ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 25, 2003 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከሐምሌ 7 እስከ ነሐሴ 25, 2003 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርያት
1. በመስክ አገልግሎት ስንካፈል የአድማጫችንን ዓይን መመልከታችን ምን ጥቅሞች አሉት? [be ገጽ 125 አን. 1-2፤ ገጽ 125 ሣጥኑን ተመልከት።]
2. አገልግሎት ልትጀምር ስትል ፍርሃት የሚሰማህ ከሆነ ምን ሊረዳህ ይችላል? [be ገጽ 128 አን. 4-5]
3. መድረክ ላይ ሆነህ ንግግር በምታቀርብበት ጊዜ የራስህን ተፈጥሯዊ አነጋገር በመጠቀም ከአንድ ግለሰብ ጋር እንደምታወራ ሆነህ እንድትናገር ምን ሊረዳህ ይችላል? [be ገጽ 129 አን. 2፤ ገጽ 129 ሣጥኑን ተመልከት።]
4. በዘሌዋውያን 16:4, 24, 26, 28፣ ዮሐንስ 13:10 እና ራእይ 19:8 ላይ የሚገኙት መሠረታዊ ሥርዓቶች አለባበሳችንንና አበጣጠራችንን በሚመለከት ምን መመሪያ ይሰጡናል? [be ገጽ 131 አን. 3፤ ገጽ 131 ሣጥኑን ተመልከት።]
5. አንድን ሰው ጨዋ ነው እንዲሁም ‘ጤናማ አስተሳሰብ’ አለው የሚያስብለው ምንድን ነው? (1 ጢሞ. 2:9, 10) [be ገጽ 132 አን. 1]
ክፍል ቁ. 1
6. ክርስቲያኖች አንዳቸው ሌላውን መታገሥ ቢኖርባቸውም ምንን ግን በዝምታ ማለፍ የለባቸውም? (ቆላ. 3:13) [w 01 7/15 ገጽ 22 አን. 7-8]
7. እውነት ወይስ ሐሰት:- አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ሦስተኛ ወዘተ ወይም ኦርዲናል የሚባሉት ቁጥሮች ሙሉ ቁጥርን ያመለክታሉ። አብራራ። [si ገጽ 282 አን. 24-5]
8. የአምላክን ቃል እንድናነብ የሚገፋፋን ዋነኛው ነገር ምንድን ነው? ይህስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 24 አን. 1]
9. ጠቢብ ሰው ‘እውቀትን የሚሸሽገው’ እንዴት ነው? (ምሳሌ 10:14) [w 01 7/15 ገጽ 27 አን. 4-5]
10. ኢዮብ ጥሩ ልማዶች በማዳበሩ ተጠቅሟል ሊባል የሚቻለው ለምንድን ነው? (ኢዮብ 1:1, 8፤ 2:3) [w 01 8/1 ገጽ 20 አን. 4]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. የአስተዳደር አካል አባላት የአሕዛብ አማኞች ለመዳን መገረዝ እንደማያስፈልጋቸው “በአንድ ልብ” መወሰን የቻሉት እንዴት ነው? (ሥራ 15:25)
12. ይሖዋ የሙሴን ሕግ ሽሮት ሳለ የአስተዳደር አካል አንዳንድ የሕጉን ግዴታዎች እንዲወጣ ጳውሎስን የጠየቀው ለምንድን ነው? (ሥራ 21:20-26) [it-1 ገጽ 481 አን. 3፤ it-2 ገጽ 1163 አን. 6–ገጽ 1164 አን. 1]
13. በቅርቡ በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የተነሱትን ነቀፋዎች የሚያስታውሱን የትኞቹ በጳውሎስ ላይ የተሰነዘሩ የሐሰት ክሶች ናቸው? (ሥራ 24:5, 6) [w 01 12/15 ገጽ 22 አን. 7–ገጽ 23 አን. 2]
14. ጳውሎስ ለሁለት ዓመታት ያህል በእስር ላይ በነበረበት ጊዜም መንግሥቱን በማወጅ ረገድ ምሳሌ የሆነው እንዴት ነው? (ሥራ 28:30, 31 አ.መ.ት )
15. ‘በበላይ ያሉት ባለ ሥልጣናት’ ‘የእግዚአብሔር ሥርዓት’ ክፍል ናቸው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? ይህስ ክርስቲያኖችን የሚነካቸው እንዴት ነው? (ሮሜ 13:1, 2) [w 00 8/1 ገጽ 4 አን. 5]