የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ሚያዝያ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 81 (181)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የመጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 2003 ንቁ! ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውንም መጽሔት አያይዞ ያበረክታል።
10 ደቂቃ:- “አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም” የሚለውን ተወያዩበት። በዚህ ዓመት ልዩ ስብሰባ የሚደረግበትን ቀን ተናገርና ሁሉም በስብሰባው ላይ ቀደም ብለው እንዲገኙ እንዲሁም ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ በትኩረት እንዲያዳምጡ አበረታታ። አስፋፊዎች ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻቸውን በስብሰባው ላይ እንዲገኙ እንዲጋብዟቸው አበረታታ።
10 ደቂቃ:- “ለአገልግሎቱ አዎንታዊ አመለካከት ያዙ።” በግንቦት 1, 2001 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 9ና 10 በአንቀጽ 9-12 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
15 ደቂቃ:- “ብርሃን አብሪ መሆን።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።
መዝሙር 73 (166) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 65 (152)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ሁሉም ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን በመጋበዝና በስብሰባው ላይ ብዙ ሰዎች እንዲገኙ በማድረግ ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በእርግጥም “ልዩ” እንዲያደርጉት አበረታታ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
22 ደቂቃ:- “ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ነጠላ መሆናቸው ያስገኘላቸውን ነጻነት ተጠቅመው የመንግሥቱን ጥቅሞች በማስፋፋት ላይ ለሚገኙ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግላቸው። በአገልግሎታቸው እርካታ እንዲያገኙ የረዳቸው ምን እንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ። ለሰባት ደቂቃ ያህል ከነሐሴ 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20-23 ላይ “ልጆች ያልወለዱት ለምንድን ነው?” ከሚለው ርዕስ አንዳንድ ተስማሚ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። ነጠላ የሆኑ ወይም ልጆች ያልወለዱ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ትዳር እንዲይዙ ወይም ልጅ እንዲወልዱ መጎትጎት ወይም በነገር መጎንተል ከመንግሥቱ ጥቅሞች ጋር እንደሚጋጭ ግለጽ።
መዝሙር 15 (35) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 16 (37)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሚያዝያ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 6 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የመጋቢት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 8 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
15 ደቂቃ:- “ይሖዋ ከልብ የምናደርገውን ጥረት ይባርካል።” ከነሐሴ 1, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29-31 ላይ የሚቀርብ ንግግር። በገጽ 30 አንቀጽ 3 እና 4 እንዲሁም በገጽ 31 አንቀጽ 3 እና 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች ጎላ አድርገህ ግለጽ። በትምህርት ሰበብ ከስብሰባ መቅረትን በተመለከተ ለጉባኤው እንደሚሠራ አድርገህ አቅርበው።
20 ደቂቃ:- “ተመላልሶ መጠየቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ያስችላል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንድ ሽማግሌ ጥያቄዎቹን በመጠቀም ያቀርበዋል። አድማጮች በአንቀጾቹ ውስጥ የቀረቡትን ሐሳቦች የሚያጠናክሩ አጫጭር የአገልግሎት ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ። አንቀጽ 5ን ስትወያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሲጀመር የሚያሳይ ከጉባኤያችሁ የተገኘ ተሞክሮ በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 41 (89) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 17 (38)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ተመላልሶ መጠየቅ ብለን የምንይዘው ምን ስናደርግ እንደሆነ ተናገር። ለመጽሔት ደንበኛችን መጽሔት ስንወስድለት፣ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን በስልክ ስናነጋግር፣ ወደ ጉባኤ ይዘናቸው ስንሄድ እንዲሁም ከዘመዶቻችን፣ ከጎረቤቶቻችን፣ ከሥራ ባልደረቦቻችን፣ አብረውን ከሚማሩት ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ስናደርግ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ለሰዎች ስናስጠና . . . ወዘተ ተመላልሶ መጠየቅ መያዝ እንደምንችል ግለጽ። አገልግሎታችን የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 88-89ን አውጣና ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ለተመላልሶ መጠየቅ መቼ ልንቀጥራቸው እንደሚገባ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ተናገር። እንዲሁም በግንቦት ወር በዓላት የሚከበሩባቸውን ቀኖችና በእነዚያ ቀናት ለአገልግሎት የተደረጉ ዝግጅቶችን ጥቀስ።
20 ደቂቃ:- “ሥርዓታማ አለባበሳችን ለአምላክ አክብሮት እንዳለን ያሳያል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በሽማግሌ የሚቀርብ። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። ጥሩ የማንበብ ችሎታ ያለው አንድ ወንድም ድምፁን ከፍ አድርጎ አንቀጾቹን እንዲያነብልህ አድርግ።
15 ደቂቃ:- መልካም ሪፖርት—ልብን ያስደስታል። (ምሳሌ 15:30) ጉባኤው በመጋቢትና በሚያዝያ ያደረገውን ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ አስመልክቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች በሚከተሉት ዘርፎች ያገኟቸውን የሚያበረታቱ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ:- (1) ፍላጎት ያሳየ ሰው በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኝ መርዳት፣ (2) ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል፣ (3) አገልግሎት አቁሞ የነበረ አስፋፊ ከጉባኤው ጋር እንቅስቃሴ ማድረጉን እንዲቀጥል መርዳት፣ (4) አዲስ ሰው ምሥራቹን መስበክ እንዲጀምር መርዳት፣ (5) በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ አዳዲስ ሰዎችን ፍላጎት መኮትኮት፣ (6) ከዚህ በፊት ያልተሠራባቸውን የአገልግሎት ክልሎች መሸፈን። በግንቦት መከናወን ያለባቸው የቀሩ ነገሮችን ጥቀስ። አንዳንዶቹን ተሞክሮዎች የሚናገሩ አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ። ሁሉንም ላደረጉት ጥረት አመስግናቸውና ወደፊትም በጥረታቸው እንዲገፉበት አበረታታቸው።
መዝሙር 55 (133) እና የመደምደሚያ ጸሎት።