የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
ሰኔ 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 57 (136)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሰኔ 25 በሚጀምር ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የይሖዋ ምሥክሮች የናዚን ጥቃት በጽናት ተቋቁመዋል ስለተባለው ቪዲዮ ውይይት ስለሚደረግ ሁሉም ፊልሙን አይተው አስቀድመው እንዲዘጋጁ አበረታታ።
15 ደቂቃ:- “‘መልካም ሥራ መሥራታችሁን’ ቀጥሉ።” በሽማግሌ የሚቀርብ ቅዱስ ጽሑፋዊ ንግግር።
20 ደቂቃ:- “የተማሪዎቻችሁን ልብ ለመንካት ጣሩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳቦች ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አዲሶች ከልባቸው ለይሖዋና ለኢየሱስ ፍቅር እንዲያሳድሩና እምነታቸውን እንዲያዳብሩ እንዴት መርዳት እንደሚቻል ለማሳየት ተግባራዊ ሐሳቦችን ጨምረህ ተናገር። ከሐምሌ 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14 አንቀጽ 18-20 ላይ ቁልፍ ነጥቦችን ተጠቀም።
መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 55 (133)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ውይይት የሚያስቆም ሐሳብ ለሚሰነዝሩ ሰዎች መልስ መስጠት። ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ማመራመር ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 15-16 ላይ “አስተያየት” የሚለውን ከልስ። በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ የሚያጋጥሙ የተለመዱትን የተቃውሞ ሐሳቦች ከገጽ 16-20 ላይ ምረጥ። አድማጮች የትኛው መልስ ውጤታማ ሆኖ እንዳገኙት እንዲሁም ምክንያቱን ጨምረው እንዲናገሩ ጋብዝ።
18 ደቂቃ:- “‘ጎልማሳ’ ክርስቲያን ነህን?” በነሐሴ 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 26-29 ላይ የተመሠረተ ጥያቄና መልስ።
15 ደቂቃ:- ከነሐሴ 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 23-25 ላይ “አለመግባባቶችን የምትፈቱት እንዴት ነው?” በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
መዝሙር 82 (183) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 69 (160)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በሐምሌና በነሐሴ የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። ጉባኤው ካሉት ብሮሹሮች መካከል ስለ ሁለቱ ጠበቅ አድርገህ ተናገር። አገልግሎት ላይ እነዚህን ብሮሹሮች እንዴት ማበርከት እንደሚቻል ለማሳየት ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። አንዳንድ አቀራረቦችን ለማግኘት የ1995 እና የ1996 ሐምሌና ነሐሴ፣ የ1997 ነሐሴ እና መስከረም፣ እንዲሁም የ1998 ነሐሴ የመንግሥት አገልግሎታችን የመጨረሻ ገጾች ተመልከት።
30 ደቂቃ:- “አቋሜን ጠብቄ እጸናለሁ! እጸናለሁ! እጸናለሁ!” በአንቀጽ 2 ላይ የሚገኙ ጥያቄዎችን በመጠቀም በጽናት ተቋቁመዋል በተባለው ቪዲዮ ላይ የሚደረግ ውይይት። በመቀጠል በአንቀጽ 3 እና 4 ላይ ተወያዩ። ኅዳር 22, 1999 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 31 ላይ የሚገኘውን ተሞክሮ በመናገር ክፍሉን ደምድም። በነሐሴ የአዲሱ ዓለም ኅብረተሰብ በእንቅስቃሴ ላይ የተባለውን ቪዲዮ እንከልሳለን።
መዝሙር 11 (29) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 83 (187)
13 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሰኔ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውስ።
15 ደቂቃ:- ወጣቶች ሆይ—የሥራ መስክ በመምረጥ ረገድ አስተዋዮች ሁኑ። ይህ ክፍል ተጨማሪ ትምህርት ከመከታተል ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች ለመከለስ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ከሚቀርቡት ሦስት ክፍሎች መካከል የመጀመሪያው ነው። አንዳንድ ክርስቲያን ወጣቶች ከፍተኛ ትምህርት በመከታተል ሰብዓዊ የሥራ መስክ ላይ የመሠማራት ግብ እየተከታተሉ ሲሆን ይህም በመንፈሳዊነታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ ነው። ይህ ክፍል ሁለት ወላጆች በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ከሚገኝ ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጃቸው ጋር በሚያደርጉት ውይይት ይቀርባል። ወጣቱ ወደፊት ሊደርስበት የሚፈልገውን ግብ አስመልክቶ ከባድ ውሳኔ በሚያደርግበት ጊዜ ላይ ይገኛል። አንዳንዶች ጠቀም ያለ ገንዘብ፣ ክብር ወይም የተደላደለ ኑሮ የሚያስገኝ ግብ ለመከታተል ሊመርጡ ቢችሉም ይህ ቤተሰብ መጽሐፍ ቅዱስን በዚህ ረገድ የሚሰጠውን ሐሳብ ለማወቅ ምርምር ያካሂዳል። (ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ገጽ 174-5፤ መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 15, 1997 ገጽ 21 እና መስከረም 1, 1999 ገጽ 19-21 አንቀጽ 1-3 እና 5-6 ተመልከት።) ወጣቱ የመንግሥቱን ፍላጎቶች ማስቀደም ይችል ዘንድ ቲኦክራሲያዊ ግብ ለመከታተል ጠቃሚ ሆኖ የሚያገኘውን የሕይወት መንገድ መምረጡ ጥበብ እንደሆነ ይስማማል።
17 ደቂቃ:- “በአገልግሎት ክልላችሁ መስማት የተሳናቸውን ሰዎች በመፈለግ ረገድ ንቁ ሁኑ።” ከአንድ ደቂቃ በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳቦችን ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 12 (32) እና የመደምደሚያ ጸሎት።