ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ነሐሴ:- ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን? የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? መስከረም:- ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲገኝ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት በማድረግ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ። ኅዳር:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ሌላ የቆየ መጽሐፍ ልናበረክትላቸው እንችላለን።
◼ በ2002 የአውራጃ ስብሰባዎች ፕሮግራም ላይ የተደረጉ ማስተካከያዎች:-
መስከረም 27-29:- አዲስ አበባ(በእንግሊዝኛ)
ጥቅምት 11-13:- አዲስ አበባ (በአማርኛ እና በምልክት ቋንቋ)
ጥቅምት 18-20:- ድሬዳዋ (በአማርኛ)
ጥቅምት 18-20:- ደሴ (በአማርኛ)*
ጥቅምት 25-27:- ጅማ (በአማርኛ)
ጥቅምት 25-27:- መቀሌ (በአማርኛ እና በትግርኛ)
ኅዳር 1-3:- ሻሸመኔ (በአማርኛ)*
ኅዳር 1-3:- ነቀምቴ (በአማርኛ)
ኅዳር 8-10:- ባህር ዳር (በአማርኛ)*
ኅዳር 8-10:- ሶዶ (በአማርኛ)*
ኅዳር 9 እና 10:- ጊምቢ (በኦሮምኛ)
ኅዳር 16 እና 17:- ይርጋለም (በሲዳምኛ)
ኅዳር 16 እና 17:- አምቦ (በኦሮምኛ)*
ኅዳር 16 እና 17:- ሶዶ (በወላይትኛ)*
* ማስተካከያ የተደረገባቸው
◼ ጉባኤዎች በመስከረም ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2003 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2003 እና የ2003 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። እነዚህን ጽሑፎች በአረብኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛና በጣሊያንኛ ቋንቋዎች ማግኘት ይቻላል። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2003 በአማርኛና በትግርኛ ቋንቋዎች ማዘዝ ይቻላል።
◼ መስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ በእጅ ያሉት ጽሑፎችና መጽሔቶች ዓመታዊ ቆጠራ በተቻለ መጠን ነሐሴ 31, 2002 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይርቅ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ቆጠራ የጽሑፍ አስተባባሪው በየወሩ ከሚያካሂደው ቆጠራ ጋር ተመሳሳይ ነው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18-AM) ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶችን ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቡድኑ ከታቀፈው ከእያንዳንዱ ጉባኤ የመጽሔት አገልጋይ ማግኘት ይቻላል። እያንዳንዱ አስተባባሪ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18-AM) ይደርሱታል። እባካችሁ ዋናውን ቅጂ ከመስከረም 6 በፊት ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሙያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። የአስተባባሪው ጉባኤ ጸሐፊ ቆጠራውን በበላይነት መከታተል ይኖርበታል። እርሱና የአስተባባሪው ጉባኤ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ቅጹ ላይ ይፈርማሉ።