‘የተወሰነ መጠን አስቀሩ’
በጥንቱ የክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ መሸፈን የነበረባቸው የተወሰኑ ወጪዎች ነበሩ። እነዚህን ወጪዎች ለመሸፈን እያንዳንዱ ሰው እንደ ገቢው ‘የተወሰነ መጠን እንዲያስቀር’ ማበረታቻ ተሰጥቶት ነበር። (1 ቆሮ. 16:1-3) ሁሉም ባሳዩት ልግስና ምክንያት ‘ምስጋና ለእግዚአብሔር በማብዛታቸው’ ተደስተዋል።—2 ቆሮ. 9:11, 12
በዛሬው ጊዜ ዓለም አቀፉ የይሖዋ ሕዝቦች ሥራ መስፋፋቱን ስለቀጠለ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ የገንዘብ ድጋፍ አስፈልጓል። በዚህ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ ማበርከት እንችል ዘንድ እኛም በቋሚነት ‘የተወሰነ መጠን ማስቀረታችን’ ተገቢ ነው። (2 ቆሮ. 8:3, 4) ቁሳዊ እርዳታ ማድረግ የሚቻልባቸው ብዙ የተለያዩ መንገዶች አሉ። (የኅዳር 1, 2001 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-9 ተመልከት) ይህን አጋጣሚ እውነተኛ ደስታ የሚያስገኝ መብት አድርገን እንመለከተዋለን።—ሥራ 20:35