የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
ሐምሌ 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 2 (4)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
17 ደቂቃ:- የሚያዝያ የአገልግሎት ሪፖርት። በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግርና በቃለ ምልልስ የሚቀርብ። የአገሪቱንና የጉባኤውን የሚያዝያን የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ጎላ ያሉ ገጽታዎች ጥቀስ። የመጋቢት የአገልግሎት እንቅስቃሴ ጎላ ያሉ ገጽታዎችንም መጥቀስ ይቻላል። በዚያ ወር በአገልግሎት ለመካፈል ተጨማሪ ጥረት ካደረጉ የተለያዩ አስፋፊዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። በአገልግሎት ሙሉ ተሳትፎ በማድረጋቸው ስላገኙት ደስታና ወደፊትም በአገልግሎት እንደተጠመዱ ለመቀጠል ምን እርምጃ እንደወሰዱ እንዲናገሩ አድርግ።—ከመጋቢት 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ አንቀጽ 28-30ን ተመልከት።
20 ደቂቃ:- “ይበልጥ እርዳታ ወደሚያስፈልግበት ቦታ ሄደህ ማገልገል ትችላለህ?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈን ከመጋቢት እስከ ግንቦት ስለተደረገው ልዩ ዘመቻ ጥቀስ። አስፋፊዎች በገለልተኛ ክልሎች ወይም እምብዛም ባልተሠራባቸው የአገልግሎት ክልሎች ውስጥ ሲያገለግሉ ያገኟቸው አበረታች ተሞክሮዎች ካሉ ጨምረህ ተናገር።—አገልግሎታችን የተባለውን መጽሐፍ ከገጽ 112-13 ተመልከት።
መዝሙር 18 (42) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 (10)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ:- ወጣቶች ሆይ—የመረጣችሁት የሥራ መስክ የሚያስከትለውን ኪሳራ አስሉ። አንድ አባትና በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ወንድ ወይም ሴት ልጁ በሰብዓዊ ሥራ ረገድ ጥሩ ተሞክሮ ወዳለው ሽማግሌ ቀርበው ያነጋግሩታል። ወጣቱ ከሁለት ሳምንት በፊት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሥራ መስክ በመምረጥ ረገድ በቀረበው ክፍል ላይ በደንብ ካሰላሰለበት በኋላ የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት የመጀመሩን ጉዳይ በቁም ነገር አስቦበታል። ሆኖም ቁሳዊ ፍላጎቱን እንዴት ማሟላት እንደሚችል ትንሽ ግራ ገብቶታል። ሽማግሌው ሚዛናዊ አመለካከት መያዝ አስፈላጊ መሆኑን ጠበቅ አድርጎ ይናገራል። (መስከረም 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 11 አንቀጽ 13) አንድ ሰው የራሱን ወጪ መሸፈን እንዲችል አንድ ዓይነት ስልጠና ማግኘቱ ብልህነት ነው። ብዙዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅና ብዙ ወጪ የማይጠይቅ መሠረታዊ የእጅ ሞያ ተምረዋል። (የካቲት 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14፤ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ገጽ 178) በጥር-መጋቢት 1997 ንቁ! ገጽ 9-11 ላይ ባሉት ነጥቦች አብረው በመወያየት ተስማሚ ሥራ ለማግኘት ወይም ለመፍጠር የሚያስችሉ አንዳንድ ተግባራዊ ሐሳቦችን ይለዋወጣሉ።
20 ደቂቃ:- “ክርስቲያናዊ ገለልተኝነት ምንድን ነው?” ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 269-273 አንቀጽ 1 ድረስ የሚደረግ ውይይት። ከገጽ 270 አንቀጽ 3-ገጽ 271 አንቀጽ 2 ድረስ ያለውን ስትወያዩ በሚያዝያ 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28 አንቀጽ 3-6 ላይ የቀረቡትን ምክንያቶች ጨምረህ ጥቀስ። ከገጽ 272 አንቀጽ 4-ገጽ 273 አንቀጽ 1 ድረስ ያለውን ስትመረምሩ ክርስቲያናዊ ገለልተኝነት ውስጣዊ ስሜታችንና አነጋገራችንን ሳይቀር እንዴት እንደሚቆጣጠር ተናገር። ክርስቲያናዊ ገለልተኝነት ያለውን ጠቃሚ ውጤት ጎላ አድርገህ በመናገር ክፍሉን ደምድም።
መዝሙር 24 (50) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 7 (19)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- ከመጋቢት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29-31 ላይ “ልብን አዘጋጅቶ ይሖዋን መፈለግ” በሚለው ርዕስ ላይ የተመሠረተ ንግግር። መጨረሻ ላይ የክለሳ ነጥቦች አዘጋጅ።
መዝሙር 25 (53) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 (98)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሐምሌ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው።
20 ደቂቃ:- ወጣቶች ሆይ—የትምህርት ዕቅድ ስታወጡ ማስተዋል ተጠቀሙ። አንድ ሽማግሌ ተጨማሪ ትምህርት መከታተልን አስመልክቶ ከወላጆችና በአሥራዎቹ ዕድሜ ከሚገኙ ልጆቻቸው ጋር ይነጋገራል። ሽማግሌው የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ነገሮች መካከል የመጀመሪያውን ቦታ መያዝ የሚገባው ለምን እንደሆነ ጎላ አድርጎ በመግለጽ በመስከረም 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16-17 አንቀጽ 11-13 ላይ የሚደረገውን ውይይት ይመራል። (ታኅሣሥ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-19, አንቀጽ 13-15) ከዚያም የውይይቱ ተሳታፊዎች ተጨማሪ ትምህርት መከታተል ያለውን ጥቅምና ጉዳት በማመዛዘን ረገድ ማስተዋል የመጠቀምንና በአገልግሎት በቅንዓት እየተካፈለ ራሱን ለመርዳት የሚያስችለውን ያህል ብቻ ትምህርት የመከታተልን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገው በመግለጽ በመጋቢት 1999 ንቁ! ገጽ 28-9 ላይ የሚገኘውን ምክር ይከልሳሉ። አንድ ሰው በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ጥሩ ውጤት አግኝቶ ያለፈ ወጣት የግድ ከፍተኛ ትምህርት መከታተል አለበት ብሎ ማሰብ አይኖርበትም። ሁሉም ኢየሱስ የመንግሥቱን ፍላጎት በመጀመሪያ ቦታ ላይ ስለ ማስቀመጥ በሰጠው ማሳሰቢያ መመራት እንደሚገባቸው ይስማማሉ።—ማቴ. 6:33
15 ደቂቃ:- ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ለጉባኤዎች በሙሉ የተላከውን የመጋቢት 20, 2000 ደብዳቤ ይከልሳል።
መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 84 (190)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ለአውራጃ ስብሰባ፣ ለእረፍት ወይም የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ሲጓዙ መደበኛ ባልሆነ ምሥክርነት ያጋጠማቸውን ተሞክሮ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
20 ደቂቃ:- “የአውራጃ ስብሰባ—የደስታ ጊዜ።” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የይሖዋ ሕዝቦች ለምን ትልልቅ ስብሰባዎች ያደርጉ እንደነበረና እነዚህ ስብሰባዎች ዛሬም ቢሆን እኩል ጠቀሜታ ያላቸው ለምን እንደሆነ ተናገር። እንደነዚህ ያሉት አጋጣሚዎች ኃይላችንን የሚያድስ የወዳጅነት መንፈስና ጠቃሚ መንፈሳዊ ምግብ የምናገኝባቸው ናቸው። እያንዳንዱ ክርስቲያን በአውራጃ ስብሰባው ላይ ሦስቱንም ቀን መገኘቱ አስፈላጊ መሆኑን ጠበቅ አድርገህ ተናገር።
17 ደቂቃ:- “ወደኋላ አትበሉ!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደ መጠን ከታኅሣሥ 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25 ላይ ያሉትን ተሞክሮዎች ተናገር።
መዝሙር 30 (63) እና የመደምደሚያ ጸሎት።