ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴ:- ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም መጠቀም ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት እና የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? መስከረም:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ኅዳር:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን መጽሐፍ ወይም ሌላ የቆየ መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል።
◼ መስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ እባካችሁ ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም በተባለው ቅጽ የእንግሊዝኛ ክፍል ላይ የሚከተለውን ማስተካከያ አድርጉ:- በተራ ቁጥር (2) ሥር “+” በሚለው ምልክት ፋንታ “predonate” የሚለውን ቃል አስገቡ።
◼ ከዚህ ዓመት ጀምሮ የዘወትር አቅኚዎች የአቅኚነት አገልግሎት ትምህርት ቤት በሚካፈሉበት ዓመት እስከ መስከረም 1 ድረስ ዕድሜያቸው ቢያንስ 16 ካልሞላ በትምህርት ቤቱ አይካፈሉም። ሆኖም በዚያው ዓመት በትምህርት ቤቱ የሚካፈል የዘወትር አቅኚ የሆነ ወላጅ ካላቸው በትምህርት ቤቱ መካፈል ይችላሉ።
◼ ጉባኤዎች በመስከረም ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2002 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል።
◼ በ2002 የአገልግሎት ዓመት የምትጠቀሙባቸውን በቂ መጠን ያላቸው ቅጾች ለእያንዳንዱ ጉባኤ በመላክ ላይ ናቸው። እባካችሁን እነዚህን ቅጾች በአግባቡ ተጠቀሙባቸው። ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ መዋል ይኖርባቸዋል።
◼ በእጅ ያሉት ጽሑፎችና መጽሔቶች ዓመታዊ ቆጠራ በተቻለ መጠን ነሐሴ 31, 2001 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይርቅ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ቁጥር የጽሑፍ አስተባባሪው በየወሩ ከሚያካሂደው ቆጠራ ጋር ተመሳሳይ ነው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18-AM) ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶችን ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቡድኑ ከታቀፈው ከእያንዳንዱ ጉባኤ የመጽሔት አገልጋይ ማግኘት ይቻላል። እያንዳንዱ አስተባባሪ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18-AM) ይደርሱታል። እባካችሁ ዋናውን ቅጂ ከመስከረም 6 በፊት ለማኅበሩ ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሙያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። የአስተባባሪው ጉባኤ ጸሐፊ ቆጠራውን በበላይነት መከታተል ይኖርበታል። የአስተባባሪው ጉባኤ ጸሐፊና ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ቅጹ ላይ ይፈርማሉ።