ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የጽሑፍ ክለሳ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከግንቦት 6 እስከ ነሐሴ 19, 2002 በነበሩት ሳምንታት በተሰጡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ ተዘግቶ የሚደረግ የጽሑፍ ክለሳ። በሌላ ወረቀት ተጠቅመህ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የቻልከውን ያህል ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ስጥ።
[ማሳሰቢያ:- በጽሑፍ ክለሳው ወቅት ለማንኛውም ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ማየት የሚፈቀደው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው። በቅንፍ ውስጥ የተጠቀሱት ጽሑፎች በግልህ ምርምር እንድታደርግባቸው የቀረቡ ናቸው። የትኛው መጠበቂያ ግንብ እንደሆነ በሚጠቀስበት ጊዜ አንቀጹ የተሰጠው በሁሉም ቦታ ላይ አይደለም።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር እውነት ወይም ሐሰት እያልክ መልስ:-
1. ኤርምያስ 18:1-6 ይሖዋ ሰዎች ከፈቃዳቸው ውጪ የሆኑ ነገሮች እንዲያከናውኑ እንደሚያስገድዳቸው ያሳያል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w99 4/1 ገጽ 22 አን. 3-4ን ተመልከት።]
2. ሐሰተኛ ነቢያት፣ ሰዎች የአምላክን እውነተኛ ማስጠንቀቂያ እንዲያዳምጡ በማድረግ ፋንታ ሐሰትን እንዲያዳምጡ በማበረታታት የአምላክ ቃል ያለውን ኃይልና ውጤት ሰርቀዋል። (ኤር. 23:30) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w92 2/1 ገጽ 4 አን. 3ን ተመልከት።]
3. ኤርምያስ 25:15, 16 ላይ ‘አሕዛብን ሁሉ የሚያሳብደው’ ‘ይህ የቁጣ የወይን ጠጅ ጽዋ’ የተባለው ነገር የሐሰት ሃይማኖት ያለውን የማደንዘዝ ኃይል ያመለክታል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w94 3/1 ገጽ 20 አን. 13ን ተመልከት።]
4. ማቴዎስ ‘የጠላት ምድር’ የሚለውን የኤርምያስ ትንቢት የተጠቀመበት መንገድ የታላቁ ሔሮድስ ሰለባ የሆኑት ሕፃናት በትንሣኤ አማካኝነት ተመልሰው የሚመጡበትን የሞት ምድር ያመለክታል። (ኤር. 31:15, 16፤ ማቴ. 2:17, 18) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w79 6/15 ገጽ 19 አን. 13ን ተመልከት።]
5. ኤርምያስ 37:21 ይሖዋ አስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ በሚኖርበት ጊዜ ታማኝ አገልጋዮቹን በሕይወት ማቆየት እንደሚችል ዋስትና ይሰጠናል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w97 9/15 ገጽ 3 አን. 4–ገጽ 4 አን. 2ን ተመልከት።]
6. የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በ607 ከዘአበ በኢየሩሳሌም ላይ ያደረሰው ጥፋት ያስከተለውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል። [si ገጽ 130 አን. 1]
7. ሰቆቃወ ኤርምያስ 5:7 ይሖዋ ወላጆቻቸው በሠሩት ኃጢአት በቀጥታ ልጆችን እንደሚቀጣ በግልጽ ያሳያል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 9/1 ገጽ 27 ሣጥኑን ተመልከት።]
8. ሕዝቅኤል 9:4 ላይ የተጠቀሰው ግምባር ላይ የሚጻፍ ምልክት እውቀት ብቻውን አንድን ሰው ከጥፋት እንደሚያተርፈው ያሳያል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 9/15 ገጽ 14 አን. 18ን ተመልከት።]
9. ኤፌሶን 4:8 [NW ] ላይ የተጠቀሱት “ስጦታ የሆኑ ወንዶች” በመንፈስ ቅዱስ የተሾሙና የእምነት አጋሮቻቸውን መንፈሳዊ ፍላጎቶች እንዲያሟሉ ሥልጣን የተሰጣቸው ክርስቲያን ሽማግሌዎች ናቸው። (ሥራ 20:28) [w00 8/1 ገጽ 6 አን. 3]
10. ሕዝቅኤል ምዕራፍ 23 ባለው ዘመናዊ ፍጻሜ መሠረት ኦሖሊባ ከፕሮቴስታንት እምነት ጋር ልትመሳሰል የምትችል ሲሆን ታላቅ እህቷ ኦሖላ ደግሞ ከሮማ ካቶሊክ ጋር ትመሳሰላለች። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 9/15 ገጽ 21 አን. 22ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ:-
11. በኢየሩሳሌም ጥፋት በተደመደመው ከ617 እስከ 607 ከዘአበ በነበሩት ወሳኝ ዓመታት ወቅት ጉልህ ሚና የነበራቸው ሦስት ነቢያት እነማን ናቸው? [si ገጽ 133 አን. 2]
12. ሉቃስ 9:23 ላይ ለቀረበው ግብዣ ምላሽ በመስጠት ለክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ልባዊ አድናቆት ማሳየት የሚቻለው እንዴት ነው? [w00 3/15 ገጽ 8 አን. 1]
13. ይሖዋ ኤርምያስን ‘ያታለለው’ በምን መንገድ ነው? (ኤር. 20:7) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w89 5/1 ገጽ 31 አን. 6ን ተመልከት።]
14. ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ “ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል” ሲል ምን ማለቱ ነበር? (ዮሐ. 14:26) [w00 4/1 ገጽ 8 አን. 7-8]
15. በኤርምያስ 35:18, 19 መሠረት ለዘመናዊው የሬካባውያን ክፍል የተዘረጋው ተስፋ ምንድን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ su ገጽ 131 አን. 7ን ተመልከት።]
16. ኔፊሊሞች “ስማቸው የታወቀ” እና “ኃያላን” የሆኑት በምን መንገድ ነው? (ዘፍ. 6:4) [w00 4/15 ገጽ 28 አን. 1]
17. ባሮክ መንፈሳዊ ሚዛኑን የሳተው እንዴት ነበር? እሱ ካጋጠመው ተሞክሮ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (ኤር. 45:1-5) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w97 8/15 ገጽ 21 አን. 14-16ን ተመልከት።]
18. ኤርምያስ 50:38 ላይ የሚገኘው ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው መቼና እንዴት ነበር? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ dp ገጽ 150 አን. 2-3ን ተመልከት።]
19. በሰቆቃወ ኤርምያስ 1:15 መሠረት ‘ድንግሊቱ የይሁዳ ልጅ’ ኢየሩሳሌም የደረሰባት ዕጣ ለሕዝበ ክርስትና ምን ትርጉም ይዟል? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 9/1 ገጽ 27 ሣጥኑን ተመልከት።]
20. ሕዝቅኤል 21:26 ላይ ተመዝግቦ በሚገኘው መሠረት “መጠምጠሚያውን አውልቅ፣ ዘውዱንም አርቅ” የሚለው አባባል ትርጉም ምንድን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 9/15 ገጽ 19 አን. 16ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር የሚያሟላውን ቃል (ቃላት) ወይም ሐረግ ስጥ:-
21. ልኩን የሚያውቅ ሰው ከመልካም _________________________ የሆነ ነገር አያደርግም። በተጨማሪም እንዲያደርግ በሚጠበቅበትና ሊያደርግ በሚችለው ነገር መካከል _______________________ እንዳለ ይገነዘባል። (ሚክ. 6:8) [w00 3/15 ገጽ 21 አን. 1-2]
22. መንፈስ ቅዱስ _________________________ ወይም _________________________ እንዳይደርስብን ባይከላከልልንም _____________________________________ ግን ሊረዳን ይችላል። (1 ቆሮ. 10:13፤ 2 ቆሮ. 4:7) [w00 4/1 ገጽ 11 አን. 6]
23. ነቢዩ ዳንኤል ኢየሩሳሌም ለ _________________________________ ባድማ ሆና እንደምትቆይ ኤርምያስ ከጻፈው ተገንዝቧል። ይህ ሁኔታ በትክክል መፈጸሙ ይሖዋ ባለው __________________________________________ የመናገር ችሎታ ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል። (ኤር. 25:12፤ ዳን. 9:2) [si ገጽ 129 አን. 37]
24. የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ በእውነተኛ አምላኪዎች ውስጥ ___________________________________ እና __________________________________ መንፈስ ሊያሳድርባቸው የሚገባ ሲሆን ይሖዋ አምላክን ለሚንቁ ደግሞ _________________________________ ማስጠንቀቂያ ሊሆናቸው ይገባል። [si ገጽ 132 አን. 13]
25. አብርሃም አለመግባባትን ለመፍታት ያሳየው የራስን ጥቅም በፈቃደኝነት የመተው ምሳሌ ____________________________ ወይም _____________________________ ከወንድሞቻችን ጋር ያለንን ውድ ዝምድና እንዲያበላሽብን እንዳንፈቅድ ያበረታታናል። (ዘፍ. 13:5-12) [w00 8/15 ገጽ 24 አን. 3-4]
ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ምረጥ:-
26. ኢዮብ የይሖዋን (እውቀት፤ ምሕረት፤ ፍርድ) ከፍ አድርጎ በመመልከት ባሪያዎቹን (በማስተዋል፤ በርኅራኄ፤ በአግባቡ) ይዟቸዋል። (ኢዮብ 31:13, 14) [w00 3/15 ገጽ 26 አን. 1]
27. ኤርምያስ 16:2-4 ላይ ነቢዩ በነጠላነት እንዲኖር የታዘዘው (ያለውን የራስን ጥቅም የመሰዋት መንፈስ ለማንጸባረቅ፤ መሲሑ የሚከተለውን የነጠላነት ሕይወት አስቀድሞ ለማሳየት፤ ይሖዋ ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋት የተናገረው ቃል እርግጠኛ መሆኑን ለማጠናከር) ነበር። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w78 4/15 ገጽ 31 አን. 2ን ተመልከት።]
28. ምሳሌ 4:7 ላይ ጥበብ የሚያመለክተው (ከተጨባጭ መረጃዎች ጋር መተዋወቅን፤ መረጃዎቹ እርስ በርስ ያላቸውን ዝምድና መረዳትን፤ እውቀትንና ማስተዋልን በሥራ ላይ ማዋልን) ነው። [w00 5/15 ገጽ 21 አን. 1]
29. የአምላክ ስም በመጀመሪያ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዴት ተብሎ ይነበብ እንደነበር በትክከል ማወቅ የሚያስቸግረው መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ በዕብራይስጥ ቋንቋ የተጻፈው (በአናባቢ፤ በተነባቢ) ፊደላት ብቻ ስለነበረ ነው። [rs ገጽ 195 አን. 3]
30. ሕዝቅኤል ምዕራፍ 1 ላይ የተገለጸው መንኰራኩር (የአምላክን መሲሐዊ መንግሥት፤ የይሖዋን መላእክታዊ መንፈሳዊ ድርጅት፤ ይሖዋ ከቀሪዎቹ ጋር የሚያደርገውን የሐሳብ ግንኙነት) ያመለክታል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 9/15 ገጽ 11 አን. 5ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያሉትን ጥቅሶች ከታች ካሉት ሐሳቦች ጋር አዛምድ:-
ዘዳ. 7:25, 26፤ ምሳሌ 4:18፤ 5:21፤ ኤር. 46:28፤ ሮሜ 15:4
31. ይህ ትእዛዝ የይሖዋ ሕዝቦች በፊት አክብሮት ይሰጧቸው የነበሩ ምስሎችን እንዴት ሊያዩአቸው እንደሚገባ ምሳሌ ይሆናቸዋል። [rs ገጽ 186 አን. 5]
32. አምላክ ማጽናኛ የሚሰጥበት አንደኛው መንገድ ስለ ወደፊቱ ጊዜ አስደናቂ ተስፋ በያዘው በጽሑፍ በሰፈረው ቃሉ አማካኝነት ነው። [5, w00 4/15 ገጽ 5 አን. 4]
33. ወላጆች የሚሰጡት ተግሣጽ ከተገቢው መጠን ማለፍ ወይም ከታቀደው የማረምና የማስተማር ዓላማ መውጣት የለበትም። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ kl ገጽ 148 አን. 20ን ተመልከት።]
34. ይሖዋ አገልጋዮቹ ዓላማውን እንዲረዱ የሚያደርገው ደረጃ በደረጃ ስለሆነ ብዙውን ጊዜ የእውቀት መጨመር የአስተሳሰብ ማስተካከያ ማድረግን ይጠይቃል። [rs ገጽ 206 አን. 3]
35. ማንኛውም ዓይነት የፆታ ርኩሰት ምንም ያህል በምሥጢር የተፈጸመ ቢሆን ከአምላክ የተሰወረ አይደለም። [w00 7/15 ገጽ 31 አን. 3]