ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠይቅ ስናደርግ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ካገኘን ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝ ይቻላል። ኅዳር:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። ታኅሣሥ:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ።
◼ እባካችሁ በቅርቡ በሚደረገው “የአምላክ ቃል አስተማሪዎች” በተባለው የ2001 የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም ላይ የተደረገውን የሚከተለውን ማስተካከያ ልብ በሉ:- ጥቅምት 12-14:- አዲስ አበባ፤ ይህ ስብሰባ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን የእንግሊዝኛ እና የምልክት ቋንቋ ፕሮግራሞችንም ይጨምራል፤ ጥቅምት 19–21:- ድሬዳዋ፤ በመንግሥት አዳራሽ፤ ጥቅምት 27 እና 28 (ለሁለት ቀን):- መቀሌ፤ ኅዳር 3 እና 4 (ለሁለት ቀን):- ደሴ፣ ነቀምት፤ ኅዳር 10 እና 11 (ለሁለት ቀን):- ባሕር ዳር። ቀጥሎ ባሉት ፕሮግራሞች ላይ ምንም ለውጥ አልተደረገም:- ጥቅምት 26-28:- ጅማ፤ ኅዳር 9-11:- ሻሸመኔ። በሁለት ቀን የሚቀርቡት የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራሞች እንዲያጥሩ ተደርገዋል። በአዲስ አበባ ለማድረግ የታቀደው አንድ ስብሰባ ብቻ ነው።
◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ውስጥ ያለው አባሪ “የ2002 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ሲሆን ዓመቱን ሙሉ ልንጠቀምበት እንድንችል በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።
◼ የጉባኤያችሁ የስብሰባ ሰዓት ከጥር አንድ ጀምሮ የሚቀየር ከሆነ ጸሐፊው የጉባኤ ስብሰባዎች መረጃ እና የመጋበዣ ወረቀት ማዘዣ ቅጽ (S-5) በመላክ ለውጡን ለማኅበሩ ማሳወቅ ይገባዋል። አስፈላጊ ከሆነ በዚያው ቅጽ ተጠቅሞ አዲስ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት ማዘዝ ይቻላል። መጋበዣ ወረቀት ማዘዝ የሚገባችሁ እንዲደርሳችሁ ከምትፈልጉበት ጊዜ ቢያንስ ከስምንት ሳምንት በፊት መሆን አለበት።
◼ ጉባኤዎች ከጥቅምት ወር የጽሑፍ ትእዛዛቸው ጋር ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2002ን ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። ቡክሌቱን በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛና በትግርኛ ቋንቋዎች ማግኘት ይቻላል። ቡክሌቱ ደርሶን እስክንልክላችሁ ድረስ በጉባኤያችሁ የጽሑፍ መላኪያ ዝርዝር ላይ “በቅርቡ የሚደርስ” ተብሎ ይወጣል። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር በልዩ ትእዛዝ የሚገኝ ጽሑፍ ነው።
◼ እንደገና ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦ አረብኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፤ እንግሊዝኛ:- የቴፕ ክሮች:- ዮሐንስ፤ የቪዲዮ ክሮች:- መጽሐፍ ቅዱስ— ለዘመናችን የሚሠራ መጽሐፍ፣ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ኖኅ፣ ፐርፕል ትሪያንግልስ፣ በመለኮታዊ ትምህርት አንድ መሆን። ፈረንሳይኛ:- የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (bi12)።