የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/02 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 12/02 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ታኅሣሥ፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥር፦ እንደ “መንግሥትህ ትምጣ ”፣ ወጣትነትህ፣ የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው ያሉ የቆዩ መጽሐፎችን ማበርከት ይቻላል። የካቲት፦ ራእይ ​—⁠ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት።

◼ የ2003 የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበት ዕለት ረቡዕ ሚያዝያ 16 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። ይህ ማስታወቂያ አስቀድሞ የወጣው ከአንድ በላይ የሆኑ ጉባኤዎች በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚጠቀሙ ከሆነና ሌሎች ተጨማሪ አዳራሾችን መከራየት ካስፈለገ ወንድሞች በአቅራቢያቸው የሚገኙ አዳራሾችን አስቀድመው መከራየት እንዲችሉ ነው። በዓሉ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ከመሆኑ አኳያ የሽማግሌዎች አካል የመታሰቢያውን ንግግር የሚያቀርበውን ወንድም ሲመድብ ብቃት ያለውን ሽማግሌ ይመርጣል እንጂ በተራ እንዲዳረስ ወይም በየዓመቱ አንድ ሽማግሌ ብቻ እንዲያቀርብ ማድረግ የለበትም። እንዲሁም በአጭሩ ንግግሩን የሚያስተዋውቅ ሊቀ መንበር መመደቡ ይመረጣል።

◼ ጥር 6 የሚጀምር ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የተገኙ የተጠመቁ አስፋፊዎች በሙሉ የሕክምና አሰጣጥን የሚመለከት ማሳሰቢያ/ባለሙያዎችን ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርግ ሰነድ የተባለውን ቅጽ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ለልጆቻቸው ደግሞ የመታወቂያ ካርድ ይሰጣቸዋል።

◼ ጉባኤዎች በወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉብኝት ሳምንት በሚያደርጉት የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። ይህ ማስተካከያ ሥራ ላይ የሚውለው ከጥር 2003 ጀምሮ ሲሆን ትምህርት ቤቱ በመዝሙርና በጸሎት ከተከፈተ በኋላ ለ25 ደቂቃ ያህል ይካሄዳል። በአንድ የንግግር ባሕርይ ላይ ለአምስት ደቂቃ ንግግር ከቀረበ በኋላ የማስተማሪያ ንግግር ለአሥር ደቂቃ ይቀርባል፤ ከዚያም የሳምንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ሐሳቦች ለአሥር ደቂቃ ያህል ይቀርባሉ። ክፍል ቁጥር 2, 3 እና 4 አይቀርቡም። ከትምህርት ቤቱ ቀጥሎ የአገልግሎት ስብሰባ ለግማሽ ሰዓት ይቀርባል። ከዚያም መዝሙር ይዘመርና የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ለግማሽ ሰዓት ንግግር ያቀርባል። ከዚያም ስብሰባው በመዝሙርና በጸሎት ይደመደማል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ