መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“አንድ ግሩም ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ባካፍልዎት ደስ ይለኛል። [ማቴዎስ 22:37ን አንብብ።] ይህ ምን ማለት ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ‘አምላክን በልብህና በአእምሮህ ፈልገው’ የሚለውን ይህንን ርዕስ ይመልከቱ። እውነተኛ እምነት ከልብ ጋር ብቻ የተያያዘ ነገር ነው ወይስ አእምሮንም ማሠራት የሚጠይቅ ነው? መጽሔቱ የሚሰጠው መልስ ግንዛቤን የሚያሰፋ ነው።”
ንቁ! ሚያዝያ 2002
“መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ ትምህርት የማግኘትን አስፈላጊነት ያጎላል። [ምሳሌ 2:10, 11ን አንብብ።] አብዛኞቻችን ልጆች ብቃት ያላቸው መምህራን ማግኘታቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንገነዘባለን። ይህ ንቁ! መጽሔት መምህራን የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና ጎላ አድርጎ የሚገልጽ ከመሆኑም በላይ የሚከፍሏቸውን መሥዋዕቶች እንደምናደንቅ እንዴት ማሳየት እንደምንችልና መምህራን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟቸው ወላጆች እርዳታ ሊያበረክቱ የሚችሉበት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 15
“በየትኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች መተማመኛ የሚሆናቸው ነገር ማግኘት ይፈልጋሉ። ለምሳሌ ያህል ጥሩ ሥራ መያዝን እንደ መተማመኛ አድርገው ይመለከቱታል። ይሁን እንጂ ዘላለማዊ መተማመኛ ሊሆነን የሚችል ዘላቂ የደህንነት ምንጭ እንዳለ ያውቃሉ? [መዝሙር 16:8, 9ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም እውነተኛ መተማመኛ ማግኘት የሚቻልበትን መንገድ ያብራራል።”
Apr. 22
“በዛሬው ጊዜ ብዙዎች ሲከተሉት የኖሩትን ሃይማኖት እየተዉ አምላክን በራሳቸው መንገድ ማምለክ ጀምረዋል። ስለዚህ ሁኔታ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ አምላክን የምናመልክበት መንገድ ለውጥ እንደሚያመጣ ይናገራል። [ዮሐንስ 4:24ን አንብብ።] ይህ የንቁ! እትም መንፈሳዊ ፍላጎትዎን ሊያረኩ ስለሚችሉበት ከሁሉ የተሻለ መንገድ ይናገራል።”