የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/01 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 5/01 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ካገኘን ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝ ይቻላል። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመርን ግብ በማድረግ እውቀት መጽሐፍን ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ። ሰኔ:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በማስጀመር ላይ አተኩሩ። ሐምሌ እና ነሐሴ:- ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን? ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ እና የሙታን መናፍስት​—⁠ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? እባካችሁ ከላይ የተዘረዘሩትን ብሮሹሮች በበቂ መጠን እዘዙ። መስከረም:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ።

◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው ሰኔ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ ለጉባኤው በማስታወቂያ መነገር አለበት።

◼ የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለው መጽሐፍ ተጠንቶ ካለቀ በኋላ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የሚጠናው ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ ይሆናል። ለቀጣዮቹ ጊዜያት ሁሉ መጠቀም ትችሉ ዘንድ ፕሮግራሙን ፎቶ ኮፒ አድርጋችሁ በመጽሐፋችሁ ውስጥ መያዝ ትችላላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ