የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/01 ገጽ 3-4
  • የይሖዋን ስምና ሥራዎቹን አስታውቁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋን ስምና ሥራዎቹን አስታውቁ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 11 የጉባኤው ጸሐፊ በቡድናቸው ውስጥ አገልግሎት ያቆሙ ሰዎች ካሉ ስማቸውን ለመጽሐፍ ጥናት መሪዎቻቸው መስጠት ይኖርበታል። የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አገልግሎት ላቆሙ ሁሉ የእረኝነት ጉብኝት እንዲደረግ ቀዳሚ ሆኖ ዝግጅት ያደርጋል። ግለሰቡ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቢደረግለት ጥሩ እንደሆነ ከተወሰነ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከቀሩት የአገልግሎት ኮሚቴ አባላት ጋር ተመካክሮ ማን ቢያስጠናው እንደሚሻል ይወስናል። ጥናቱ ለረጅም ጊዜ እንዲቀ​ጥል ማድረጉ አስፈላጊ ባይሆንም ጥናቱን የሚመራው ሰው ሰዓቱን፣ ተመላልሶ መጠየቁንና ጥናቱን ሪፖርት ማድረግ ይችላል።
  • 12 ባለፈው የሚያዝያ ወር አንዲት እህት ከቤት ወደ ቤት ስታገለግል መንገድ ላይ ላገኘችው አንድ ወጣት መጽሔት አበረከተችለት። ወጣቱ ባለቤቱ አገልግሎት ያቆመች የይሖዋ ምሥክር መሆኗን ነገራት። የመንግሥት አዳራሹ የት እንደሚገኝ ጠየቃትና እህት ቤታቸው መጥታ እሱንና ባለቤቱን እንድታነጋግራቸው ጋበዛት። በዚህ ምክንያት ባልና ሚስቱ በቀጣዩ ስብሰባ ላይ የተገኙ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀመርላቸው ተስማሙ።
  • 13 በሚደረገው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ለመካፈል ተዘጋጁ! የይሖዋን ስምና ሥራዎቹን እንድናስታውቅ ያሳሰበን መዝሙራዊ “ተቀኙለት፣ ዘምሩለት፣ ተዓምራቱን ሁሉ ተናገሩ። በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ” በማለት አክሎ ተናግሯል። (መዝ. 105:​2, 3) በአገልግሎቱ የምናደርገውን ጥረት በማሳደግና የዚህን ዓመት የመታሰቢያ በዓል እስከ ዛሬ ካከበርነው ሁሉ የበለጠ እንዲሆን በማድረግ ለይሖዋ ታላቅ ስምና ‘ለታላላቅ ሥራዎቹ’ የምንቆረቆር መሆናችንን እናሳይ!
  • ‘የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ ስበኩ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ‘ምሥራቹን በሚገባ መሥክሩ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ስለ ይሖዋ ድንቅ ሥራዎች መናገራችሁን ቀጥሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • የይሖዋን ግርማ በሰፊው አውጁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 2/01 ገጽ 3-4

የይሖዋን ስምና ሥራዎቹን አስታውቁ

1 “እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፣ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ። . . . እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።” (መዝ. 105:​1, 3) እነዚህን ቃላት የጻፈው መዝሙራዊ ስለ ይሖዋና ስለ ‘ሥራዎቹ’ ለሌሎች በመናገር ከፍተኛ ደስታ አግኝቷል። ሥራዎቹ የተባሉት ምንድን ናቸው? ከአምላክ ክብራማ ንግሥና እንዲሁም ካደረገው ‘የማዳን’ ዝግጅት ጋር የተያያዙ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።​—⁠መዝ. 96:​2, 3፤ 145:​11, 12

2 በ2001 ወደሚከበረው የመታሰቢያ በዓል እየተቃረብን ስንሄድ ይሖዋ ያደረገልንን ነገሮች በማሰብ እንድንደሰት የሚያደርጉን በርካታ ምክንያቶች አሉን። እንዴት? የጌታ እራት ለእውነተኛ ክርስቲያኖች ከማንኛውም በዓላት ሁሉ አቻ የማይገኝለት በዓል መሆኑ ምንም አያጠያይቅም። ከአስፈላጊነቱ፣ ካለው ዓላማ ወይም ከአከባበሩ አኳያ ሲታይ ከጌታ እራት ጋር የሚተካከል አንድም ክብረ በዓል የለም። ይህ ይሖዋና ኢየሱስ መዳን የምናገኝበትን መንገድ ለማዘጋጀት ስላደረጉት ነገር የምናስብበት ወቅት ነው። የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት ሰሞን ‘የማዳኑን’ ዝግጅት ለሌሎች በማስታወቅ በመስክ አገልግሎት ከወትሮው የተለየ እንቅስቃሴ ይኖራል ብሎ ማሰቡ የሚጠበቅ ነገር ነው!

3 ረዳት አቅኚ ትሆናለህ? ባለፈው የሚያዝያ ወር ለመጀመሪያ ጊዜ 1, 495 አስፋፊዎች በረዳት አቅኚነት አገልግለዋል። በዚህ ዓመት መጋቢትንና ሚያዝያን ከፍተኛ የአገልግሎት እንቅስቃሴ የሚደረግባቸው ልዩ ወራት ማድረግ እንችል ይሆን? በመጋቢት አምስት ቅዳሜዎችና ሁለት ብሔራዊ በዓላት ያሉት ሲሆን ሚያዝያ አምስት እሑዶችና አንድ ሕዝባዊ በዓል አለው። ሰብዓዊ ሥራ ያላቸው በርካታ አስፋፊዎች ቅዳሜና እሑድ ሙሉ ቀን በማገልገል ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል እንደሚቻል ተገንዝበዋል። አንድ ረዳት አቅኚ በወር ውስጥ የሚጠበቅበትን 50 ሰዓት ለማሟላት በሳምንት ማገልገል የሚኖርበት በአማካይ 12 ሰዓት ብቻ ነው። በገጽ 4 ላይ ባለው ሣጥን ውስጥ ለናሙና የቀረበውን ፕሮግራም በጥንቃቄ ተመልከት። ከእነዚህ ውስጥ ከአንተ ሁኔታ ጋር የሚስማማው የትኛው ፕሮግራም ነው? ካልሆነ በመጋቢትና በሚያዝያ ወራት ረዳት አቅኚ ሆነህ ለማገልገል የራስህን ፕሮግራም ማውጣት ትችላለህ።

4 ሽማግሌዎች ከፍተኛ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ለሚደረግበት ጊዜ ሌሎችን ማነሳሳትና ድጋፍ መስጠት መጀመር ያለባቸው አሁን ነው። ባለፈው ዓመት ሁሉም ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች ረዳት አቅኚ ሆነው ባገለገሉበት በአንድ ጉባኤ ውስጥ በሚያዝያ ወር ከ121 አስፋፊዎች መካከል 64ቱ በረዳት አቅኚነት አገልግለዋል! እንዲሁም በመጋቢትና በሚያዝያ ስድስት ሰዎች ያልተጠመቁ አስፋፊ ሆነው አገልግሎት ሲጀምሩ በመመልከታቸው ጉባኤው በሙሉ ተደስቷል። በእርግጥም፣ ትንንሽ ልጆችና አዲሶች ብቃቱን የሚያሟሉ ከሆነ ሕዝባዊ ምሥክርነት በሚሰጥበት በዚህ እንቅስቃሴ ለመካፈል ሽማግሌዎችን ቀርበው ማነጋገር የሚችሉበት ከሁሉ የተሻለው ጊዜ ይህ ነው።

5 ተጨማሪ ጥረት ማድረግ በረከት ያስገኛል:- የተለየ ግቦችን የሚያወጡና ግባቸው ላይ ለመድረስ ተጨማሪ ጥረት የሚያደርጉ ጉባኤዎች በእጅጉ ይባረካሉ። አንዳንድ ጉባኤዎች ብዙም ያልተሠራባቸውን ክልሎች ለመሸፈን፣ አማራጭ በሆኑ የአገልግሎት መስኮች ለመመስከር ወይም ቤት ያልተገኙትንና በግንባር ማግኘት በሚያስቸግር አካባቢ የሚኖሩትን ከተቻለ በስልክ ለማነጋገር የተለየ ትኩረት መስጠት ይችላሉ።

6 የጤና መታወክ ወይም የዕድሜ መግፋት አንድ ሰው በአገልግሎት የተቻለውን ያህል እንዳይካፈል ሊያግደው ይገባልን? ይህ ሁልጊዜ የሚያጋጥም አይደለም። ለምሳሌ ያህል ካንሰር ያለባት አንዲት የ84 ዓመት እህት እግሯ ቢያብጥባትም በሚያዝያ ወር ረዳት አቅኚ ሆና አገልግላለች። በስልክ የሚሰጠው ምሥክርነት በአገልግሎት ሙሉ ተሳትፎ እንድታደርግና ይሖዋን የምታወድስበትን የጊዜ መጠን ከፍ እንድታደርግ አስችሏታል። ይህ ደግሞ እሷንም ሆነ ጉባኤውን በእጅጉ አነቃቅቷል።

7 ለመታሰቢያው በዓል ጥሩ ዝግጅት አድርጉ:- በዚህ ዓመት የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ሚያዝያ 8 ነው። ይህ ዕለት እሑድ ላይ የሚውል መሆኑ ብዙ ሰዎች በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ጥሩ አጋጣሚ ይከፍታል። ሁላችንም (1) ራሳችን በበዓሉ ላይ በመገኘትና (2) ሌሎች በበዓሉ ላይ አብረውን እንዲገኙ በመጋበዝ ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር እንዲኖረን ማድረግ እንችላለን። እነማንን መጋበዝ ይኖርብናል?

8 በተደጋጋሚ ጊዜ ተመላልሶ መጠየቅ ባታደርግላቸውም እንኳ ለእውነት መጠነኛ ፍላጎት አሳይተው የነበሩ ሰዎችን ለማወቅ የመስክ አገልግሎት ማስታወሻህን ተመልከት። የመታሰቢያው በዓል ከሚከበርበት ዕለት ሁለት ወይም ሦስት ሳምንት ቀደም ብለህ ሁሉንም ሄደህ በመጎብኘት የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ ወረቀት ስጣቸው። ሁኔታህ የሚፈቅድልህ ከሆነ በዓሉ ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያሳዩትን አብረውህ እንዲሄዱ አድርግ።

9 አንዳንድ ጉባኤዎች የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ ወረቀት የሚጠቀሙበት የተወሰነውን ብቻ ነው። የመጋበዣ ወረቀቱ በሙሉ መሰራጨት ይችል ዘንድ የጉባኤ ጸሐፊዎች ቀደም ብሎ ለጉባኤው እንዲሰጥ ማድረግ አለባቸው። በመጋበዣው ወረቀት ግርጌ ላይ የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበትን ሰዓትና ቦታ በታይፕ ወይም በጥሩ የእጅ ጽሑፍ መጻፍ ትፈልግ ይሆናል። ወይም የመታሰቢያውን በዓል የምታከብሩት በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ ከሆነ አዳራሹ የሚገኝበትን ቦታ የሚጠቁመውን የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት አብረህ መስጠት ትችላለህ። ለማስታወስ ያክል፣ የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ወረቀት በተቻለ መጠን ለቤቱ ባለቤት በእጅ መሰጠት አለበት።

10 አገልግሎት ያቆሙ ሰዎ​ችን አትርሱ:- አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ራሱን ለይሖዋ ወስኖ ይህንን ውሳኔውን በውኃ ጥምቀት ሲያሳይ መመልከቱ በጣም የሚያስደስት ነው። ይሁን እንጂ በየ​ዓመቱ ከመካከላችን አንዳንዶች ከእኛ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያቋርጣሉ እንዲሁም ስለ ይሖዋና ስለ ሥራዎቹ ለሌሎች መናገራቸውን ያቆማሉ። ስለ እነርሱ የምናስብበት በቂ ምክንያት አለን። አገልግሎት ያቆሙ ብዙዎቹ እውነትን እርግፍ አድርገው ባይተዉም በደረሰባቸው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት፣ በግል ችግር ወይም በኑሮ ጭንቀቶች ምክንያት መስበካቸውን አቁመው ሊሆን ይችላል። (ማቴ. 13:​20-22) በመንፈሳዊ በተዳከመ ሁኔታ ላይ የሚገኙት እነዚህ ሰዎች በሰይጣን ሥርዓት ጨርሶ ከመዋጣቸው በፊት ወደ ጉባኤ እንዲመለሱ እርዳታ ማግኘት አለባቸው። (1 ጴ⁠ጥ. 5:​8) አገልግሎት ካቆሙት መካከል አስፋፊ የመሆን ብቃቱ ያላቸው ሁሉ በዚህ የመታሰቢያ በዓል ወቅት ምሥራቹን በመስበኩ ሥራ እንደገና መካፈል እንዲጀምሩ ለመርዳት ልዩ ጥረት ማድረግ እንፈልጋለን።

11 የጉባኤው ጸሐፊ በቡድናቸው ውስጥ አገልግሎት ያቆሙ ሰዎች ካሉ ስማቸውን ለመጽሐፍ ጥናት መሪዎቻቸው መስጠት ይኖርበታል። የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አገልግሎት ላቆሙ ሁሉ የእረኝነት ጉብኝት እንዲደረግ ቀዳሚ ሆኖ ዝግጅት ያደርጋል። ግለሰቡ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቢደረግለት ጥሩ እንደሆነ ከተወሰነ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከቀሩት የአገልግሎት ኮሚቴ አባላት ጋር ተመካክሮ ማን ቢያስጠናው እንደሚሻል ይወስናል። ጥናቱ ለረጅም ጊዜ እንዲቀ​ጥል ማድረጉ አስፈላጊ ባይሆንም ጥናቱን የሚመራው ሰው ሰዓቱን፣ ተመላልሶ መጠየቁንና ጥናቱን ሪፖርት ማድረግ ይችላል።

12 ባለፈው የሚያዝያ ወር አንዲት እህት ከቤት ወደ ቤት ስታገለግል መንገድ ላይ ላገኘችው አንድ ወጣት መጽሔት አበረከተችለት። ወጣቱ ባለቤቱ አገልግሎት ያቆመች የይሖዋ ምሥክር መሆኗን ነገራት። የመንግሥት አዳራሹ የት እንደሚገኝ ጠየቃትና እህት ቤታቸው መጥታ እሱንና ባለቤቱን እንድታነጋግራቸው ጋበዛት። በዚህ ምክንያት ባልና ሚስቱ በቀጣዩ ስብሰባ ላይ የተገኙ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀመርላቸው ተስማሙ።

13 በሚደረገው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ለመካፈል ተዘጋጁ! የይሖዋን ስምና ሥራዎቹን እንድናስታውቅ ያሳሰበን መዝሙራዊ “ተቀኙለት፣ ዘምሩለት፣ ተዓምራቱን ሁሉ ተናገሩ። በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ” በማለት አክሎ ተናግሯል። (መዝ. 105:​2, 3) በአገልግሎቱ የምናደርገውን ጥረት በማሳደግና የዚህን ዓመት የመታሰቢያ በዓል እስከ ዛሬ ካከበርነው ሁሉ የበለጠ እንዲሆን በማድረግ ለይሖዋ ታላቅ ስምና ‘ለታላላቅ ሥራዎቹ’ የምንቆረቆር መሆናችንን እናሳይ!

[ሣጥን]

በሳምንት 12 ሰዓት በማገልገል ረዳት አቅኚ መሆን የሚያስችል የተለያየ ፕሮግራም

ቀን ሰዓት

ሰኞ 1 2 − −

ማክሰኞ 1 − 3 −

ረቡዕ 1 2 − 5

ሐሙስ 1 − 3 −

አርብ 1 2 − −

ቅዳሜ 5 4 3 5

እሁድ 2 2 3 2

ድምር፦ 12 12 12 12

ከእነዚህ ውስጥ ከአንተ ሁኔታ ጋር የሚስማማ ፕሮግራም ይኖር ይሆን? ከሌለ ለምን የራስህን ፕሮግራም አታወጣም?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ