የቤቴል ግንባታ ፕሮጀክታችን በመፋጠን ላይ ነው!
ከታች የምትመለከቷቸው ፎቶግራፎች በግንባታ ላይ ያለውን የቤቴል ሕንጻ የሚያሳዩ ሲሆኑ በጥቅምት ወር የተነሱ ናቸው። ከላይ ያለው ፎቶ የሚያሳየው ከፊት ለፊት በኩል ያለውን የሕንጻውን መግቢያና የእንግዳ መቀበያ ክፍሉን ነው። የታችኛው ፎቶግራፍ ደግሞ ሕንጻውን ከበስተጀርባ የሚያሳይ ነው። የግንባታው ሥራ እየተከናወነ ያለው በአንድ የሕንጻ ተቋራጭ ድርጅት ስለሆነ በአሁኑ ወቅት ሕንጻውን ለመጎብኘት እንደማይቻል ስንገልጽላችሁ እናዝናለን። የሕንጻው ግንባታ እየተፋጠነ ሲሆን ከፎቶግራፎቹ ማየት እንደምትችሉት የመጨረሻው ፎቅ በመሠራት ላይ ነው። ግንባታው በወጣለት ፕሮግራም መሠረት በሚያዝያ 2004 ገደማ ይጠናቀቃል ብለን እንጠብቃለን። በዚህ አጋጣሚ ለምታደርጉት የገንዘብ መዋጮና ሥራው እንዲሳካ ለምታቀርቡት ጸሎት ልባዊ ምስጋናችንን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን።
[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
▲ ከፊት ለፊት ያለው የሕንጻው መግቢያና የእንግዳ መቀበያ ክፍል ከበስተጀርባ ▼