው ጉዳይ የምንማረው ወሳኝ የሆነ መሠረታዊ ሥርዓት ምንድን ነው? (ዘኁ. 15:35) [w98 9/1 ገጽ 20 አን. 1]
16. “የሰሎሞንን ጥበብ ሁሉ” ለመስማት ረዥም መንገድ ተጉዛ የመጣችውን የሳባን ንግሥት መምሰል የምንችለው ምን በማድረግ ነው? (1 ነገ. 10:1-9) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w99 7/1 ገጽ 31 አን. 1-2ን ተመልከት።]
17. በ1 ነገሥት 17:3, 4, 7-9, 17-24 መሠረት ኤልያስ በይሖዋ ላይ እምነት እንዳለው ያሳየባቸው ሦስት መንገዶች ምንድን ናቸው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w92 4/1 ገጽ 19 አን. 5ን ተመልከት።]
18. ናቡቴ የወይን ቦታውን ለአክዓብ ለመሸጥ ፈቃደኛ አለመሆኑ እምቢተኝነቱን የማያሳየው ለምንድን ነው? (1 ነገ. 20:2, 3) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w97 8/1 ገጽ 13 አን. 18ን ተመልከት።]
19. በ2 ነገሥት 6:16 ላይ የሚገኙት ቃላት በዛሬው ጊዜ የሚገኙትን የይሖዋ አገልጋዮች ለማበረታታት የሚያገለግሉት እንዴት ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w98 6/15 ገጽ 18 አን. 5ን ተመልከት።]
20. በዛሬው ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከሲሞናዊነት መጠበቅ ያለባቸው በየትኞቹ መንገዶች ነው? [w98 11/15 ገጽ 28 አን. 5]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር የሚያሟላውን ቃል (ቃላት) ወይም ሐረግ ስጥ:-
21. አንድ እውነተኛ ክርስቲያን _________________________ በመሸነፍ _________________________ በሚያሳዝኑ ልማዶች መካፈል የለበትም። (ምሳሌ 29:25፤ ማቴ. 10:28) [w98 7/15 ገጽ 20 አን. 5]
22. ጳውሎስ ለንጉሥ አግሪጳ ሲመሰክር _________________________ በማድረግ እሱንና አግሪጳን _________________________ ነጥቦች ላይ ትኩረት አድርጓል። (ሥራ 26:2, 3, 26, 27) [w98 9/1 ገጽ 31 አን. 3]
23. አምላክ _________________________ አንዳንዶች አካል እንደሌለው አድርገው ሊያስቡ ቢችሉም አንድ ሰው አዘውትሮ በጥልቅ የሚያደርገው _________________________ ‘የማይታየውን አምላክ እንዲያይ’ ያስችለዋል። (ዕብ. 11:27) [w98 9/15 ገጽ 21 አን. 3-4]
24. የሶርያ ጄኔራል በሆነው _________________________ ሁኔታ እንደታየው አንዳንድ ጊዜ መጠነኛ _________________________ ማሳየት ብዙ በረከት ሊያስገኝ ይችላል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w99 2/1 ገጽ 3 አን. 6-ገጽ 4 አን. 1ን ተመልከት።]
25. የኢዮናዳብ ልብ ከንጉሥ ኢዩ ጋር እንደነበር ሁሉ በዛሬው ጊዜ የሚገኙት _________________________ በምድር ላይ _________________________ የተወከለውን ታላቁን ኢዩ _________________________ በሙሉ ልባቸው ይቀበላሉ እንዲሁም ከእሱ ጋር ይተባበራሉ። (2 ነገ. 10:15, 16) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w98 1/1 ገጽ 13 አን. 5-6ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ምረጥ:-
26. ዳዊት ‘እስራኤልን እንዲቆጥር’ በማነሳሳት ኃጢአት እንዲያሠራ ያደረገው (ሰይጣን፣ ይሖዋ፣ ኢዮአብ) ነበር። (2 ሳሙ. 24:1) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w92 7/15 ገጽ 5 አን. 2ን ተመልከት።]
27. ከ1 ነገሥት 8:1 እና ከመክብብ 1:1 ጋር በሚስማማ መንገድ ሰሎሞን ሕዝቡን የሰበሰበው (ቤተ መቅደሱን ለመገንባት፤ የእስራኤልን ጠላቶች ለማሳደድ፤ ይሖዋን ለማምለክ) ነበር። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ si ገጽ 112 አን. 3ን ተመልከት።]
28. ሰሎሞን ቤተ መቅደሱንና መኖሪያ ቤቱን በኢየሩሳሌም ለመገንባት የወሰደበት የ20 ዓመት ዘመን በ(1919፣ 1923፣ 1931) ጀምሮ በ(1938፣ 1942፣ 1950) ካበቃው መሠረተ ትምህርታዊና ድርጅታዊ አሠራር ማስተካከያ ከተደረገበት ዘመን ጋር ሊመሳሰል ይችላል። (1 ነገ. 9:10) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w92 3/1 ገጽ 20 ሣጥን።]
29. በ2 ነገሥት 2:11 ላይ የሚገኘው “ሰማይ” የሚለው ቃል (አምላክ የሚኖርበትን መንፈሳዊ ቦታ፣ ግዑዙን ጠፈር፣ አእዋፍ የሚበሩበትንና ነፋስ የሚነፍስበትን የምድርን ከባቢ አየር) ያመለክታል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w97 9/15 ገጽ 15 ሣጥን።]
30. ኢየሱስ በናዝሬት ሳይሆን በቤተልሔም እንዲወለድ ምክንያት የሆነውን የሕዝብ ቆጠራ እንዲካሄድ ያዘዘው (ታላቁ ሄሮድስ፣ አውግስጦስ ቄሳር፣ ጢባርዮስ ቄሳር) ነበር። [w98 12/15 ገጽ 7 ሣጥን።]
ቀጥሎ ያሉትን ጥቅሶች ከታች ካሉት ሐሳቦች ጋር አዛምድ:-
መዝ. 15:4፤ 2 ሳሙ. 12:28፤ 2 ሳሙ. 15:18-22፤ 2 ነገ. 3:11፤ ቆላ. 3:13
31. በይሖዋ ቲኦክራሲያዊ ዝግጅት ውስጥ የራስነት ሥልጣን መከበር አለበት። [si ገጽ 63 አን. 30]
32. ለይሖዋ ድርጅትና ለተወካዮቹ ታማኝነት ማሳየት አስፈላጊ ነው። [si ገጽ 63 አን. 30]
33. አንድ ሰው ለይሖዋ ምሕረት ያለው አድናቆት ራሱን እንዲገዛና የሌሎችን ድክመት እንዲሸፍን ሊያነሳሳው ይችላል። [w98 11/1 ገጽ 6 አን. 4]
34. በልዩ አገልግሎት ተሠማርተው ለሚገኙ የይሖዋ ታማኝ አገልጋዮች የእንግዳ ተቀባይነት ባሕርይ ማሳየትና እነሱን በትሕትና ማገልገል መብት ነው። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w97 11/1 ገጽ 30 አን. 8ን ተመልከት።]
35. ምንም እንኳ ያልተጠበቁ አጋጣሚዎች ከገመተው በላይ ሁኔታውን አስቸጋሪ ሊያደርጉበት ቢችሉም ፈሪሃ አምላክ ያለው ሰው ዕዳውን ለመክፈል የገባውን ቃል ለመጠበቅ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። [w98 11/15 ገጽ 27 አን. 1]