ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሐምሌ እና ነሐሴ:- ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም መጠቀም ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት እና የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? መስከረም:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች።
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር ርዕስ “እውነተኛ ክርስቲያኖች መለኮታዊውን ትምህርት ውበት የሚያላብሱት እንዴት ነው?” የሚል ይሆናል።