የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/01 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 3/01 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

መጋቢት 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 47 (112)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “ሚያዝያ​—⁠‘ጠንክረን የምንሠራበትና የምንጋደልበት’ ወር።” (ከአንቀጽ 1-13) በሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። በሚያዝያ ወር ማከናወን የምንፈልገውን በተመለከተ ቀስቃሽ በሆነ መንገድ በውይይት የሚቀርብ። በጉባኤው ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ክርስቲያን በዚያ ወር በአገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ በወጣው ግብ ላይ ለመድረስ የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ አበረታታ።

መዝሙር 63 (148) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 73 (166)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ:- የ 2001 የዓመት መጽሐፍን በሚገባ ተጠቀሙበት። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በገጽ 31 ላይ የሚገኘውን “የ2000 አጠቃላይ ድምር” የሚለውን ከልስ። ከገጽ 3-5 ላይ የሚገኘውን “የአስተዳደር አካል ደብዳቤ” ሐሳብ ተናገር። አንዳንድ አድማጮች ከአዲሱ የዓመት መጽሐፍ ላይ በግላቸው አበረታችና እምነት የሚያጠነክር ሆኖ ያገኙትን አንድ ሪፖርት ወይም ተሞክሮ እንዲናገሩ አድርግ። ዓለም አቀፉ የቤቴል ቤተሰብ እንደሚያደርገው ሁሉ እያንዳንዱ ቤተሰብ አንድ ላይ ሆኖ የዓመት መጽሐፉን በዓመት ውስጥ አንብቦ እንዲጨርስ አበረታታ። በገጽ 255 ላይ የሚገኙትንና ለክለሳ ታስበው የተዘጋጁትን ጥያቄዎች ጎላ አድርገህ ተናገር። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የይሖዋን ድርጅትና የድርጅቱ አካል ለመሆን ያላቸውን መብት ይበልጥ እንዲያደንቁ ለመርዳት የዓመት መጽሐፉን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። የ 2001 የዓመት መጽሐፍ ከሌላችሁ ከጥቅምት 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ላይ “መንፈስ ቅዱስን የግል ረዳቴ አድርጌዋለሁን?” የሚለውን ተወያዩበት።

22 ደቂቃ:- “ሚያዝያ​—⁠‘ጠንክረን የምንሠራበትና የምንጋደልበት’ ወር።” (ከአንቀጽ 14-30) በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። አልፎ አልፎ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የሚቀርብ ንግግር። እያንዳንዱ አስፋፊ በሚያዝያ በተቻለው መጠን በአገልግሎት ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችል ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፕሮግራም ማውጣት ይኖርበታል። በወሩ ውስጥ ለማድረግ የታቀዱትን የመስክ ስምሪት ስብሰባ ፕሮግራሞች በሙሉ ተናገር። ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ ረዳት አቅኚ እንዲሆኑና ከዚህ ስብሰባ በኋላ የማመልከቻ ቅጽ እንዲወስዱ አበረታታ።

መዝሙር 84 (190) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 90 (204)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አሁንም ማመልከቻ ለመስጠት ጊዜው እንዳላለፈ ተናገር። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር​—⁠2001 በሚለው ቡክሌት ላይ ከሚያዝያ 3-8 በወጣው ፕሮግራም መሠረት ሁሉም የመታሰቢያውን በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እንዲያነብቡ አበረታታ። የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት ሳምንት ውስጥ የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መቼ እንደሚደረግ ተናገር። በዚህ ሳምንት እሁድ ሚያዝያ 1 “የሚድኑት እነማን ናቸው?” በሚል ርዕስ ልዩ የሕዝብ ንግግር እንደሚቀርብ አትርሱ። ሚያዝያን በጥሩ ሁኔታ ለመጀመር በዚያ ቀን ሁሉም በአገልግሎት እንዲካፈሉ አሳስብ።

20 ደቂቃ:- “ሁላችንም ይሖዋን እና ልጁን እናክብር።” በሽማግሌ የሚቀርብ ቅዱስ ጽሑፋዊ በሆነ መንገድ የሚቀሰቅስ ንግግር። እያንዳንዱ አስፋፊ በሚያዝያ ሊደረግ በታቀደው ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ላይ በተቻለ መጠን የተሟላ ተሳትፎ እንዲያደርግና ሌሎች ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ ተጨማሪ ጥረት እንዲያደርግ አበረታታ።

15 ደቂቃ:- መጽሔቶቻችንን ለማበርከት የሚያስችል አቀራረብ መዘጋጀት። በሚያዝያ ወር መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን እናበረክታለን። በጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 10 አንቀጽ 3 እና 10 ላይ ያሉትን ሐሳቦች ከልስ። እያንዳንዱን ወቅታዊ መጽሔት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማበርከት (1) አንድ ርዕስ፣ (2) ተስማሚ መነጋገሪያ ነጥብ፣ (3) ፍላጎት ለመቀስቀስ የሚያስችል አንድ ጥያቄ እና (4) ወቅታዊ የሆነ አንድ ጥቅስ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ጎላ አድርገህ ተናገር። ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር ወይም የእውቀት መጽሐፍን ለመጠቀም ጥረት አድርጉ። ሰዎችን በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ቀን ላይ ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል የሚያሳይ ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት ሠርቶ ማሳያ በማቅረብ ክፍሉን ደምድም።

መዝሙር 91 (207) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 2 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 98 (220)

9 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመጋቢት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ከልስ።

18 ደቂቃ:- “ፍቅር እንድንሰብክ ይገፋፋናል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳቦችን ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። በርዕሱ ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች አጉላ። ጠለቅ ብሎ ማስተዋል በተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 2 ገጽ 673 አንቀጽ 1 ላይ የሚገኙ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። ለብዙ ዓመታት ያገለገለ አንድ አስፋፊ ለአምላክ ያለው ፍቅር በስብከቱ ሥራ ላይ እንዲጸና እንዴት እንደረዳው እንዲናገር ጋብዝ። አስፋፊዎች በሙሉ በሚያዝያና ከዚያ በኋላ ባሉት ወራት ምሥክርነት በመስጠቱ ሥራ እንዲካፈሉ አሳስብ።

18 ደቂቃ:- “ሌሎች በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ እርዷቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳቦችን ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። የሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ከአንቀጽ 14-16 የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ወደ ድርጅቱ መምራት የሚቻልባቸውን መንገዶች በተመለከተ ተጨማሪ ሐሳቦች ይዟል። ተማሪው ጥናት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኝ ለማበረታታት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹርንም (ትምህርት 5 አንቀጽ 7) ሆነ እውቀት መጽሐፍን (ምዕራፍ 5 አንቀጽ 22) መጠቀም ይቻላል። ይህን በምሳሌ ለማስረዳት ጥሩ ችሎታ ያለው አንድ አስፋፊ ጥናቱ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ስለመገኘት በቁም ነገር እንዲያስብበት ለማድረግ ከልብ ሲያበረታታው የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ