የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/03 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 9/03 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መስከረም:- ብሮሹሮች። ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲገኝ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት በማድረግ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ። ኅዳር:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ወይም ሌላ የቆየ ጽሑፍ ማበርከት ይቻላል። ታኅሣሥ:- እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው። በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፣ መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባሉትን መጽሐፎች በአማራጭነት ማበርከት ይቻላል።

◼ ቅርንጫፍ ቢሮው አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ጽሑፎችን ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማስታወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙት ጽሑፎች የትኞቹ እንደሆኑ እባካችሁ አትርሱ።

◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-3 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን።

◼ በ2004 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር እሁድ ሚያዝያ 18 ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ ወደፊት ይገለጻል። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት የሚኖራቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። ማንኛውም ጉባኤ ከሚያዝያ 18, 2004 በፊት ልዩ የሕዝብ ንግግሩን ማቅረብ አይኖርበትም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ