መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“ብዙ ሰዎች በቅርቡ የተፈጸሙትን አንዳንድ ክስተቶች ሲመለከቱ ንጹሐን ሰዎች አለ ዕድሜያቸው የሚቀጩት ለምንድን ነው ብለው ለመጠየቅ ተገፋፍተዋል። እርስዎስ ሰዎች ለምን ይሞታሉ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለትና በገጽ 7 ላይ የሚገኘውን ሰንጠረዥ አውጣ።] መጽሐፍ ቅዱስ ከእነዚህ የታወቁ አፈ ታሪኮች ስለ አንዱ ምን እንደሚል ማወቅ ይፈልጋሉ?” የሚቻል ከሆነ ከተጠቀሱት ጥቅሶች አንዱን አንብብለት።
ንቁ! ሰኔ 2002
“ብዙ የሥራ ቦታዎች ይበልጥ አደገኛ እየሆኑ እንደመጡ አስተውለው ይሆናል። ይህ መጽሔት የሥራ ቦታዎች አደጋ የማያስከትሉ እንዲሆኑ ምን ማድረግ እንደሚቻል ጥሩ ሐሳቦች ይዟል። ከዚህም በላይ ደህንነታችን ለሰብዓዊ ሥራ በሚኖረን ሚዛናዊ አመለካከት ላይ የተመካ መሆኑን ያመለክታል። እባክዎ ወስደው ያንብቡት።”
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 15
“እንደነዚህ ያሉት ችግሮች የሚወገዱበት ጊዜ የሚመጣ ይመስልዎታል? [የመጀመሪያውን ርዕስ የመግቢያ ሐሳብ አንብብና መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] እነዚህ ችግሮች በቅርቡ እንደሚወገዱ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈው የአምላክ ቃል ያረጋግጥልናል። [መዝሙር 72:12-14ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አሁን ያሉት ችግሮች እንዴት እንደሚወገዱ ያብራራል።”
Awake! June 22
“በምድር ላይ የሚኖር ሁሉም ሰው እውነተኛ ነጻነት ማግኘት የሚችል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አምላክ የገባውን ይህንን አስደሳች ተስፋ ይመልከቱ። [ሮሜ 8:21ን አንብብ።] ይህ ተስፋ እውን እንዲሆን ማንኛውም ዓይነት ባርነት መወገድ እንደሚኖርበት አይስማሙም? ይህ የንቁ! እትም አምላክ የሰጠው ተስፋ እንዴት እውን እንደሚሆን ይነግረናል።”