የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/02 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሐምሌ 8 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 15 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 22 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 29 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 5 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 7/02 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሐምሌ 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 89 (201)

v15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 1 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት የተለያዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ‘እኛ ክርስቲያኖች ነን’ ለሚሉ ሰዎች በተለያየ መንገድ መልስ ሲሰጥ የሚያሳዩ ይሁኑ።​—⁠ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 19ን ተመልከት።

10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሳጥን። ለጉባኤው ተግባራዊ ሊሆን በሚችል መንገድ አንድ ሽማግሌ በንግግር ያቀርበዋል።

20 ደቂቃ፦ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመሥከር የተደራጁ መሆን። በአገልግሎታችን መጽሐፍ በገጽ 93 እና 94 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በወጣው አባሪ የመጀመሪያ ገጽ ላይ ያሉትን አቀራረቦች በመጠቀም ከዚህ ቀደም ለማያውቁት ሰው፣ ለጎረቤት፣ ለዘመድ ወይም ለጓደኛ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥክርነት ሲሰጥ የሚያሳዩ ሁለት ወይም ሦስት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።

መዝሙር 59 (139) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 61 (144)

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

18 ደቂቃ፦ “እናንተም እንዲሁ ሩጡ።” በጥር 1, 2001 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 28-31 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ።

20 ደቂቃ፦ በአገልግሎታችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስን መጠቀም ያስፈለገበት ምክንያት። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ኢየሱስ ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠንቅቆ ያውቅ የነበረ ሲሆን በሚያስተምርበትም ወቅት ከእነርሱ በተደጋጋሚ ይጠቅስ ነበር። (ሉቃስ 24:27, 44-47) ያስተማረው ከራሱ አመንጭቶ አልነበረም። (ዮሐ. 7:16-18) እኛም በአምላክ ቃል መጠቀማችን አስፈላጊ ነው። እኛ በራሳችን ከምንናገረው ቃል የበለጠ ኃይል አለው። (ዮሐ. 12:49, 50፤ ዕብ. 4:12) ቅዱሳን ጽሑፎች የሚሰጡት ማጽናኛና ተስፋ ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች ይስባል። በመግቢያችሁ ላይ ቢያንስ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ለማንበብ ግብ አድርጉ። ለዚህ ወር በተዘጋጁት መጽሔት ለማበርከት በሚረዱ አቀራረቦች ውስጥ የተካተቱትን ጥቅሶች አመልክት። አድማጮች በአገልግሎት ላይ መጽሐፍ ቅዱስን የሚጠቀሙት እንዴት እንደሆነና መጽሐፍ ቅዱስን መጠቀማቸው በራሳቸውና በሚያነጋግሯቸው ሰዎች ላይ ምን ውጤት እንዳመጣ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 96 (215) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 22 (47)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አብረው የሚያገለግሉ አንድ ወላጅና ልጅ በገጽ 1 ላይ ያሉትን አቀራረቦች በመጠቀም መጽሔቶቻችንን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ ያቀርባሉ። በአንደኛው ሠርቶ ማሳያ መጠበቂያ ግንብ በሌላኛው ደግሞ ንቁ! መጽሔት ይበረከታል። ልጆች በአገልግሎት እድገት እንዲያደርጉ ወላጆች እንዲያሰለጥኗቸው አበረታታ።

17 ደቂቃ፦ ስለ እስልምና ጥያቄዎችን ለሚጠይቅ ሰው ምን ብለህ ትመልሳለህ? በንግግርና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ (እንግሊዝኛ) ከተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 12ን በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስና ቁርዓን የሚመሳሰሉበትን አንዳንድ ነጥቦች በአጭሩ ግለጽ። (በገጽ 285 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ተመልከት።) እስልምና ስለ ነፍስ በሚያስተምረው ትምህርትና (ገጽ 297-300) መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ በሚሰጠው ማብራሪያ መካከል ያለውን ልዩነት አሳይ። (በገጽ 299 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።) በማመራመር መጽሐፍ በገጽ 374-378 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነፍስ ምን እንደሚል ፍላጎት ላሳየ አዲስ ሰው እንዴት ማብራራት እንደሚቻል በሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

18 ደቂቃ፦ ጥሩ የአመጋገብ ልማድ አዳብሩ። አንድ ሽማግሌ በጥቅምት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21-23 አንቀጽ 11-18 ላይ ተመሥርቶ ንግግር ያቀርብና ዋና ዋና ነጥቦችን ከአድማጮች ጋር በመከለስ ይደመድማል።

መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 79 (177)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሐምሌ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው።

10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

25 ደቂቃ፦ “እንደ አንድ አካል ተባብራችሁ ሥሩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 3ን ስትወያዩ ከሚያዝያ 22, 2000 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔት ገጽ ከ9-10 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። አንቀጽ 4 ላይ ደግሞ ከሚያዝያ 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16-17 አንቀጽ 4-6 ላይ ተጨማሪ ሐሳቦችን ተናገር።

መዝሙር 36 (81) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 17 (38)

13 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከጉባኤው የተገኙ አንዳንድ ተሞክሮዎች። አድማጮች በአውራጃ ስብሰባ ሲገኙ፣ በረዳት አቅኚነት ሲያገለግሉ ወይም በሌሎች መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ሲካፈሉ ያገኟቸውን አንዳንድ የሚያንጹ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።

20 ደቂቃ፦ “እርስ በርስ ለመበረታታት የሚያስችል ልዩ አጋጣሚ።” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አድማጮች የአውራጃ ስብሰባውን በጉጉት እንዲጠባበቁ አድርግ። ሁሉም አንድም ፕሮግራም ሳያመልጣቸው ከአርብ ጠዋት ጀምሮ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ አሳስባቸው።

12 ደቂቃ፦ “ሁልጊዜ መልካም ለማድረግ ትጉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ሁላችንም መልካም ፀባይ ማሳየታችን አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ተናገር።

መዝሙር 95 (213) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ