ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የጽሑፍ ክለሳ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከመስከረም 2 እስከ ታሕሳስ 23, 2002 በነበሩት ሳምንታት በተሰጡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ ተዘግቶ የሚደረግ የጽሑፍ ክለሳ። በሌላ ወረቀት ተጠቅመህ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የቻልከውን ያህል ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ስጥ።
[ማሳሰቢያ:- በጽሑፍ ክለሳው ወቅት ለማንኛውም ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ማየት የሚፈቀደው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው። በቅንፍ ውስጥ የተጠቀሱት ጽሑፎች በግልህ ምርምር እንድታደርግባቸው የቀረቡ ናቸው። የትኛው መጠበቂያ ግንብ እንደሆነ በሚጠቀስበት ጊዜ አንቀጹ የተሰጠው በሁሉም ቦታ ላይ አይደለም።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር እውነት ወይም ሐሰት እያልክ መልስ:-
1. አስደናቂ በሆኑት የይሖዋ ባሕርያት ላይ ማሰላሰል ወደ እሱ ለመቅረብ የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ ነው። (መዝ. 143:5) [w00 10/15 ገጽ 4 አን. 6]
2. ሕዝቅኤል 37:15-24 ላይ የተጠቀሰው የሁለቱ በትሮች መጋጠም ባለው ዘመናዊ ፍጻሜ መሠረት በ1919 ታማኝ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ‘አንድ ንጉሥ’ እና “አንድ እረኛ” በሆናቸው በክርስቶስ ሥር መሰባሰባቸውን ያሳያል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 9/15 ገጽ 25 አን. 13ን ተመልከት።]
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ተቺዎች በዳንኤል መጽሐፍ ላይ የሠፈረውን ታሪክ እውነተኝነት ቢጠራጠሩም ባለፉት ዓመታት በቁፋሮ የተደረሰባቸው ግኝቶች አባባላቸውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎባቸዋል። [si ገጽ 138 አን. 4]
4. የታመነ ከሚመስል ምንጭ ወይም ከፍተኛ እውቀት አለኝ ከሚል ሰው አንድ ነገር ብንሰማ ውሸት ነው ብለን እንዳንቀበል የሚያደርግ አጥጋቢ ምክንያት ሊኖረን አይችልም። [w00 12/1 ገጽ 29 አን. 7-8]
5. “ትናንሽ ትንቢቶች” የሚለው አባባል የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ክፍል የሆኑት የመጨረሻዎቹ 12 መጻሕፍት ያላቸው ጠቀሜታ አነስተኛ መሆኑን በሚገባ ይገልጻል። [si ገጽ 143 አን. 1]
6. ይሖዋ አሞጽን በይሁዳና በእስራኤል ትንቢት እንዲናገር በላከው ጊዜ ‘ከነቢያት ልጆች’ መካከል አንዱ ነበር። (2 ነገ. 2:3) [si ገጽ 148 አን. 1]
7. አብድዩ 16 ኤዶማውያን ለይሁዳ ባሳዩት ጥላቻ የተነሳ በብሔር ደረጃ እንደሚጠፉ ይተነብያል። (አብ. 12) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w89 4/15 ገጽ 30 ሣጥኑን ተመልከት።]
8. ሶፎንያስ 3:9 ላይ የተጠቀሰው ‘ንጹሕ ልሳን’ ስለ አምላክና ስለ ዓላማዎቹ የሚገልጸውን እውነት በተገቢ ሁኔታ መረዳትን ይጨምራል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w01 2/15 ገጽ 27 አን. 18ን ተመልከት።]
9. ኢየሱስ በጌቴሴማኒ መናፈሻ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ጭንቀት የተሰማው እንደ ተናቀ ወንጀለኛ ተቆጥሮ መሞቱ በይሖዋና በቅዱስ ስሙ ላይ ሊያመጣ የሚችለው ነቀፋ አሳስቦት ነው። (ማቴ. 26:38፤ ሉቃስ 22:44) [w00 11/15 ገጽ 23 አን. 1]
10. ዘካርያስ 9:6, 7 ላይ በተገለጸው መሠረት “በይሁዳም እንደ አለቃ” የሆነው ‘ፍልስጥኤማዊ’ በትንቢታዊ ሁኔታ በዛሬው ጊዜ “ታማኝና ልባም ባሪያ” እያሠለጠነ እንደ አስፈላጊነቱ ኃላፊነት የሚሰጣቸውን የሌሎች በጎች አባላትን ያመለክታል። (ማቴ. 24:45) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 7/1 ገጽ 23 አን. 14ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ:-
11. ምሥራቹን እንድንሰብክ የተሰጠን ኃላፊነት ሕዝቅኤል ጉበኛ ሆኖ እንዲያገለግል ከተሰጠው ኃላፊነት ጋር ሊመሳሰል የሚችለው እንዴት ነው? (ሕዝ. 33:1-11) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 1/1 ገጽ 28 አን. 13ን ተመልከት።]
12. ሕዝቅኤል በራእይ ከተመለከታቸው አጥንቶች ጋር የሚመሳሰለው በዘመናችን የታየው ነገር ምንድን ነው? (ሕዝ. 37:5-10) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 9/15 ገጽ 24 አን. 12ን ተመልከት።]
13. የዘካርያስ መጽሐፍ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት ለመጻፉ ከሁሉ ይበልጥ አሳማኝ የሆነው ማስረጃ ምንድን ነው? (ዘካ. 9:2-4) [si ገጽ 169 አን. 5]
14. ሕዝቅኤል በተመለከተው ራእይ ላይ የተጠቀሰው ከተማ ምን ያመለክታል? (ሕዝ. 48:15-17) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w99 3/1 ገጽ 18 አን. 22ን ተመልከት።]
15. በኢሳይያስ 2:2-4 መሠረት በዛሬው ጊዜ በእስራኤል እየታዩ ያሉ ክስተቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ አይደሉም ብሎ መናገር የሚቻለው እንዴት ነው? [rs ገጽ 224 አን. 3]
16. ዳንኤል ለ30 ቀናት ያህል ለንጉሡ ካልሆነ በስተቀር ለማንኛውም አምላክ ወይም ሰው ልመና እንዳይቀርብ ንጉሡ ላወጣው ሕግ ከሰጠው ምላሽ ምን ትምህርት ማግኘት ይቻላል? (ዳን. 6:7-10) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ dp ገጽ 125 አን. 25-8ን ተመልከት።]
17. ቅቡዓን ቀሪዎች በብሔራት መካከል እንደ አንበሳ የሆኑት የትኛውን የይሖዋን መልእክት በማወጃቸው ነው? (ሚክ. 5:8) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w81 7/15 ገጽ 23 አን. 10ን ተመልከት።]
18. ዕንባቆም 3:14 ላይ የሚገኘው “የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ” የሚለው አባባል ምን ሐሳብ ያስተላልፋል? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w00 2/1 ገጽ 22 አን. 15፤ w81 8/1 ገጽ 29 አን. 6-7ን ተመልከት።]
19. ሶፎንያስ 2:3 ላይ የሚገኘው “ምናልባት” የሚለው ቃል ምን ያሳያል? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w01 2/15 ገጽ 19 አን. 8ን ተመልከት።]
20. በዘካርያስ 8:6 (የ1980 ትርጉም ) መሠረት ከ1919 አንስቶ ባሉት ዓመታት ይሖዋ ያከናወነው በሰው ዘንድ በጣም አዳጋች የሚመስል ነገር ምንድን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w96 1/1 ገጽ 16 አን. 18-19ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር የሚያሟላውን ቃል (ቃላት) ወይም ሐረግ ስጥ:-
21. በ_________________________ አማካኝነት ይሖዋን የምናነጋግረው ሲሆን ይህም አምልኮታዊ በሆነ መንገድ ሐሳባችንን ለአምላክ መግለጽ ማለት ነው። እሱ እኛን የሚያነጋግርበት ዋነኛው መንገድ ደግሞ _________________________ አማካኝነት ነው። (መዝ. 65:2፤ 2 ጢሞ. 3:16) [w00 10/15 ገጽ 5 አን. 1-2]
22. ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እንዲጀምር የሚሰጠው ትእዛዝ ‘_________________________’ እንደሆነ የሚገልጸውን 1 ተሰሎንቄ 4:16 ከይሁዳ 9 ጋር በማወዳደር እሱ ሚካኤል መሆኑን ማወቅ እንችላለን። በተጨማሪም ሚካኤል የሚለው ስም “_________________________” የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ይህ ስም ኢየሱስ የይሖዋን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥና የአምላክን ጠላቶች ለማጥፋት በሚወሰደው እርምጃ ግንባር ቀደም እንደሚሆን በግልጽ ያሳያል። [rs ገጽ 219 አን. 1-2]
23. ‘ኢየሩሳሌምን የመጠገንና የመሥራት ትእዛዝ የወጣው’ _________________________ ሲሆን ይህም መሲሑ በተገለጠበት _________________________ የተደመደመው 69 የዓመታት ሳምንታት የጀመረበት ዓመት ነው። (ዳን. 9:25) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ dp ገጽ 190 አን. 20–ገጽ 191 አን. 22ን ተመልከት።]
24. ፀሐይ ወደ ጨለማ እንደሚለወጥ የሚናገረው ኢዩኤል 2:31 ከማቴዎስ 24:29, 30 ጋር ተዛማጅነት አለው። እዚህ ጥቅስ ላይ _________________________ የሰው ልጅ _________________________ እንደሚመጣ ተናግሯል። [si ገጽ 147 አን. 13]
25. _________________________ አሦርንና ዋና ከተማዋ _________________________ በተመለከተ የተናገረው ትንቢት የይሖዋን ፍትሕና የበላይነት ከፍ ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ይሖዋ በክፉዎች ላይ የፍትሕ እርምጃ እንደሚወስድ ትምክህት ያሳድርብናል። [si ገጽ 160 አን. 11]
ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ምረጥ:-
26. የሕዝቅኤል መጽሐፍ ይሖዋ (ለጋስ፣ ትሑት፣ ቅዱስ) መሆኑን ጎላ አድርጎ የሚገልጽ ከመሆኑም በላይ (አንድ ሰው የሚያዳብረው ባሕርይ፤ የይሖዋ ስም መቀደስ፤ ጥሩ ባልንጀራ መሆን) ከምንም ነገር በላይ እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ያሳውቃል። [si ገጽ 137 አን. 33]
27. ዳንኤል በኖረበት ዘመን የኖረው ሕዝቅኤል ዳንኤልን (ከኖኅና ከኢዮብ፤ ከሙሴና ከኢያሱ፤ ከኤልያስና ከኤልሳዕ) ጋር አያይዞ በመጥቀስ በእርግጥ በሕይወት የነበረ ሰው መሆኑን አረጋግጧል። [si ገጽ 138 አን. 2]
28. በዳንኤል 2:34, 35, 45 መሠረት ምስሉን የመታውና የፈጨው ድንጋይ (አርማጌዶንን፣ የአምላክ ሕዝቦች የሚያውጁትን ከባድ የፍርድ መልእክት፤ መሲሐዊውን መንግሥት) ይወክላል። [si ገጽ 142 አን. 20, 23]
29. ኢዩኤል 1:4-6 ላይ የተጠቀሰው ምሳሌያዊው የአንበጦች ብሔር (የእስራኤልን ብሔር፤ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን፤ የሮማን ሠራዊት) ያመለክታል። (ሥራ 2:1, 14-17) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w98 5/1 ገጽ 9 አን. 9ን ተመልከት።]
30. ቆላስይስ 1:13 ላይ የተጠቀሰው ‘የፍቅሩ ልጅ መንግሥት’ (መሲሐዊው መንግሥት፤ ከ33 እዘአ የጰንጠቆስጤ ዕለት አንስቶ ክርስቶስ በክርስቲያን ጉባኤ ላይ የጀመረው አገዛዝ፤ የክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት) ነው። [rs ገጽ 232 አን. 4]
ቀጥሎ ያሉትን ጥቅሶች ከታች ካሉት ሐሳቦች ጋር አዛምድ:-
ሆሴዕ 6:6፤ ኢዩ. 2:32፤ ዘካ. 4:6, 7፤ 13:3፤ ሮሜ 12:2
31. ይህ ሥርዓት የሚከተለው ባሕላዊም ሆነ ዓለማዊ የአቋም ደረጃ አስተሳሰባችንን እንዲቀርጸው መፍቀድ የለብንም። [w00 11/1 ገጽ 21 አን. 6]
32. አምላክን የሚያስደስተው ለወጉ ያህል የቀረበ ብዙ መሥዋዕት ሳይሆን እሱን በማወቅ ላይ የተመሠረተ የታማኝ ፍቅር መግለጫ ነው። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ si ገጽ 145 አን. 16ን ተመልከት።]
33. መለኮታዊውን ስም የተሸከመውን አካል ማወቅ፣ ማክበርና በእሱ መታመን ለመዳን የግድ አስፈላጊ ነው። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w89 3/15 ገጽ 30 ሣጥኑን ተመልከት።]
34. የአምላክ ዓላማ የሚፈጸመው በሰው ኃይል ሳይሆን አገልጋዮቹ ተራራ መሰል መሰናክሎችን እንዲወጡና ለአምላክ በሚያቀርቡት አገልግሎት እንዲጸኑ በሚያስችላቸው በመንፈሱ አማካኝነት ነው። [si ገጽ 169 አን. 2]
35. የይሖዋን ድርጅት ለይቶ የሚያሳውቀው የታማኝነት ባሕርይ የቅርብ የሥጋ ዝምድናን ከመሰለ ከማንኛውም ዓይነት ሰብዓዊ ዝምድና የላቀ ነው። [si ገጽ 171 አን. 24]