የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/03 ገጽ 2-7
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሰኔ 9 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 16 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 23 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 30 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 7 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 6/03 ገጽ 2-7

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሰኔ 9 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 36 (81)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የግንቦት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት 2003 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውን መጽሔት አያይዞ ያበረክታል። በእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ ላይ ጥቅስ መነበብ ይኖርበታል።

15 ደቂቃ:- “ተቀዳሚ ሥራችን የሆነው ክርስቲያናዊ አገልግሎት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ወጣቶች የሙሉ ጊዜ አገልግሎትን ቢጀምሩ የሚያገኟቸውን በረከቶች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ አበረታታ። ከኅዳር 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19-20 ላይ “ባህልና ሕሊና በሚጋጭበት ጊዜ” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

20 ደቂቃ:- “ጡረታ መውጣት በአገልግሎት የበለጠ ተሳትፎ ለማድረግ በር ይከፍት ይሆን?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የሚቻል ከሆነ የጡረታ ጊዜያቸውን ይሖዋን የበለጠ ለማገልገል ለተጠቀሙበት ለአንድ አስፋፊ ቃለ መጠይቅ አድርግ። ምን ማስተካከያ ማድረግ እንዳስፈለጋቸውና በውጤቱም ምን በረከቶችን እንዳገኙ ጠይቃቸው።

መዝሙር 84 (190) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 16 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 58 (138)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

12 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

25 ደቂቃ:- “‘የምሥክርነቱን ሥራ’ በትጋት አከናውኑ።” ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። በአንቀጽ 5 እና 6 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ ለአንድ ባለ ሱቅ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥክርነት ሲሰጥና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለው ትራክት ሲበረከት የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በአንቀጽ 7 እና 8 ላይ ከመወያየታችሁ በፊት አንቀጾቹ እንዲነበቡልህ አድርግ። በመጨረሻም “አትርሷቸው!” የሚለውን ሣጥን አንብበህ ተወያዩበት።

መዝሙር 69 (160) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 23 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 71 (163)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የግንቦት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውን መጽሔት አያይዞ ያበረክታል።

20 ደቂቃ:- የተስፋ መቁረጥን ስሜት ለመቋቋም ምን ማድረግ ይቻላል? በኅዳር 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-9 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። “ጥሩ ዝንባሌ መያዝ” የሚለውን ንዑስ ርዕስ ጨምረህ አቅርብ። ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክሮችንና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን ግለጽ። ውጤታማ የሆኑ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች በአገልግሎታቸው ደስተኞች እንዲሆኑ ምን እንደረዳቸው እንዲናገሩ አስቀድመህ ዝግጅት አድርግ።

15 ደቂቃ:- “ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ መስበክ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ 2 እና 3 ላይ ስትወያዩ አድማጮች በአካባቢያችሁ የትኞቹን ወቅታዊ ጉዳዮች መግቢያ አድርገው መጠቀም እንደሚችሉ እንዲናገሩ ጋብዝ። በአንቀጽ 4 ላይ ስትወያዩ ከተጠቆሙት አቀራረቦች መካከል በአንዱ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 2 (4) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 30 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 1 (3)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሰኔን ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በሐምሌና በነሐሴ የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። ጉባኤው ካሉት ብሮሹሮች መካከል ሁለቱን አስተዋውቅና ብሮሹሮቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንዳንድ አቀራረቦችን ለማግኘት የ1995 እና የ1996 ሐምሌና ነሐሴ፣ የ1997 ነሐሴ እና መስከረም፣ እንዲሁም የ1998 ነሐሴ የመንግሥት አገልግሎታችንን የመጨረሻ ገጾች ተመልከት። ተጨማሪ አቀራረቦች የሚገኝባቸውን ጽሑፎች ለማግኘት ከመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ ላይ “Presentations” በሚለው ርዕስ ሥር “List by Publication” የሚለውን ንዑስ ርዕስ ተመልከት።

15 ደቂቃ:- “የአካል ጉዳተኝነት ፍሬያማ ከመሆን አያግድም።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከነሐሴ 22, 1990 ንቁ! መጽሔት ገጽ 22-3 ላይ (እንግሊዝኛ) “ሌሎች ምን እርዳታ ማበርከት ይችላሉ?” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

20 ደቂቃ:- ስለ አምላክ መንግሥት ለመስበክ የአምላክን ቃል ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠቀሙ። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። በአገልግሎት ላይ ለምናገኘው ለእያንዳንዱ ሰው ስለ መንግሥቱ የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ለማንበብ ጥረት እናደርጋለን። ይሁን እንጂ ጥቅሶችን ከማንበብ የበለጠ ነገር ማድረግ ይኖርብናል። ጥቅሶቹን ማብራራት፣ በምሳሌ ማስረዳትና እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ መናገር ይኖርብናል። በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 155-6 ላይ “ሰብዓዊ ገዥዎች የሰው ልጅ በአስቸኳይ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማቅረብ አልቻሉም” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር የሚገኙ አንዳንድ ጥቅሶችን እንደምሳሌ ተጠቅመህ ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል አሳይ። ከዚያም አንድ አስፋፊ በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት አንድን ጥቅስ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ። አስፋፊው ጥቅስ በማንበብ ሠርቶ ማሳያውን ይጀምርና የአምላክ መንግሥት አገዛዝ ግለሰቡን እንዴት እንደሚጠቅመው ለማስረዳት አጭርና ግልጽ ማብራሪያ፣ ቀላል ምሳሌና ተግባራዊነቱን የሚያሳይ ሐሳብ በማቅረብ ሠርቶ ማሳያውን ይደመድማል። ከሠርቶ ማሳያው በኋላ አስፋፊው ጥቅሱን እንዴት እንዳብራራ፣ ምን ምሳሌ እንደተጠቀመና ተግባራዊነቱን እንዴት እንዳጎላ በአጭሩ ግለጽ። ሁሉም የአምላክን ቃል ውጤታማ በሆነ መንገድ የመጠቀም ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ አበረታታ።

መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 57 (136)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ:- “የይሖዋን መሥፈርቶች ለማክበር መነሳሳት።” በነሐሴ 1, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 17-19 አን. 11-18 ላይ ተመሥርቶ በመጠበቂያ ግንብ መሪው የሚቀርብ ንግግር። በመጽሔቱ ላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። አድማጮች መልሱ ግልጽ እንዲሆንላቸው እርዳቸው። አንቀጽ 13 ላይ ስትደርስ ቤቴልን በምንጎበኝበት ጊዜ አለባበሳችንና የጸጉር አበጣጠራችን ምን መሆን እንዳለበት ከሚናገረው የሰኔ 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን የጥያቄ ሣጥን ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። ብዙ ጎብኚዎች በዚህ ረገድ ችግር ባይታይባቸውም ጂንስ ልብሶች በምንዝናናበት ጊዜ የሚለበሱ ልብሶች በመሆናቸው በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ወይም ቤቴልን በምንጎበኝበት ጊዜ መልበስ ተገቢ እንዳልሆነ በግልጽ ተናገር። አንቀጽ 16 ላይ ስትደርስ በአገራችን እንኳ ብዙ ጊዜ በቢሮዎችና በሽያጭ ሱቆች ውስጥ የሚሠሩ ሴቶች ሰውነትን የሚያጋልጥ ልብስ እንዲለብሱ እንደሚጠበቅባቸውና ይህም ከይሖዋ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ጋር እንደሚጋጭ ግለጽ። በአንቀጽ 18 ላይ ደግሞ ሁሉም በአለባበስ ረገድ የይሖዋን ከፍተኛ የሥነ ምግባር ደረጃ እንዲጠብቁ አበረታታ።

20 ደቂቃ:- “መለኮታዊውን ስም ማስታወቅ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። አንቀጽ 4 ላይ ስትደርሱ አዋጅ ነጋሪዎች ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 124 ላይ ከሚገኘው “የአምላክን ስም ማስታወቅ” ከሚለው ሣጥን ውስጥ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። ጥሩ ተሞክሮ ያለው አንድ አስፋፊ ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርግ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ። በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 197-8 ላይ በሚገኙ ሁለት ወይም ሦስት ጥቅሶች አማካኝነት የአምላክን የግል ስም ማወቅና ስሙን መጥራት አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ተናገር።

መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ