የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/01 ገጽ 1
  • ወደኋላ አትበሉ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወደኋላ አትበሉ!
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘መልካም ዜና ማብሰር’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ከቤት ወደ ቤት በምናከናውነው አገልግሎት የሚያጋጥሙንን ተፈታታኝ ሁኔታዎች መቋቋም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • አምላክ በእርግጥ ስለ አንተ ያስባል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • “ከቤት ወደ ቤት”
    ለይሖዋ ዘምሩ
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 7/01 ገጽ 1

ወደኋላ አትበሉ!

1 ከቤት ወደ ቤት ሄደን ለመስበክ ስንዘጋጅ ከሁሉ ይበልጥ ፈታኝ የሚሆንብን ከራሳችን ቤት መውጣት ሊሆን ይችላል። ብቃቱ የለኝም የሚለው ስሜት ሄደን እውነትን ‘ለሁሉም ዓይነት ሰዎች’ ከመንገር ወደኋላ እንድንል ሊያደርገን ይችላል። (1 ጢ⁠ሞ. 2:​3, 4) ሆኖም ምሥራቹን ለመስበክ ማመንታት አይገባንም። ለምን?

2 መልእክቱ የይሖዋ ነው:- ይሖዋ ሐሳቡን በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል ገልጿል። ይህን መልእክት ለሌሎች ስናደርስ የምናስተላልፈው የእርሱን እንጂ የራሳችንን ሐሳብ አይደለም። (ሮሜ 10:​13-15) ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት አንቀበልም ሲሉ ይሖዋን አንቀበልም ማለታቸው ነው። ይሁንና በዚህ ምላሽ ተስፋ አንቆርጥም። ይህ መልእክት የዓለም ሁኔታዎች የሚለወጡበትን ጊዜ በሚናፍቁና ለሚያስፈልጓቸው መንፈሳዊ ነገሮች ንቁ በሆኑ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት እንደሚያገኝ እርግጠኞች ነን።​—⁠ሕዝ. 9:​4፤ ማቴ. 5:​3, 6

3 ሰዎችን የሚስበው ይሖዋ ነው:- ቀደም ሲል እኛን ለማዳመጥ ፈቃደኛ ያልነበረ ሰው የነበረበት ሁኔታ ሲለወጥና ልቡ ሲለሳለስ መልእክቱን ይቀበል ይሆናል። በዚህ ጊዜ ይሖዋ ግለሰቡን ‘ወደ እርሱ በመሳብ’ ለእርሱ ያለውን በጎ ፈቃድ ያሳያል። (ዮሐ. 6:​44, 65) እንዲህ ባለው አጋጣሚ ይሖዋ እንዲጠቀምብን ዝግጁ ሆነን ለመገኘትና ለመላእክታዊ አመራር ታዛዥ መሆን እንፈልጋለን።​—⁠ራእይ 14:​6

4 አምላክ መንፈሱን ይሰጠናል:- መንፈስ ቅዱስ ‘ከይሖዋ ባገኙት ሥልጣን በድፍረት እንድንናገር’ ያስችለናል። (ሥራ 14:​1-3 NW ) አገልግሎታችንን ለማከናወን የዚህ ብርቱ ኃይል ድጋፍ እንዳለን በማስታወስ እውነትን ለጎረቤቶቻችን፣ ለሥራ ባልደረቦቻችን፣ በክፍል ውስጥ አብረውን ለሚማሩ፣ ለዘመዶቻችን ወይም የተማረ ሀብታም ሳንል ለሰዎች ከመናገር ወደኋላ አንልም።

5 ኢየሱስ እንዴት እንደምንሰብክ አስተምሮናል:- ኢየሱስ ስሜት ቀስቃሽ ጥያቄዎችን፣ ቀጥተኛ ምሳሌዎችንና ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያቶችን ተጠቅሟል። እውነትን ከልብ በመነጨ ስሜት፣ ቀላልና ማራኪ በሆነ መንገድ አስተምሯል። ዛሬም ቢሆን ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለም። (1 ቆ⁠ሮ. 4:​17) የምንሰብክበት መቼት ሊለያይ ቢችልም ብርቱ ኃይል ያለው የመንግሥቱ መልእክት አንድ ነው።

6 ሰዎችን ልዩና ለሕይወታቸው ወሳኝ በሆነ መንገድ ለመርዳት ይሖዋ የሚጠቀምብን ሰዎች የመሆን መብት አግኝተናል። እንግዲያው ፈጽሞ ወደኋላ አንበል! ደፋሮች በመሆን ይሖዋ ምሥራቹን ለሌሎች መንገር እንችል ዘንድ ‘የቃሉን ደጅ እንዲከፍትልን’ እንፍቀድ።​—⁠ቆላ. 4:​2-4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ