የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/02 ገጽ 9
  • መንፈሳዊ ፍላጎታችሁን አርኩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መንፈሳዊ ፍላጎታችሁን አርኩ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘በማዳመጥ ተጨማሪ ትምህርት ቅሰሙ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • መስማትና መማር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • “የአምላክ ትንቢታዊ ቃል” የ1999 የአውራጃ ስብሰባ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 9/02 ገጽ 9

መንፈሳዊ ፍላጎታችሁን አርኩ

1 በቅርቡ የምናደርገው “ቀናተኛ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች” የተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ መንፈሳዊ ፍላጎታችንን የምናሟላበት ግሩም አጋጣሚ ይሰጠናል። የስብሰባው ፕሮግራም ለጤና ተስማሚ እንደሆነ ሰብዓዊ ምግብ ‘የእምነትን ቃል’ በመመገብ በመንፈሳዊ ይገነባናል። (1 ጢ⁠ሞ. 4:6) ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንድንቀርብ ያስችለናል። እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመቋቋም የሚረዱንን ምክሮችና ማበረታቻዎች እናገኛለን። ይሖዋ “አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ” በማለት ማረጋገጫ ሰጥቶናል። (መዝ. 32:8) በሕይወታችን ውስጥ የሱን ፍቅራዊ መመሪያ በማግኘታችን ምንኛ ተባርከናል! ከስብሰባው ፕሮግራም የተሟላ ጥቅም ማግኘት እንድንችል ልንወስዳቸው የምንችላቸውን አንዳንድ ተግባራዊ እርምጃዎች እስቲ እንመልከት።

2 ልባችንን ማዘጋጀት ያስፈልገናል:- ሁላችንም የየራሳችንን ምሳሌያዊ ልብ የመጠበቅ ኃላፊነት ተጥሎብናል። (ምሳሌ 4:23) ይህም ራሳችንን መገሰጽንና ውስጣዊ ስሜታችንን በተመለከተ ለራሳችን ሐቀኛ መሆንን ይጠይቃል። ስብሰባው ከይሖዋ ጋር ባለን ዝምድና ላይ የምናሰላስልበትና ‘ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ የምንመለከትበት’ ወቅት ነው። ልባችን ‘በውስጣችን የሚተከለውን ቃል መቀበል’ ይችል ዘንድ ይሖዋ እንዲመረምረን፣ በውስጣችን እርማት የሚሻ “በደል” ካለ ለይቶ እንዲያመለክተንና ‘በዘላለም መንገድ’ እንዲመራን ልንለምነው ይገባል።​—⁠ያዕ. 1:21, 25፤ መዝ. 139:23, 24

3 አዳምጡ እንዲሁም አሰላስሉ:- ማርያም በጥሞና ታዳምጠው ስለነበር ኢየሱስ “መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም” በማለት አመስግኗታል። (ሉቃስ 10:39, 42) እኛም እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ካለን ትኩረታችን ተራ በሆኑ ነገሮች እንዲሠረቅ አንፈቅድም። ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ መቀመጫችንን ይዘን በትኩረት እንከታተላለን። ከሌሎች ጋር ከማውራት ወይም ያለምክንያት ወዲያ ወዲህ ከማለት እንቆጠባለን፤ እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በካሜራዎችና በቪዲዮ መቅረጫዎች ሌሎችን ላለመረበሽ ጥንቃቄ እናደርጋለን።

4 ንግግሮቹን በምናዳምጥበት ጊዜ ትምህርቱ እንዴት እየተብራራ እንዳለ ለማስተዋል እንዲረዳን አጭር ማስታወሻ ብንይዝ ጥሩ ይሆናል። የምናዳምጠውን ከዚህ በፊት ከምናውቀው ጋር ለማያያዝ መሞከር አለብን። እንዲህ ማድረጋችን ትምህርቱን በሚገባ ለመረዳትና በአእምሯችን ውስጥ ለመያዝ ይረዳናል። የጻፍነውን ማስታወሻ ስንከልስ ትምህርቱን እንዴት በሥራ ላይ ማዋል እንደምንችል ማሰብ ይኖርብናል። ሁላችንም ‘ይህ ትምህርት ከይሖዋ ጋር ያለኝን ዝምድና የሚነካው እንዴት ነው? በሕይወቴ ውስጥ ምን ዓይነት ማስተካከያዎችን ማድረግ ያስፈልገኛል? ከሌሎች ጋር ባለኝ ግንኙነት ረገድ ይህን ትምህርት በሥራ ላይ ማዋል የምችለው እንዴት ነው? በአገልግሎት ላይ እንዴት ልጠቀምበት እችላለሁ?’ እያልን ራሳችንን መጠየቃችን ተገቢ ነው። የነኳችሁን ነጥቦች ከሌሎች ጋር ተወያዩባቸው። እንዲህ ማድረጋችን የይሖዋን ቃል ‘በልባችን ውስጥ ጠብቀን’ ለማኖር ይረዳናል።​—⁠ምሳሌ 4:20, 21

5 የተማርነውን በሥራ ላይ እናውል:- አንድ ተሰብሳቢ በአውራጃ ስብሰባ ላይ ከተገኘ በኋላ እንዲህ አለ:- “ፕሮግራሙ በግለሰብ ደረጃ እያንዳንዱን ሰው በጥልቅ የሚነካ ሲሆን አንድ ሰው የራሱንና የቤተሰቡን የልብ ሁኔታ እንዲመረምርና አስፈላጊውን ቅዱስ ጽሑፋዊ እርዳታ ፍቅራዊ በሆነ መንገድ እንዲያቀርብ የሚያነሳሳ ነበር። ለጉባኤው ከአሁኑ የበለጠ እገዛ እንዳደርግ ስለተጣለብኝ ግዴታ ይበልጥ እንዳስብ ረድቶኛል።” ብዙዎቻችን እንደዚሁ እንደተሰማን አያጠራጥርም። ይሁን እንጂ ስብሰባው አበረታችና መንፈስን የሚያድስ እንደሆነ ተናግሮ መሄዱ ብቻውን በቂ አይደለም። ኢየሱስ ‘ይህን ብታውቁ፣ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ’ በማለት ተናግሯል። (ዮሐ. 13:17) በግል የሚነኩንን ነጥቦች በሥራ ላይ ለማዋል ትጋት የተሞላበት ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። (ፊልጵ. 4:9) መንፈሳዊ ፍላጎታችንን በተሟላ ሁኔታ ለማርካት ቁልፉ ይህ ነው።

[ገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

በሰማችሁት ትምህርት ላይ አሰላስሉ፦

■ ከይሖዋ ጋር ያለኝን ዝምድና የሚነካው እንዴት ነው?

■ ከሌሎች ጋር ባለኝ ግንኙነት ረገድ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?

■ በሕይወቴ ውስጥና በአገልግሎቴ ተግባራዊ ላደርገው የምችለው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ