ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ በሚደረግበት ወቅት ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝ ይቻላል። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመርን ግብ በማድረግ እውቀት መጽሐፍን ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹርን አበርክቱ። ሰኔ:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ።
◼ በሚያዝያ በረዳት አቅኚነት ለማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች ከወዲሁ እቅድ ማውጣትና ማመልከቻቸውን ቀደም ብለው መመለስ ይገባቸዋል። ይህም ሽማግሌዎች አስፈላጊ የሆኑ የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶችን እንዲያደርጉ እንዲሁም በቂ መጽሔቶችንና ሌሎች ጽሑፎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል። ረዳት አቅኚዎች ሆነው እንዲያገለግሉ የተፈቀደላቸው በሙሉ ስም ዝርዝራቸው ለጉባኤው መነበብ ይኖርበታል።
◼ የመታሰቢያው በዓል እሁድ ሚያዝያ 8, 2001 ይከበራል። በዚያ ዕለት ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ በስተቀር ሌላ ስብሰባ አይኖርም። ሽማግሌዎች የመጠበቂያ ግንብ ጥናት በሌላ ቀን እንዲመራ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ይችላሉ።
◼ ጉባኤ የሚሰበሰቡ ሁሉ የግል ኮንትራታቸውን ጨምሮ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ኮንትራት ሲያስገቡም ሆነ ሲያሳድሱ መላክ ያለባቸው በጉባኤው በኩል ነው።
◼ ማኅበሩ አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ማኅበሩ ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ጽሑፎችን ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማስታወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። የትኞቹ ጽሑፎች በልዩ ትእዛዝ እንደሚገኙ እባካችሁ አትርሱ።
◼ አዲስ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ:- የይሖዋ ምሥክሮች—እነማን ናቸው?፤ ፈረንሳይኛ:- የይሖዋ ምሥክሮች—እነማን ናቸው?፣ የ2001 የቀን መቁጠሪያ፤ ትግርኛ:- የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ (29 መዝሙሮች)።
◼ እንደገና ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው፦ አማርኛ:- የውይይት አርዕስት፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2001፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊ ስም፣ T-21 (በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት)። እንግሊዝኛ:- የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል፣ አወር ፕሮብለምስ—ሁ ዊል ኸልፕ አስ ሶልቭ ዘም?፤ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የውዳሴ መዝሙር (ትንሹ)፣ ኪንግደም ኢንተርሊንየር፣ የ1987 መጠበቂያ ግንብ ጥራዝ፣ የ1994 ንቁ! ጥራዝ፤ የቴፕ ክሮች:- (ጽሑፎች) ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት (አምስት ክሮችን የያዘ አልበም)፣ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? (4 ክሮችን የያዘ አልበም)፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን መማሪያ መጽሐፌ (4 ክሮችን የያዘ አልበም)፤ (ድራማዎች) ዱዊንግ ዋት ኢዝ ራይት ኢን ጀሆቫስ አይስ፣ ጀሆቫ ዴሊቨርስ ኦል ዞስ ኮሊንግ አፕኦን ሂዝ ኔም፣ ዱኢንግ ጎድስ ዊል ዊዝ ዚል፣ ቢዌር ኦቭ ሉዚንግ ፌይዝ ባይ ድሮዊንግ አዌይ ፍሮም ጀሆቫ፤ (የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች) ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ሥራ፣ ራእይ፤ የቪዲዮ ክሮች:- መጽሐፍ ቅዱስ —በአንተ ሕይወት ውስጥ ያለው ኃይል። ፈረንሳይኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ ሮድ ቱ ፓራዳይዝ (ለእስላሞች የተዘጋጀ)። ብሬይል:- የተለያዩ ጽሑፎች ስለሚደርሱን እባካችሁ ጠይቃችሁ ተረዱ።