የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/03 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 8/03 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴና መስከረም:- ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ”፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት . . .፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ ኤ ሳትስፋይንግ ላይፍ​—⁠ሃው ቱ አቴይን ኢት? እና የሙታን መናፍስት —⁠ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? መስከረም:- እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ:- ላይፍ—⁠ሃው ዲድ ኢት ጌት ሂር? ባይ ኢቮሉሽን ኦር ባይ ክሪኤሽን? ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲገኝ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት በማድረግ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ። ኅዳር:- እውቀት መጽሐፍ ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር ይበረከታል። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ወይም ሌላ የቆየ ጽሑፍ ማበርከት ይቻላል።

◼ መስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ከዚያም የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።

◼ በእጅ ያሉት ጽሑፎችና መጽሔቶች ዓመታዊ ቆጠራ በተቻለ መጠን ነሐሴ 31, 2003 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይርቅ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ቆጠራ የጽሑፍ አስተባባሪው በየወሩ ከሚያካሂደው ቆጠራ ጋር ተመሳሳይ ነው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18) ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶችን ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ(ዮቹ) ማግኘት ይቻላል። የአስተባባሪው ጉባኤ ጸሐፊ ቆጠራውን በበላይነት መከታተል ይኖርበታል። እርሱና የአስተባባሪው ጉባኤ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ቅጹ ላይ ይፈርማሉ። እያንዳንዱ አስተባባሪ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18) ይደርሱታል። በአዳራሹ ለብቻቸው የሚጠቀሙ ጉባኤዎችም እነዚህ ቅጾች ይደርሷቸዋል። እባካችሁ ዋናውን ቅጂ እስከ መስከረም 6 ድረስ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሙያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።

◼ ጉባኤዎች በመስከረም ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2004 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር​—2004 እና የ2004 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ ይኖርባቸዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ