የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/01 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ኅዳር 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 26 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 11/01 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ኅዳር 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 80 (180)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የጉባኤያችሁን የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ከልስ።

15 ደቂቃ:- “ብርታት   ለማግኘት   በይሖዋ ታመኑ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከጥቅምት 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 18-​19 አንቀጽ 6-8 ላይ አጠር ያለ ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።

22 ደቂቃ:- “ይሖዋ ላሳየን ፍቅር አመስጋኝ መሆን የሚያስገኛቸው በረከቶች​—⁠ክፍል 1።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከአንቀጽ 3-6 ያለውን ስትወያዩ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት፣ በመንገድ ላይ ምሥክርነት እንዲሁም በተመላልሶ መጠይቅ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ያገኙትን የሚያበረታቱ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጉባኤውን ጋብዝ።

መዝሙር 58 (138) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 76 (172)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በታኅሣሥ ውስጥ በሚቀርበው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም በመለኮታዊ ትምህርት አንድ መሆን የተባለውን የቪዲዮ ፊልም አይተው እንዲመጡ አበረታታ። (ጥያቄዎቹ በታኅሣሥ 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ይወጣሉ።)

15 ደቂቃ:- “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም” የሚለውን ተወያዩበት።

22 ደቂቃ:- “የማስተዋል ችሎታችሁን አዳብሩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንድ ሽማግሌ ባለፈው ዓመት የተደረገውን የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም ሕያው በሆነ የክለሳ ውይይት ያቀርበዋል።

መዝሙር 87 (195) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 79 (177)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የኅዳር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። “መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?” በሚለው ዓምድ ሥር ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ከዚያም በታኅሣሥ ወር ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት የምንጠቀምበትን አቀራረብ እንዴት ማግኘት እንደምንችል ግለጽ። በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ ውስጥ “አቀራረቦች” በሚለው ርዕስና ገባ ብሎ በሚገኘው “በጽሑፉ ዓይነት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ተመልከት። ከዚያ ያገኘኸውን አንድ ወይም ሁለት አቀራረብ ጥቀስ። “በማውጫው ውስጥ ይገኛል” የሚለውን በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን ርዕስ ተመልከት።

15 ደቂቃ:- “ጊዜ ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በጥቅምት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 20-1 አንቀጽ 9-10 ላይ ካለው “አንዳንዶች ለጥናት የሚሆን ጊዜ የሚያገኙት እንዴት ነው?” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ዋና ዋና ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። አድማጮች አላስፈላጊ የሆኑ ሥራዎችን በመተው ይበልጥ ጠቃሚ ለሆኑ ነገሮች ጊዜ እንዲያገኙ የረዷቸውን ተግባራዊ መንገዶች እንዲናገሩ ጋብዝ። ለግልና ለቤተሰብ ጥናት፣ ለጉባኤ ስብሰባዎች፣ ለመስክ አገልግሎት እንዲሁም ለዕለታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጊዜ መመደብ ያለውን አስፈላጊነት ጎላ አድርገህ ግለጽ።

15 ደቂቃ:- ልጆች ይሖዋን እያወደሱ ነው። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አብዛኞቹ ጉባኤዎች በስብከቱ ሥራ ላይ የሚካፈሉ ብዙ ልጆች አሏቸው። አብዛኛውን ጊዜ የሚመሠክሩት ለትላልቅ ሰዎች ቢሆንም በስብከቱ ሥራ መሳተፋቸው የተገባ ነው። (መዝ. 148:12, 13፤ ማቴ. 21:15, 16) ወላጆችም ሆኑ ሌሎች አስፋፊዎች ትኩረት ሰጥተውት ስልጠናና ማበረታቻ የሚሰጧቸው ከሆነ ልጆች በመስክ አገልግሎት በመካፈል ብዙ ደስታ ያገኛሉ። አድማጮች ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎትና ተመላልሶ መጠይቅ በማድረጉ ሥራ ልጆችን ማሳተፍ ስለሚቻልባቸው መንገዶች ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። ልጆቻቸው መጽሔት እንዲያበረክቱ፣ በአቀራረባቸው መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጠቀሙና ከቤት ወደ ቤት በሚያደርጉት አገልግሎት ሰዎችን በድፍረት እንዲያነጋግሩ ለማሰልጠን ወላጆች ምን እንዳደረጉ እንዲናገሩ ጠይቅ። ልጆችን ማመስገን የሚያስገኘውን ጥቅም ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። አስፋፊ ለሆኑ አንድ ወይም ሁለት ልጆች ቃለ ምልልስ በማድረግ ከስብከቱ ሥራ ውስጥ ደስ የሚላቸው የትኛው እንደሆነና አስደሳች ሆኖ ያገኙት ለምን እንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ።

መዝሙር 24 (50) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 89 (201)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።

17 ደቂቃ:- የማመራመር መጽሐፍ አንዳንድ ገጽታዎች። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ገጽታዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ለሌሎች ለማስረዳት እንዴት ጠቃሚ እንደሆኑ የሚያሳዩትን የሚከተሉትን ምሳሌዎች ተመልከት። “መንግሥት” (ገጽ 226-7) ወይም “መንፈስ” (ገጽ 378-​379) እንደሚሉት ላሉት ቃላት የተሰጡ ፍቺዎች፤ የአምላክ ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትና እንዴት እንደተሠራበት ከሚያሳዩ (ገጽ 191-3) ወይም ስለ ሲኦል ሐቁን ከሚናገሩ (ገጽ 169-​70) የተለያዩ ትርጉሞች የተወሰዱ የማመሳከሪያ ጥቅሶች፤ ከሌሎች ሃይማኖቶች የምንለይባቸውን እምነቶች የሚያብራሩ (ገጽ 199-​201) ወይም አንድ ሰው ትክክለኛውን ሃይማኖት እንዴት ማወቅ እንደሚችል የሚያሳዩ (ገጽ 327-​29) ዝርዝሮች፤ የገና በዓል አመጣጥን (ገጽ 176-8) ወይም የጥንት ክርስቲያኖች ያሳዩትን ገለልተኝነት (ገጽ 273-5) የሚያሳዩ ታሪኮች፤ ፍጥረትን የሚደግፉ (ገጽ 85-6) ወይም ማሪዋና እና ትምባሆ መጠቀም ያለውን ጉዳት የሚያሳዩ (ገጽ 108-​11) ሳይንሳዊ መረጃዎች። አስፋፊዎች ይህንን ጥሩ የማስተማሪያ መሣሪያ ምንጊዜም በመስክ አገልግሎት ላይ አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ እንዲጠቀሙበት አበረታታ።

20 ደቂቃ:- “ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አዲስ መሣሪያ አግኝተናል!” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ጉባኤው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ለማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለው ትራክት ደርሶት ከሆነ አስተናጋጆች በስብሰባው ላይ ለተገኙት ሁሉ አንድ ቅጂ እንዲያድሉ አድርግ። “መጽሔቶቻችንን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?” በሚለው ዓምድ ሥር ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች ጨምረህ አቅርብ። ሠርቶ ማሳያዎቹን የሚያቀርቡት አስፋፊዎች አስተዋጽኦ ማድረግ ስለሚቻልበት ዝግጅት በመጥቀስ አንደኛው መጠበቂያ ግንብ ሌላኛው ደግሞ ንቁ! ያበረክታሉ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች አስፋፊዎቹ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ለማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት በመስጠት የሚደመድሙ ሲሆን በአንደኛው ሠርቶ ማሳያ ላይ መጽሔት ለወሰደ በሌላኛው ሠርቶ ማሳያ ላይ ደግሞ መጽሔት ለመውሰድ ፈቃደኛ ላልሆነ ሰው ትራክቱን ያበረክታሉ። ሁሉም አዲሱን ትራክት በአገልግሎት ለሚያገኙት ሰው ሁሉ እንዲሰጡ አበረታታ።

መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ