የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/01 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 4/01 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። እምብዛም ባልተሠራባቸው የአገልግሎት ክልሎች ውስጥ የቆዩ መጽሔቶችን በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙባቸው። ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ካገኘን ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝ ይቻላል። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመርን ግብ በማድረግ እውቀት መጽሐፍን ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ። ሰኔ:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ትኩረት ስጡ። ሐምሌ:- ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊ ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ እና የሙታን መናፍስት ​—⁠ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?

◼ ለ2001 የአውራጃ ስብሰባ ደረት ላይ የሚለጠፈው ካርድ ከሐምሌ ጀምሮ ከጽሑፍ ጋር አብሮ ስለሚላክላችሁ ማዘዝ አያስፈልግም። ጉባኤዎች ተጨማሪ ካርድ ካስፈለጋቸው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) ማዘዝ ይኖርባቸዋል። የካርድ መያዣ ፕላስቲክ ማግኘት የሚፈልጉ ካሉ ማዘዝ ያስፈልጋል።

◼ “የ2001 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ክፍል ቁ. 4 የሚቀርበው ከተጠቀሱት የማመራመር መጽሐፍ ገጽና አንቀጾች ይሆናል። አንቀጾችን በምትቆጥሩበት ጊዜ መቁጠር የሚኖርባችሁ ገባ ብለው የጀመሩትን ብቻ ነው።

◼ ማኅበሩ የሁሉም ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችና ጸሐፊዎች ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር እንዲኖረው ይፈልጋል። በማንኛውም ወቅት ለውጥ የሚኖር ከሆነ የጉባኤው ጸሐፊ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ አድራሻ ለውጥ (S-29) የተባለውን ቅጽ ሞልቶ ወዲያውኑ ወደ ማኅበሩ መላክ ይኖርበታል።

◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ (S-205-AM) እና የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ (S-205b-AM) ቅጾች በበቂ መጠን መኖሩን መከታተል ይኖርባቸዋል። እነዚህን ቅጾች በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) ማዘዝ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያህል የሚበቃ ቅጽ ይኑራችሁ። ሁሉም የዘወትር አቅኚዎች ማመልከቻ ቅጾች ተጠናቅቀው መሞላታቸውን ለማረጋገጥ እንደገና ተመልከቱ። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን በመገመት መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል።

◼ በማንኛውም ጊዜ ወደ ሌላ አገር ለመጓዝ ስታስቡ እዚያ በሚደረጉ የጉባኤ፣ የወረዳ ወይም የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የመገኘት እቅድ ካላችሁ ስብሰባዎቹ የሚደረጉበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ለማወቅ ጥያቄያችሁን የምትልኩት በዚያ አገር ሥራውን በበላይነት ለሚከታተለው ቅርንጫፍ ቢሮ መሆን ይኖርበታል። የቅርንጫፍ ቢሮዎችን አድራሻ መጨረሻ ከወጣው የዓመት መጽሐፍ መጨረሻ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።

◼ አዲስ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦ አረብኛ:- ፈጣሪ፤ ትራክቶች:- T-21፤ እንግሊዝኛ:- የ2001 የዓመት መጽሐፍ።

◼ እንደገና ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ:- ፈጣሪ፣ የቤተሰብ ሕይወት፣ እውቀት፣ ዘላለም መኖር (ትንሹ)፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፣ መጽሐፍ ቅዱስ —⁠የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፣ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች፣ ኮንኮርዳንስ፣ ማውጫ 1930-1985፣ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (በኪስ የሚያዝ ዴሉክስ)፤ ብሮሹሮች:- በደስታ ኑር፣ ሥላሴ፤ የዓመት መጽሐፎች:- 1977፣ 1994፣ 1997-99 ፤ የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች:- 1955፣ 1956፣ 1981-85፣ 1992፤ ንቁ! ጥራዞች:- 1983፣ 1994 ፤ የቴፕ ክሮች:- ዘፍጥረት፣ ዘጸአት፣ ምሳሌ፣ ዳንኤል፣ ሥራ፣ ሮሜ፣ ዕብራውያን፤ የመንግሥቱ ዜማዎች 2 እና 4፣ የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር (በድምፅ የተዘመሩ ​—⁠አንድ ካሴት)፤ የመንግሥቱን ዜማዎች መያዣ ባዶ አልበም፤ የድራማ ክሮች:- ጀሆቫስ ጃጅመንት፤ ሲዲዎች:- የመንግሥቱ ዜማዎች ቁ. 6 እና 7።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ