የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ጥር 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 1 (3)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
25 ደቂቃ:- በተደረጉልን የደግነት ዝግጅቶች መጠቀም። የሕክምና መመሪያ ካርዶችንና የሰኔ 15, 2000 እና ጥቅምት 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጡ የአንባብያን ጥያቄዎችን የመሳሰሉ ከሕክምና ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን ስንወስን እንዲረዱን ታስበው የተዘጋጁ ዝግጅቶችን አስመልክቶ ጥሩ ችሎታ ባለው ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው ለወንድሞች የሚታደሉት የሚከተሉት ሰነዶች በበቂ መጠን ሊኖሩት ይገባል:- በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርግ ሰነድ፣ የመታወቂያ ካርድ፣ ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም፣ የሕክምና ሰነዶች አጠቃቀም መመሪያ። የተጠመቁ አስፋፊዎች የዕለቱ ስብሰባ ካለቀ በኋላ እነዚህን ሰነዶች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የሚሞላው ግን ዛሬ አይደለም። የሰነዱ ባለቤትም ሆነ ምሥክሮቹ በሰነዶቹ ላይ የሚፈርሙትና ቀን የሚሞሉት በቀጣዩ ሳምንት የሚደረገው የመጽሐፍ ጥናት ስብሰባ ካለቀ በኋላ ሲሆን አስፈላጊ ሲሆን የመጽሐፍ ጥናቱ መሪ ይረዳቸዋል። ምሥክር ሆነው የሚፈርሙት ሰዎች ግለሰቡ ሰነዱ ላይ ሲፈርም ማየት ይኖርባቸዋል። ሰነዶቹ ከመሞላታቸው በፊት ማኅበሩ ያዘጋጀው የሕክምና ሰነዶች አጠቃቀም መመሪያ በጥንቃቄ መነበብ ይኖርበታል። ይህንን ቅጽ ከዚህ በፊት ሞልተህ ከነበረ ቅጹን የሞላኸው ከ2001 በፊት እስካልሆነ ወይም ቅጹ የያዘው ሐሳብ አሁን ያለህን አመለካከት የማይገልጽ እስካልሆነ ድረስ ሌላ ቅጽ መሙላት አያስፈልግህም። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ከሁኔታቸውና ከአቋማቸው ጋር በሚስማማ መንገድ ሐሳቡን ከእነዚህ ሰነዶች ላይ በመውሰድ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው የሕክምና መመሪያ ማዘጋጀት ይችላሉ።
10 ደቂቃ:- “መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?” መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ። በመጽሔት ቀን ሁሉም አስፋፊዎች የበኩላቸውን ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ።
መዝሙር 58 (138) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 84 (190)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ‘የተወሰነ መጠን አስቀሩ’ የሚለውን ሣጥን ተወያዩበት።
13 ደቂቃ:- ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ እየመረመርክ ነው? አንድ ቤተሰብ በውይይት ያቀርበዋል። በዕለቱ ጥቅስ ላይ በመወያየት የሚያገኙትን ጥቅም ለማሳደግ በታኅሣሥ 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18 ከአንቀጽ 13-14 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ይመለከታሉ። በቅርቡ የተወያዩባቸውን የሁለት ወይም የሦስት ቀን ጥቅሶች በአጭሩ ይከልሱና በጥቅሶቹ ላይ የቀረበው ሐሳብ ምን ያህል እንደጠቀማቸው ይናገራሉ። በዕለት ጥቅሱ ላይ የሚደረገው ውይይት ቤተሰቡን ምንጊዜም ንቁ እንዲሆን ለማድረግ ታስቦ ከተዘጋጀው ቋሚ የቤተሰብ ጥናት ፕሮግራም አንዱ ክፍል መሆን እንዳለበት ጎላ አድርገህ ግለጽ።
22 ደቂቃ:- “መንግሥቱን ማስቀደማችሁን ቀጥሉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። በመስከረም 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 19-21 በቀረቡት ዋና ዋና ሐሳቦች ላይ ጥቂት ጥያቄዎች ጠይቅ።
መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6 (13)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በገጽ 8 ላይ ያሉትን አቀራረቦች ተጠቅመህ መጽሔት ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ጉባኤው ያሉትን መጽሐፎች በመጥቀስ በየካቲት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር።
20 ደቂቃ:- “ወላጆች—ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አሰልጥኗቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። በሚያዝያ 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ። ልጆቻቸውን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ በመንፈሳዊ በማሰልጠናቸው ያገኟቸውን መልካም ውጤቶች እንዲናገሩ ወላጆችን ጋብዝ።
15 ደቂቃ:- በኅዳር 1, 1999 የመጠበቂያ ግንብ እትም በገጽ 20-23 ላይ በሚገኘው “የተትረፈረፈ ልግስና” በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ለጉባኤው የሚያስፈልጉት ነጥቦች ብቻ ይሸፈናሉ። የመንግሥት አዳራሽ ግንባታዎችን፣ የልዩ አቅኚነት ሥራን፣ ትላልቅ ስብሰባዎችን ለማድረግ የሚወጡ የኪራይ ወጪዎችንና ጽሑፎችን የማተሚያ ወጪዎችን በገንዘብ መደገፍ እንደሚያስፈልግ ተናገር። አስተዋጽኦ የማድረግ መብት ለሁሉም ክፍት መሆኑን ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 91 (207) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 94 (212)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “ለሠርግ ወራት የሚሆኑ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ሁሉም እንዲያዩት አበረታታቸው።
17 ደቂቃ:- “እንዴት ይሰማሉ?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። ጥቅሶቹ እንዴት ተግባራዊ ሊሆኑ እንደሚችሉ አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። በነሐሴ 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20 ከ17-18 ላሉት አንቀጾች የሚሆኑ ጥያቄዎችን ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ:- “ለመስክ አገልግሎት የሚሆኑ አቀራረቦች” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ይህ አባሪ ከዚህ ቀደም በወጡ የመንግሥት አገልግሎታችን እትሞች ላይ የወጡትንና ሌሎች አዲስ አቀራረቦችንም ጨምሮ ይዟል። የተዘጋጁት ክፍት መስመሮች ወደፊት የሚወጡትንና ለአካባቢው ውጤታማ ሆነው የተገኙ መግቢያዎችን ለመጻፍ ልንጠቀምባቸው እንችላለን። አድማጮች ይበልጥ የሚወዱት የትኛውን አቀራረብ እንደሆነና ለምን እንደሚወዱት እንዲናገሩ ጋብዝ። በየካቲት የሚበረከተውን ጽሑፍ ለማበርከት የሚያስችሉ አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ሁሉም አስፋፊዎች ይህን አባሪ በጥንቃቄ እንዲያስቀምጡትና ለአገልግሎት ሲዘጋጁ እንዲጠቀሙበት አበረታታ።
መዝሙር 67 (156) እና የመደምደሚያ ጸሎት።