የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ሐምሌ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 26 (56)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2003 ንቁ! መጽሔቶችን በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል።
15 ደቂቃ:- የይሖዋ አምልኮ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲኖረን የሚያስችለው እንዴት ነው? ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ደስተኛና ትርጉም ያለው ሕይወት ለመምራት ቁልፉ እውነተኛ አምልኮ ነው። (1) በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙንን ችግሮችና ጭንቀቶች እንድንቋቋም ይረዳናል። (ፊልጵ. 4:6, 7) (2) አምላካዊ ባሕርያትን እንድንኮተኩት ያበረታታናል። (2 ጴጥ. 1:5-8) (3) ጊዜያችንንና ንብረታችንን ከሁሉ በተሻለ መንገድ እንድንጠቀምበት ይረዳናል። (1 ጢሞ. 6:17-19) (4) የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ የተረጋገጠ ተስፋ ይሰጠናል። (2 ጴጥ. 3:13) (5) ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ዝምድና እንድንመሠርት ያስችለናል። (ያዕ. 4:8) ይሖዋን የማያውቁና የማያገለግሉ ሰዎች እነዚህ ነገሮች እንደሌሏቸው አብራራ።
20 ደቂቃ:- “አምላክ ላሳየን ምሕረት አመስጋኝ መሆን።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 3ን ስትወያዩ በጥቅምት 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 12 ላይ የቀረበውን ሐሳብ መሠረት በማድረግ የመጽሔት ደንበኞች ለማፍራት የሚረዱ ሐሳቦችን ተናገር። ጥሩ ችሎታ ያላቸው አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በማስጀመር ረገድ ውጤታማ ሆኖ ያገኙትን መንገድ እንዲናገሩ ጋብዝ። ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመርና የመምራት ግብ እንዲኖራቸው አበረታታ።—አገልግሎታችን ገጽ 91
መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 95 (213)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች እና “የግንባታ ፕሮጀክት ዜና።” የሒሳብ ሪፖርት።
10 ደቂቃ:- “መልካም በማድረግ ምሳሌ ሁኑ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
25 ደቂቃ:- በድፍረት በመመሥከር ረገድ ምሳሌነታቸውን ኮርጁ። የአምልኮ አንድነት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 172-3 ላይ የተመሠረተ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። አድማጮች በአንቀጽ 8 ላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች ሲመልሱ ጥቅሶቹንም አያይዘው እንዲናገሩ ጋብዝ። የተወሰኑ ጥቅሶች መርጠህ እንዲነበቡ አድርግ። ከእነዚህ ዘገባዎች ምን ትምህርት እንደምናገኝ እንዲሁም ከቤት ወደ ቤት የሚደረገውን አገልግሎት ጨምሮ ምሥራቹን እንድንሰብክ ለተሰጠን ሥራ ተገቢ አመለካከት እንዲኖረን የሚረዱን እንዴት እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 89 (201) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 20 (45)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሐምሌ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 6 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የሰኔ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲመሰክር የሚያሳይ ይሆናል።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- “በቡድን ሆኖ ማገልገል ደስታ ያስገኛል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 3ን በምትወያዩበት ጊዜ በመስከረም 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን የጥያቄ ሣጥን ላይ የወጡ ሐሳቦችን ጥቀስ። ለአንድ የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካች አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርግ። ለመጽሐፍ ጥናት ቡድኑ ስላደረገው የመስክ አገልግሎት ዝግጅትና ወንድሞች በቡድን በማገልገላቸው እንዴት እንደተጠቀሙ ጠይቀው።
መዝሙር 29 (62) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 71 (163)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በወሩ ውስጥ የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። በአገልግሎት የሚጠቀሙበት አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
20 ደቂቃ:- “የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ባሉበት ክልል ውስጥ ጽሑፎችን ማበርከት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በቀረቡት ጥያቄዎች ተጠቀም። አዲስ አበባ ውስጥ የውጭ አገር ቋንቋ ተናጋሪዎችን የእንግሊዝኛ ጉባኤ አባላት እንደሚያነጋግሯቸው ግለጽ።
15 ደቂቃ:- ወጣቶች ይሖዋን እያወደሱ ነው! በንግግር፣ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይትና በቃለ ምልልስ የሚቀርብ። ወጣቶች በስብሰባዎች ላይ ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሐሳቦች ሲሰጡ መስማት ያስደስተናል። በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በትጋት መሳተፋቸውና እድገት ማድረጋቸው የሚያስደስት ነው። በአገልግሎት ጥሩ ምስክርነት ሲሰጡ እውነተኛ እምነት እንዳላቸው ያሳያሉ። አምላካዊ ምግባራቸው ይሖዋን ያስከብራል። (yb88 ገጽ 53-4) መንፈሳዊ እድገት ማድረጋቸው ወደፊት ለሚያገኟቸው የአገልግሎት መብቶች መሠረት ይሆናቸዋል። በጉባኤ እንቅስቃሴዎች አዘውትረው ለሚካፈሉ ሁለት ወይም ሦስት ክርስቲያን ወጣቶች ቃለ ምልልስ አድርግ። በጉባኤ ውስጥ ያሉት ወጣቶች ይሖዋን ለማወደስ ለሚያደርጉት ጥረት ከልብ አመስግናቸው።
መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።