የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ታኅሣሥ 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 86 (193)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን አቀራረቦች በመጠቀም መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ “የመንግሥቱን መልእክት አውጁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 3ን ስትወያዩ ለሰዎች በምንመሰክርበት ወቅት እንዴት በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አውጥቶ ማንበብ እንደሚቻል የሚያሳዩ ሐሳቦችን ተናገር።—የመንግሥት አገልግሎታችን 12/01 ገጽ 1 አን. 3
18 ደቂቃ፦ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የመስክ አገልግሎት ሪፖርት። ይህን የመሰለ ጭማሪ እንዲገኝ ጉባኤያችሁ ያደረገውን አስተዋጽኦ ጥቀስ። “ቀናተኛ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች” የሚለውን የአውራጃ ስብሰባ ጭብጥ አስታውሳቸውና በቀጣዮቹ ወራት አዘውትሮ ለማገልገል፣ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎችን ለመደገፍ፣ የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈንና አስፋፊዎች በአገልግሎት የሚያሳልፉትን አማካይ ሰዓት ለማሳደግ ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ግለጽ። በተለይ የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት በሚያዝያ ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል እቅድ እንዲያወጡ አበረታታ። እንዲሁም በመንፈሳዊ ንቁ ሆኖ ለመኖር ሁሉም በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ፣ የግል ጥናት ማድረግና አዘውትሮ መጸለይ አስፈላጊ መሆኑን እንዲገነዘቡ እርዳቸው።—ፊልጵ. 2:12፤ ሉቃስ 21:36
መዝሙር 87 (195) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 11 (29)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ታኅሣሥ 29 ለማድረግ ስለታቀደው ልዩ የመስክ አገልግሎት ዝግጅት ተናገር። በጉባኤው ጸሐፊ የሚቀርብ። የጉባኤው የኅዳር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት። የኅዳር ወር የአገልግሎት ሪፖርት ከመስከረምና ከጥቅምት ጋር ሲወዳደር ምን ይመስላል? የጉባኤው አማካይ የአስፋፊ ሰዓት ከአገር አቀፉ አማካይ ጋር ሲወዳደር ምን ይመስላል? በዚህ የአገልግሎት ዓመት ምን ያህል የአገልግሎት ክልሎች ተሸፍነዋል? ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት ሁሉም በአገልግሎት እንዲካፈሉ አበረታታቸው።
15 ደቂቃ፦ ጥበበኞች ያስተውላሉ። (ዳን. 12:3, 10) በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። ፍላጎት ያሳየ አንድ ሰው “ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያላችሁ እውቀት ትክክለኛ መሆኑን እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለሁ?” በማለት ይጠይቃል። አስፋፊው በአንድ ርዕስ ላይ በማተኮር የሚደረገውን የመጽሐፍ ቅዱስ የአጠናን ዘዴ ያብራራለታል። (መጠበቂያ ግንብ 96 5/15 ገጽ 19-20) ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 113-117 ላይ ከሰፈሩት ምሳሌዎች ውስጥ አንዱን ወይም ሁለቱን በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በጥልቀት በመመርመር አምላክ ለምድር ያለውን ዓላማ እንዴት መረዳት እንደቻልን ያሳየዋል። አስፋፊው ይህንኑ ዘዴ በመጠቀም ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን እንዴት በትክክል መረዳት እንደሚቻል ይነግረውና መጽሐፍ ቅዱስን አብሮት እንዲያጠና ግብዣ ያቀርብለታል።
15 ደቂቃ፦ “በታማኝነት የሚመላለሱ አረጋውያንን አስቡ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከነሐሴ 1, 1994 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። አቅመ ደካማ የሆኑ አረጋውያን እስከ 15 ደቂቃ የሚደርስ የመስክ አገልግሎት ሪፖርት መመለስ እንዲችሉ የተደረገውን ዝግጅት ጥቀስ። ከአረጋውያን ምሥክሮች ጋር ተቀራርቦ ጊዜ ማሳለፍ የጋራ በረከት እንደሚያስገኝ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን የሚናገሩ አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።
መዝሙር 35 (79) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 63 (148)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን አቀራረቦች በመጠቀም መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ሁሉም ጥር 6 በሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተባለውን ቪዲዮ በመመልከት ተዘጋጅተው እንዲመጡ አሳስባቸው።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ “ትክክለኛ ሪፖርት እንዲዘጋጅ የበኩልህን አስተዋጽኦ ታደርጋለህን?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 2ን ስትወያዩ አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 106-8 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 65 (152)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን ለመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቻቸው እንዲሰጡ አስታውሳቸው። ጉባኤያችሁ በአዲሱ ዓመት የአገልግሎት ሰዓት የሚቀይር ከሆነ ሁሉም በአዲሱ ሰዓት አዘውትረው እንዲገኙ በደግነት አሳስባቸው። በጥር ወር የሚበረከተውን መጽሐፍ ጥቀስ። በጉባኤው ውስጥ ያሉትን ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት ልዩ ትኩረት እንዲደረግባቸው አድርግ።
35 ደቂቃ፦ “‘ቀናተኛ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች’ ከተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ የተሟላ ጥቅም ማግኘት።” በመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪው የሚቀርብ። በአንድ ደቂቃ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በርዕሱ ውስጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቅመህ በአውራጃ ስብሰባው ላይ የቀረበውን ትምህርት ከአድማጮች ጋር በውይይት አቅርበው። ጊዜህን አመጣጥነህ ተጠቀምበት። አድማጮች ቁልፍ ነጥቦችን እንዲያስታውሱ ለመርዳት አጫጭር ሐሳቦችን ማከል ትችላለህ። ተስማሚ በሚሆንበት ጊዜ አድማጮች በስብሰባው ላይ የተማሩትን እንዴት በሥራ ላይ እንዳዋሉና እንዲህ ማድረጋቸው ምን ጥቅሞች እንዳስገኘላቸው እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 84 (190) የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 31 (67)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
23 ደቂቃ፦ አምላክ ደምን አስመልክቶ ያወጣውን ሕግ ለማክበር የሚረዳ ዝግጅት። ከቅርንጫፍ ቢሮው በተላከው አስተዋጽኦ ላይ ተመሥርቶ ብቃት ባለው ሽማግሌ በንግግር የሚቀርብ። የጉባኤው ጸሐፊ ለወንድሞች የሚታደሉትን የሚከተሉትን ሰነዶች በበቂ መጠን መያዝ ይኖርበታል:- የሕክምና አሰጣጥን የሚመለከት ማሳሰቢያ/ባለሙያዎችን ከተጠያቂነት ነፃ የሚያደርግ ሰነድ፣ የመታወቂያ ካርድ፣ ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም፣ የሕክምና ሰነዶች አጠቃቀም መመሪያ። የዕለቱ ስብሰባ ካለቀ በኋላ ሰነዶቹ ለተጠመቁ አስፋፊዎች በሙሉ የሚታደሉ ሲሆን የሚሞሉት ግን ዛሬ አይደለም። የሰነዱ ባለቤትም ሆነ ምሥክሮቹ በሰነዶቹ ላይ የሚፈርሙትና ቀኑን የሚሞሉት በቀጣዩ ሳምንት የሚደረገው የመጽሐፍ ጥናት ስብሰባ ካለቀ በኋላ ሲሆን አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የመጽሐፍ ጥናቱ የበላይ ተመልካች ይረዳቸዋል። ምሥክር ሆነው የሚፈርሙት ሰዎች ግለሰቡ ሰነዱ ላይ ሲፈርም ማየት ይኖርባቸዋል። ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም የተባለው ሰነድ ከመሞላቱ በፊት የሕክምና ሰነዶች አጠቃቀም መመሪያ የተሰኘው ሰነድ በጥንቃቄ መነበብ ይኖርበታል። ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም የተባለውን ሰነድ ከዚህ በፊት ሞልተህ ከነበረና በደንብ የተያዘ ከሆነ ሌላ ቅጽ መሙላት አያስፈልግህም። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ከሁኔታቸውና ከአቋማቸው ጋር በሚስማማ መንገድ ሐሳቡን ከእነዚህ ሰነዶች ላይ በመውሰድ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው የሕክምና መመሪያ ማዘጋጀት ይችላሉ።
17 ደቂቃ፦ “ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተባለውን ፊልም ማየት አለብህ።” ብቃት ያለው አንድ ሽማግሌ ያቀርበዋል። በገጽ 7 ላይ ባለው ሣጥን ውስጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም በቀጥታ ደም አልወስድም በተባለው የቪዲዮ ፊልም ላይ ከአድማጮች ጋር መወያየት ጀምር። ስትደመድም የመጨረሻውን አንቀጽ አንብብ።
መዝሙር 35 (79) እና የመደምደሚያ ጸሎት።