የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/02 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መጋቢት 11 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 18 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 25 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 1 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 3/02 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

መጋቢት 11 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 85 (191)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም በቅርብ ጊዜ የወጡ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! እትሞችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት የተለያዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ ክርስቲያናዊ ገለልተኝነታችንን መጠበቅ። ብቃት ባለው ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በሚቀጥለው ሳምንት ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች የተባለውን ቡክሌት ይዘው እንዲመጡ ሁሉንም አስታውሳቸው። ብሔራዊ ስሜትን የሚያንጸባርቁ ድርጊቶችን በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታና በመኖሪያ አካባቢ ማየት የተለመደ ሆኗል። እኛ በአጽናፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነት ላይ ስለተነሳው ግድድርና ስለ መንግሥቱ መልእክት እናውቃለን። ብሔራዊ ስሜት በሚንጸባረቅባቸው እንቅስቃሴዎች ለምን እንደማንሳተፍ ለሌሎች በዘዴ በምናስረዳበት ጊዜ በአምላክ ቃል ውስጥ ያገኘነውን ተስፋም ማካፈል ይገባናል። የይሖዋ ምሥክሮችና ትምህርት (እንግሊዝኛ) የተባለው ብሮሹር በገጽ 20-4 ላይ “ለባንዲራ ሰላምታ መስጠት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር እንዲሁም የማመራመር መጽሐፍ ገጽ 273-5 ብሔራዊ ስሜትን በሚያንጸባርቁ ሥነ ሥርዓቶች ለምን እንደማንካፈል ያብራራሉ። ዋና ዋና ነጥቦችን ካቀረብክ በኋላ ወላጆች እነዚህን ክፍሎች ከልጆቻቸው ጋር በጥንቃቄ እንዲከልሷቸው አበረታታ። በብሮሹሩ በገጽ 20 ላይ የሚገኘውን ተሞክሮ ተናገር። ዮሐንስ 6:​15፤ 17:​16 ላይና 18:​36 እንዲሁም ያዕቆብ 4:​4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ተናገር። ሁላችንም እነዚህን መሠረታዊ ሥርዓቶች በሚገባ ማወቃችንና በብሔራት ወይም በጎሳ መካከል በሚፈጠሩ ግጭቶች ውስጥ ለአንዱ ከመወገን መቆጠባችን ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ግለጽ። መንግሥታት ያላቸውን ሥልጣን እያከበርን ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ ብቻ የተወሰነ አምልኮ ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን ጎላ አድርገህ ተናገር።

20 ደቂቃ፦ “‘በበጎ ሥራ ባለ ጠጎች ሁኑ።’” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። መጋቢት 28 ለሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ዝግጅት ሁሉም በአገልግሎት የተሟላ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ። የመጋበዣ ወረቀቶቹን ጥሩ አድርገን እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል ተናገር። አስፋፊዎች ባለፈው ዓመት ዘመዶቻቸውን፣ ጎረቤቶቻቸውን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻቸውንና ፍላጎት ያሳዩ ሌሎች ሰዎችን በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ መጋበዝ የቻሉት እንዴት እንደሆነና እንዲህ ማድረጋቸው ምን ደስታ እንዳስገኘላቸው እንዲናገሩ ጋብዝ። ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ በሚያዝያ ወር ረዳት አቅኚ እንዲሆኑና ስብሰባው እንዳበቃ የአቅኚነት ማመልከቻ ቅጽ እንዲወስዱ አበረታታቸው።

መዝሙር 37 (82) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 18 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 62 (146)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ተወያዩበት። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር​—⁠2002 በተባለው ቡክሌት ላይ ከመጋቢት 23-28 ድረስ በወጣው ፕሮግራም መሠረት ሁሉም የመታሰቢያውን በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እንዲያነቡ አበረታታ።

15 ደቂቃ፦ “ከይሖዋና ከልጁ ጋር በደስታ ተባበሩ።” በሽማግሌ የሚቀርብ ቅዱስ ጽሑፋዊ የሆነ ቀስቃሽ ንግግር። ብዙ ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ አብረውን እንዲገኙ ለመጋበዝ ሁሉም እስከ መጋቢት 28 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።

20 ደቂቃ፦ ልጆቻችሁ መጽሐፍ ቅዱስን ጥሩ አድርገው መጠቀም እንዲችሉ አሰልጥኗቸው። አንደኛ ጴጥሮስ 3:​15ን በማንበብ ጀምር። ከዚያም ወላጆችን “ልጆቻችሁ ክርስቲያናዊ አቋማቸውን ለማስረዳት መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ያውቃሉ?” በማለት ጠይቅ። ወጣቶችን ደግሞ “አቋማችሁን ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሳችሁ ማስረዳት ትችላላችሁ?” ብለህ ጠይቅ። ከዚያም ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች በተባለው ብሮሹር ገጽ 9-11 ላይ “ጤናማ የሥነ ምግባር ደንቦች” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ሦስት ወይም አራት ነጥቦችን በጥያቄና መልስ ሸፍን። ቀጥለህ ምሳሌ የሚሆኑ ወጣት አስፋፊዎች በብሮሹሩ ገጽ በ12-15 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠቀም የልደት ቀንን፣ ገናንና ፋሲካን በተመለከተ ያላቸውን አቋም ሲያብራሩ የሚያሳይ ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሦስት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች እንዲያቀርቡ አድርግ። ሁሉም ያጠኑበትና ያሰመሩበት የራሳቸው የዚህ ብሮሹር ቅጂ እንዲኖራቸው አበረታታ።

መዝሙር 72 (164) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 25 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53 (130)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “ኮንትራቶችን የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ከልስ። በሚያዝያ ወር በረዳት አቅኚነት ለማገልገል ማመልከቻ ለማስገባት አሁንም ጊዜው እንዳላለፈ ተናገር። በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች በመጠቀም ጥቅስ ሲነበብና መጽሔት ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ። አስተዋጽኦ ማድረግ የሚቻልበትን ዝግጅት ጥቀስ። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ የአቀራረቡን አንዳንድ መልካም ገጽታዎች ጎላ አድርገህ ግለጽ።

15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። “ከአስተዳደር አካል የተላከ ደብዳቤ” ከሚለው ጎላ ያሉ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

18 ደቂቃ፦ “ልክን ማወቅ​—⁠ሰላምን ለማስፈን የሚረዳ ባሕርይ።” በመጋቢት 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21-24 ላይ ተመሥርቶ ከተግባራዊ ጠቀሜታና ከአንዳንድ የክለሳ ጥያቄዎች ጋር የሚቀርብ ንግግር።

መዝሙር 97 (217) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 10 (27)

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመጋቢት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው።

18 ደቂቃ፦ “‘ስጦታ የሆኑ ወንዶች’ የአምላክን መንጋ በትጋት ይጠብቃሉ።” በአንድ ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። የተጠቀሱትን ጥቅሶች አብራራ። አገልግሎት ላቆሙት የእረኝነት ጉብኝት በማድረግና አቅመ ደካማ የሆኑት የአቅማቸውን ያህል እንዲሠሩ በመርዳት ጥሩ ውጤት እንዴት ሊገኝ እንደሚችልና ደግሞም እንደሚገኝ ግለጽ። አፍቃሪ እረኞች መንጋው በይሖዋ አገልግሎት በንቃት እየተሳተፈ ለመቀጠል የሚያደርገውን ልባዊ ጥረት ያደንቃሉ።

20 ደቂቃ፦ “ከስብከቱ ሥራ የምታገኙት ደስታ እየጨመረ ይሂድ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 5ን ስትወያዩ በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ እንዴት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን እንዲናገሩ ጠይቅ። ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ ባደረግንበት የመጀመሪያ ወር ምን ያህል የአገልግሎት ክልል እንደተሸፈነ የክልል አገልጋዩን ጠይቅ። ለአንድ ሰው አጠር ያለ ምሥክርነት እንዴት መስጠት እንደምንችል የሚያሳዩ አንድ ወይም ሁለት ምሳሌዎችን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። በዚህ ሳምንት ሁሉም ለመመስከር የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን እንዲፈጥሩ አበረታታ።

መዝሙር 83 (187) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ