የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/01 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 6/01 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሰኔ:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን የማስጀመር ግብ ይኑራችሁ። ሐምሌ እና ነሐሴ:- ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም መጠቀም ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊ ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት እና የሙታን መናፍስት​—⁠ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? እባካችሁ ከላይ የተዘረዘሩትን ብሮሹሮች በበቂ መጠን እዘዙ። መስከረም:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ።

◼ አንዳንድ ወንድሞች ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው የሚልኩትን ደብዳቤ በቤቴል ባለ ግለሰብ ስም እንደሚልኩ ተስተውሏል። የይሖዋ ድርጅት የሚሠራው በቲኦክራሲያዊ መንገድ በመሆኑ እንዲህ ማድረጉ ተገቢ አይደለም። በተመሳሳይ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ስልክ በምትደውሉበት ጊዜ ሁሉንም ጉዳይ ለመረጣችሁት አንድ ወንድም ለመንገር ከመፈለግ ይልቅ ስልኩን ያነሳው ሰው ጉዳዩ ከሚመለከተው ክፍል ጋር እንዲያገናኛችሁ መጠየቁ የተሻለ ነው።

◼ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የበላይ ተመልካቾች ተማሪዎችን በየዓመቱ እንደገና መመዝገብ እንደማያስፈልጋቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን። አንድ ተማሪ አንዴ ከተመዘገበ በኋላ ጉባኤውን ለቅቆ እስካልሄደ ወይም እንዲሰረዝ የሚያደርገው ሁኔታ እስካልተከሰተ ድረስ እንደተመዘገበ ይቆያል። እንዲሁም ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 10 አንቀጽ 7 ላይ በሚገኘው መመሪያ መሠረት ክፍሉ ከሚቀርብበት ቀን ቢያንስ ሦስት ሳምንት አስቀድሞ የክፍል መስጫው ወረቀት መሰጠት ይኖርበታል። የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክፍል መስጫው ቅጽ (S-89) ለዚሁ ዓላማ መዋል ይኖርበታል።

◼ አዲስ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦ ፈረንሳይኛ:- የ2001 የዓመት መጽሐፍ

◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦ አማርኛ:- የይሖዋ ምሥክሮች በኢትዮጵያ​—⁠ነፃነት አፍቃሪዎች (ይህ ብሮሹር ለሕዝብ እንዲሰራጭ ታስቦ የተዘጋጀ አይደለም።)

◼ እንደገና ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው፦ አረብኛ:- ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ፣ የዳንኤል ትንቢት፣ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች፤ እንግሊዝኛ:- ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ፣ የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ፣ ራእይ ታላቁ መደምደሚያ፣ ትልቁ የመዝሙር መጽሐፍ፣ አዲሲቱ ዓለም ትርጉም በኪስ የሚያዝ ዴሉክስ፤ ሲዲ:- የመንግሥቱ ዜማዎች ቁ. 1, 3, 8፤ የቴፕ ክሮች:- ታላቁ አስተማሪ፣ የመንግሥቱ ዜማዎች ቁ. 1, 3, 5-8፣ ማቴዎስ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ