ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች የካቲት:- ሕይወት—እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት? (እንግሊዝኛ)፣ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!፣ ወይም ጉባኤው ያለው ማንኛውም ባለ 192 ገጽ የቆየ መጽሐፍ። በአማርኛ መንግሥትህ ትምጣ እና በሕይወት መትረፍ የተባሉትን መጻሕፍት ለማበርከት ትኩረት ስጡ። መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ እና ግንቦት:- የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግላቸው ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝ ይቻላል። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመርን ግብ በማድረግ እውቀት መጽሐፍን ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹርን አበርክቱ።
◼ የ2001 አውራጃ ስብሰባ ጊዜያዊ ፕሮግራም:-
ጥቅምት 12-14ድሬዳዋ
ጥቅምት 19-21አዲስ አበባ*
ጥቅምት 26-28አዲስ አበባ+
ጥቅምት 26-28ጅማ
ጥቅምት 26-28መቀሌ
ኅዳር 2-4አዲስ አበባ
ኅዳር 2-4ደሴ
ኅዳር 2-4ነቀምት
ኅዳር 9-11ሻሸመኔ
ኅዳር 9-11ባሕር ዳር
* በምልክት ቋንቋም ይኖራል።
+ በእንግሊዝኛ ቋንቋም ይኖራል።
◼ መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እሱ የወከለው ሰው የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ምርመራው እንዳለቀ ውጤቱን የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች የአገልግሎት እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ መድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎቹ እርዳታ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት የማኅበሩን ዓመታዊ S-201 ደብዳቤዎች ተመልከቱ። እንዲሁም የመንግሥት አገልግሎታችን 9-68 ገጽ 5 አንቀጽ 12-20ን ተመልከቱ።
◼ ጸሐፊው ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች የቀረበ መጠይቅ ቅጽ (S-82) የሞሉትን የተጠመቁ አስፋፊዎች ሁኔታ በሚመለከት በአካባቢ ሕንፃ ሥራ ኮሚቴው እጅ ያለው መረጃ ወቅታዊ መሆኑን መከታተል አለበት። በፈቃደኛ ሠራተኛው ሁኔታ ላይ ለውጥ ካለ ማለትም ወደ ሌላ ጉባኤ ከሄደ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ወይም ሽማግሌ ሆኖ ከተሾመ ወዲያውኑ አዲስ ቅጽ ተሞልቶ መላክ ይገባዋል። ፈቃደኛ ሠራተኛው የፖስታ ሣጥን ቁጥር ወይም ስልክ ቁጥር ከለወጠ ወይም በጉባኤ ውስጥ እንደ ቀድሞው በጥሩ አቋም ላይ የማይገኝ ከሆነ ሽማግሌዎች ወዲያውኑ ለአካባቢ ሕንፃ ሥራ ኮሚቴው በደብዳቤ ማሳወቅ ይገባቸዋል።
◼ ለማንም ባልተመደበ የአገልግሎት ክልል ውስጥ የሚያገለግሉ አስፋፊዎች እውቀት መጽሐፍ ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ማበርከት ይችላሉ። የቤቱ ባለቤት እነዚህ ጽሑፎች ካሉት ማንኛውንም ሌላ ጽሑፍ ማበርከት ይቻላል። እንደዚህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥም የቆዩ መጽሔቶችን ወይም ደግሞ መንግሥትህ ትምጣ፣ በሕይወት መትረፍ፣ ለዘላለም መኖር፣ በዓይን የማይታዩ መናፍስት (እንግሊዝኛ)፣ በደስታ ኑር፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት የመሳሰሉትን ጽሑፎች ማበርከት ትችላላችሁ። ሁሉም ቤታቸው ላልተገኙ ሰዎች የሚተዉላቸውን ወይም ጽሑፍ ለማይወስዱ ሰዎች የሚያበረክቷቸው የተለያዩ ትራክቶች ይዘው መሄድ ይገባቸዋል። ልዩ አቅኚዎች ለማንም ባልተመደቡ የአገልግሎት ክልሎች ውስጥ በሚሠሩበት ጊዜና በክልሎቹ አቅራቢያ ጉባኤ በሚኖርበት ጊዜ ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ተከታትሎ ለመርዳት ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል።
◼ ቤተሰቦች—የመጽሐፍ ቅዱስን ንባብ የሕይወታችሁ ክፍል አድርጉት! የተባለው የእንግሊዝኛ የቴፕ ክር በብዛት አለን። ብዙ ቤተሰቦች በቅርብ ባደረግነው የአውራጃ ስብሰባ ላይ የቀረበው የዚህ ድራማ ክር ያላቸው አይመስልም።
◼ የአስተዳደር አካሉ ከሌሎች ጉዳዮች ጎን ለጎን ሰዎች ማንበብና መጻፍ እንዲማሩ ለመርዳት በምናደርገው ጥረት የተገኙ ውጤቶችን መስማት ይፈልጋል። ይህም ራሳቸውን ወስነው የተጠመቁትንም ሆነ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች የሚጨምር ነው። በጣም ብዙ ሰዎች ማንበብና መጻፍ እንዲማሩ እርዳታ እንዳገኙ ይሰማናል። ቢሆንም ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ የደረሰን ሪፖርት ሁለት ሰዎች ብቻ እርዳታ እንዳገኙ የሚገልጽ ነው። በመሆኑም በእጃችን ያለውን ሪፖርት ማስተካከል እንድንችል ሁላችሁም ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ ማንበብና መጻፍ እንዲማሩ የረዳችኋቸውን ሰዎች ብዛት ለጉባኤያችሁ ጸሐፊ እንድታሳውቁ እንጠይቃለን። ወደፊትም እባካችሁ እንደዚህ ያለውን ሪፖርት ለወረዳ የበላይ ተመልካቹ አስታውቁ። ማንበብና መጻፍን የተማሩ መኖራቸው በጣም ያስደስተናል። እንዲሁም ሰዎችን በዚህ ረገድ በመርዳት የተሳተፋችሁትን ሁሉ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን።—ራእይ 1:3