የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
የካቲት 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 3 (6)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የካቲት 25 የሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም ከዘፍጥረት 6:1 እስከ 9:19 ድረስ በማንበብና ኖህ—አካሄዱን ከአምላክ ጋር አደረገ የተባለውን የቪዲዮ ፊልም በማየት እንዲዘጋጁ አበረታታ።
20 ደቂቃ:- “የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ ስበኩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። (ከአንቀጽ 1-13) በሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። በመጋቢትና በቀጣዮቹ ወራት ልናከናውን ያቀድነውን አስመልክቶ የሚደረግ ቀስቃሽ ውይይት። ሁሉም በመጋቢት ወር በተቻለ መጠን በአገልግሎቱ ይበልጥ ለመካፈል ከዚህ አባሪ ጋር የቀረበውን የቀን መቁጠሪያ በመጠቀም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፕሮግራም ማውጣት አለባቸው። ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ በመጋቢት ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ አበረታታ። አንቀጽ 7 እና 8ን ስትወያዩ ባለፈው ዓመት በተከበረው የመታሰቢያ በዓል ወቅት ረዳት አቅኚ ሆነው ያገለገሉ ያገኟቸውን በረከቶች እንዲናገሩ ጠይቅ። ከስብሰባው በኋላ የረዳት አቅኚነት ማመልከቻ ቅጽ ማግኘት እንደሚቻል ተናገር።
13 ደቂቃ:- “መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?” አስፋፊዎች በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚወጣው ይህ ዓምድ መጽሔቶችን በዚህ አስጨናቂ ዘመን ውስጥ ከሚከሰቱት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ጋር አያይዞ ለማቅረብ በተሻለ እንዲዘጋጁ እንዴት እንደረዳቸው ጠይቅ። ለሰዎች ማጽናኛ በመስጠትና ለሚያሳስቧቸው ጥያቄዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ መልስ እንዲያገኙ በመርዳት አንዳንዶች ምን ተሞክሮ አግኝተዋል? አስተዋጽኦ ማድረግ ስለሚቻልበት ዝግጅት በመጥቀስ በቅርብ ጊዜ የወጣ አንድ መጠበቂያ ግንብ እንዲሁም አንድ ንቁ! መጽሔት ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 56 (135) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 71 (163)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
12 ደቂቃ:- “በምድር ላይ ከሚገኙ ሰዎች ሁሉ ይበልጥ ደስተኛ የሆኑት ሕዝቦች።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በጥቅምት 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 6 ላይ የሚገኘውን “ደስታ ለማግኘት ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች” የሚለውን ሣጥን በአጭሩ አክለህ አቅርብ።
25 ደቂቃ:- “የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ ስበኩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። (ከአንቀጽ 14-23) በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። በመጋቢት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ለማድረግ ጉባኤው ያደረጋቸውን ልዩ ዝግጅቶች ግለጽ። ልዩ የአገልግሎት ክልል የመሸፈን ዘመቻ በዚህ ወር እንደሚጀምር ጥቀስ። በወሩ ውስጥ ለሚደረጉት የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች የወጣውን አጠቃላይ ፕሮግራም በዝርዝር ተናገር። አገልግሎት ያቆሙትን በድጋሚ አገልግሎት እንዲጀምሩ ስለ ማድረግ እንዲሁም ልጆችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ያልተጠመቁ አስፋፊዎች እንዲሆኑ ስለ መርዳት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። በመጋቢት ረዳት አቅኚ ለመሆን ያመለከቱትን አስፋፊዎች ስም አንብብ፤ እንዲሁም ሌሎችም ረዳት አቅኚ ለመሆን በጸሎት እንዲያስቡበት አበረታታቸው።
መዝሙር 60 (143) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 77 (174)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። መጽሔት ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ። አንዱ ሠርቶ ማሳያ በአንድ ወጣት እንዲቀርብ አድርግ። አስፋፊዎች የየካቲት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ:- “ምሥክርነት ለመስጠት የሚረዱት የቪዲዮ ፊልሞች በሰዎች ላይ እያሳደሩ ያሉት በጎ ተጽዕኖ።” ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። እስከ አሁን በአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራማችን ላይ ከቪዲዮ ፊልሞቻችን መካከል ስምንቱን ከልሰናል። በርዕሱ ውስጥ የቀረቡትን ምሳሌዎች በአጭሩ ከተወያያችሁ በኋላ አስፋፊዎች ቪዲዮዎቹን ለሌሎች በማሳየት ያገኙትን ውጤት እንዲናገሩ ጋብዝ።
15 ደቂቃ:- “ኖኅ—አካሄዱን ከአምላክ ጋር አደረገ ከተሰኘው የቪዲዮ ፊልም ሁሉም ሰው ሊማር ይችላል።” በገጽ 7 ላይ በሚገኘው ሣጥን ውስጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች ብቻ በመጠቀም በቀጥታ ከአድማጮች ጋር ስለ ኖኅ ቪዲዮ ውይይት ጀምር። በሚያዝያ የወጣቶች ጥያቄ—እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ እንከልሳለን።
መዝሙር 96 (215) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 91 (207)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
12 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
12 ደቂቃ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር በእውቀት መጽሐፍ ተጠቀሙ። በመጋቢት ወር የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ማድረግ እንፈልጋለን። በነሐሴ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 አንቀጽ 8 ላይ ያለውን ተሞክሮ በአጭሩ ተናገር። እውቀት መጽሐፍ በመጠቀም በቅርቡ ጥናት ያስጀመረ ካለ እንዴት እንዳስጀመረ በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ። በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የቀረበውን “እውቀት መጽሐፍን ለማበርከት የሚረዱ አቀራረቦች” የሚል ርዕስ አስታውሳቸው። እውቀት መጽሐፍን በመጠቀም በአባሪው ገጽ 6 ላይ “ቀጥተኛ አቀራረብ” በሚል ርዕስ ከቀረቡት አቀራረቦች መካከል አንዱን አቅርብ።
16 ደቂቃ:- “መስበካችንን መቀጠል ያለብን ለምንድን ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለብዙ ዓመታት መስበካቸውን ሳያቋርጡ ለቀጠሉ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ መጠይቅ በማድረግ ደምድም። በዚህ ሥራ የጸኑት ለምን እንደሆነና መጽናታቸው እንዴት እንደጠቀማቸው እንዲናገሩ አድርግ።
መዝሙር 57 (136) እና የመደምደሚያ ጸሎት።