የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
የካቲት 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 3 (6)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የካቲት 26 በሚጀምር ሳምንት በምናደርገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ—የሰው ልጅ ካሉት መጻሕፍት ሁሉ እጅግ ጥንታዊ የሆነና ለዘመናችን የሚሠራ መጽሐፍ በተባለው ቪዲዮ ላይ ውይይት ይደረጋል። ውይይቱ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 7 ላይ በሚገኙ ጥያቄዎች ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
15 ደቂቃ:- “በመልካም ሥራ ይሖዋን አስከብሩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። አዋጅ ነጋሪዎች ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 187 አንቀጽ 2-3 ላይ የሚገኙ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ:- “ሌሎችን ማሳመን የሚቻለው እንዴት ነው?” አንድ የመጽሐፍ ጥናት መሪ ከአንድ አቅኚ ወይም ውጤታማ አስፋፊ ጋር በዚህ ርዕስ እንዲሁም በግንቦት 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21-3 ላይ በሚገኘው ርዕስ የተመረጡ ነጥቦች ላይ የተመሠረተ ውይይት ያደርጋሉ። በገጽ 23 ላይ የሚገኘውን “የተማሪህን ልብ መንካት” የሚለውን ሣጥን መርምሩ። በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ በጣም የተለመደ አንድ የሐሰት ሃይማኖት ትምህርት እንደ ምሳሌ አንስታችሁ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ርዕሰ ጉዳይ ምን እንደሚል አንድን ሰው እንዴት ማሳመን እንደሚቻል ተወያዩ።
መዝሙር 90 (204) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 99 (221)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
22 ደቂቃ:- “የይሖዋን ስምና ሥራዎቹን አስታውቁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። አንድ ሽማግሌ በተቻለ መጠን ብዙዎች ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ ለማበረታታት የሚደረገውን ጥረት ጨምሮ በመጋቢትና በሚያዝያ ከፍተኛ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ለማድረግ ጉባኤው ያወጣውን ዕቅድ ይዘረዝራል። ባለፈው ዓመት በሚያዝያ ወር በረዳት አቅኚነት ያገለገሉ አንዳንድ አስፋፊዎች ያገኙትን እርካታ እንዲናገሩ ጋብዝ። ብቃት ያላቸው አገልግሎት ያቆሙ አስፋፊዎች እንደገና አገልግሎት እንዲጀምሩ እንዲሁም ልጆችና ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን ብቃቱን እንዲያሟሉ መርዳት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት አድርግ።—በኅዳር 2000 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።
መዝሙር 10 (27) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የየካቲት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። የአገልግሎት ክልሎችን በልዩ ዘመቻ ለመሸፈን የተደረጉትን ዝግጅቶች ተናገር።
12 ደቂቃ:- እውቀት መጽሐፍን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል ለማሳየት የቀረቡ ሐሳቦች። በመጋቢት ወር እውቀት መጽሐፍ ስታበረክት ምን ዓይነት አቀራረብ ለመጠቀም መርጠሃል? ከዚህ በፊት የወጡ የመንግሥት አገልግሎታችንን የመጨረሻ ገጾች መለስ ብለህ ከተመለከትክ ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ ምን ብለህ እንደምትናገር የሚጠቁሙ ሐሳቦችን ጭምር አካትተው የያዙ አቀራረቦችን ታገኛለህ። ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ወይም ሦስት አቀራረቦችን ከልስ። (ታኅሣሥ 1995፤ መጋቢት፣ ሰኔ፣ ኅዳር 1996፤ ሰኔ 1997፤ መጋቢት 1998) ከኅዳር 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኙትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዱ ሁለት ቀጥተኛ አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ሁሉም አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ልዩ ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
25 ደቂቃ:- “መጽሐፍ ቅዱስ—የሰው ልጅ ካሉት መጻሕፍት ሁሉ እጅግ ጥንታዊ የሆነና ለዘመናችን የሚሠራ መጽሐፍ ለተባለው የቪዲዮ ክር አድናቆት ማሳየት።” በገጽ 7 ላይ የሚገኙ ጥያቄዎችን በመጠቀም ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ሙሉ በሙሉ እና በከፊል በአጠቃላይ በ37 ቋንቋዎች ከ100 ሚልዮን በሚበልጡ ቅጂዎች የታተመ በመሆኑ በጣም በስፋት የተሰራጨ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሆኑን ጎላ አድርገህ ተናገር። በሚያዝያ ወር የዚህን የቪድዮ ክር ሦስተኛ ክፍል እንመረምራለን። ርዕሱ መጽሐፍ ቅዱስ—በአንተ ሕይወት ውስጥ ያለው ኃይል የሚል ይሆናል።
መዝሙር 21 (46) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 36 (81)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
18 ደቂቃ:- “ይሖዋ ኃይል ይሰጣል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። አድማጮች በጥቅሶቹ ተግባራዊነት ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
22 ደቂቃ:- “አዲስ የመንግሥት አዳራሽ ሲሠራ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነገሮች” የሚለውን ተወያዩበት።
መዝሙር 26 (56) እና የመደምደሚያ ጸሎት።