የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/01 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥቅምት 8 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 15 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 22 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 29 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 5 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 10/01 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ጥቅምት 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 2 (4)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 1 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ተጠቅመህ መጽሔት ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።

35 ደቂቃ:- “ራስህን በፈቃደኝነት ልታቀርብ ትችላለህ?” ከአንቀጽ 4-6 ያለው በቀጥታ ሊነበብ ይችላል፤ የቀረውን ግን በጥያቄና መልስ ተወያዩበት።

መዝሙር 64 (151) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 48 (113)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ:- “ስለ ራስህ ያለህ አመለካከት ምን ይመስላል?” በጥር 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 20-22 ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

20 ደቂቃ:- መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹና የመጽሔት አገልጋዩ የጉባኤውን የመጽሔት ስርጭት በተመለከተ ይወያያሉ። አስፋፊዎች መጽሔታችንን በጥሩ ሁኔታ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉት እንዴት ነው? ሁለቱ ወንድሞች ጥቅምት 4, 1999 በሚጀምር ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ “ለመጽሔቶች ትኩረት ስጡ!” በሚለው ርዕስ ሥር የቀረቡትን ሰባት ነጥቦች ይወያዩባቸዋል። በየካቲት 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-9 ላይ ያለውን ተሞክሮ ይከልሱና እዚያ ላይ የተሰጡት ሐሳቦች በጉባኤው ክልል ውስጥ እንዴት ሊሠሩ እንደሚችሉ ይጠቁማሉ። ሁሉም በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በየወሩ የሚወጡትን የናሙና አቀራረቦች እንዲጠቀሙ ማበረታቻ ይሰጣል።

መዝሙር 67 (156) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 69 (160)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 1 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም መጽሔት ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።

10 ደቂቃ:- ምን ብለህ ትመልሳለህ? በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 205-6 ላይ “የይሖዋ ምሥክሮች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጧቸውን ማብራሪያዎች የሚያገኙት እንዴት ነው?” ለሚለው ጥያቄ የተሰጠውን ግልጽ መልስ በአጭሩ ጥቀስ። በተመላልሶ መጠይቅ ላይ ለዚህ ጥያቄ እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚቻልና ከዚያም አድማጩ በጉባኤ ስብሰባ እንዲገኝ ሞቅ ያለ ግብዣ ሲደረግለት የሚያሳይ ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

25 ደቂቃ:- በነሐሴ 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 20-23 ላይ የሚገኘው “ልጆች ያልወለዱት ለምንድን ነው?” የሚለው ርዕስ ዋና ዋና ነጥብ በክለሳ ይቀርባል። በተጨማሪም በዚህ ወር የአውራጃ ስብሰባ የሚያደርጉ ጉባኤዎች ይህን ጊዜ በስብሰባው ምክንያት ያመለጣቸውን በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ይቀርብ የነበረ ትምህርት ለመሸፈን ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 72 (164)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥቅምት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውስ። በኅዳር የሚበረከቱት ጽሑፎች አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር እና የእውቀት መጽሐፍ ናቸው። ይህን አጭር ሠርቶ ማሳያ አቅርብ:- “አስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ ባለበት በዛሬው ጊዜ ብዙዎች ኑሮው በጣም ከብዶባቸዋል። የሰው ልጅ ለዚህ ችግር አድልዎ በሌለበት ሁኔታ መፍትሔ የሚያገኝለት ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት] በዚህ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ተስፋ አበረታች ሆኖ አግኝቼዋለሁ።” መዝሙር 72:​12-14ን አንብብ። ከዚያም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ከተባለው ብሮሹር ወይም ከእውቀት መጽሐፍ ከዚህ ጋር ተስማሚ የሆነ አንድ ሐሳብ ካካፈልከው በኋላ አስተዋጽዎ ማድረግ ስለሚቻልበት ዝግጅት በመግለጽ ጽሑፉን እንዲወስድ ጋብዘው።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

18 ደቂቃ:- “በመንፈሳዊ ምን ያህል በሚገባ ትመገባለህ?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጥሩ የመንፈሳዊ አመጋገብ ልማድ ለማዳበር ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንና እንዴት እንደሆነ ከሚያዝያ 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-​31 ላይ አድማጮች ተጨማሪ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

መዝሙር 81 (181) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 84 (190)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

18 ደቂቃ:- ለስብሰባዎች በቤተሰብ መዘጋጀት። ሁሉም በስብሰባዎች ላይ ጥሩ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል አንድ አባት ከቤተሰቡ ጋር ይወያያል። በሐምሌ 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19-​20 አንቀጽ 9 ላይ ያሉትን መመሪያዎች በመጠቀም በሚቀጥለው ሳምንት በመጠበቂያ ግንብ ጥናት ላይ የሚሰጡትን ሐሳብ ይዘጋጃሉ። (1) እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሐሳብ የሚሰጥባቸው አንድ ወይም ሁለት ጥያቄዎች ይመርጣል። (2) አንቀጹ ውስጥ ያለውን ሐሳብ በሚገባ ከመረመሩ በኋላ መልሶቹን በራሳቸው አባባል ይዘጋጃሉ። (3) ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቁልፍ የሆኑትን መርጠው እንዴት ከርዕሱ ጋር እንደሚያያዙ ከተወያዩ በኋላ ከትምህርቱ ጋር እንዴት አቀናብረው ሊመልሱት እንደሚችሉ ይወስናሉ። ሁሉም በስብሰባው ላይ ተሳትፎ ለማድረግ ጉጉት ያሳያሉ።

17 ደቂቃ:- “ዓላማው ምንድን ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በስብሰባዎች ላይ መገኘት ያለውን ጥቅም እንዲገነዘቡ መርዳት አስፈላጊ መሆኑን ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። እውቀት መጽሐፍ ምዕራፍ 17 አንቀጽ 6-8ን ተጠቅመህ እንዴት ይህን ማድረግ እንደሚቻል የሚያሳይ ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

መዝሙር 89 (201) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ