የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
መስከረም 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 (10)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሁሉም በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ባለፈው የአገልግሎት ዓመት በተካሄደው የወረዳ ስብሰባ ላይ የወሰዱትን ማስታወሻ ከልሰው እንዲመጡ አበረታታ። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የነሐሴ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የነሐሴ 2003 ንቁ! መጽሔቶችን በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሕያው ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አንድ ተማሪ ወይም ወላጅ ለመምህር ሲመሠክር የሚያሳይ ይሁን።
10 ደቂቃ:- “‘ለአምላክ ክብር ስጡት’ የ2003 የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ።” በአውራጃ ስብሰባው ላይ ሦስቱንም ቀናት ለመገኘት ቀደም ብለው ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁትን ሁሉ ከልብ አመስግናቸው። እንዲሁም እስካሁን እንደዚያ ያላደረጉትን በተቻለ መጠን ቶሎ እንዲያጠናቅቁ አበረታታ።
25 ደቂቃ:- “እናንተ ወጣቶች—ለሚመጣው ዘመን መልካም መሠረት ጣሉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንድ ሽማግሌ ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም ያቀርበዋል። በአንቀጽ 5 ላይ ስትወያዩ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት መካፈል የሚያስገኘውን ደስታና በረከት ጎላ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 21 (46) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 54 (132)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
25 ደቂቃ:- “በይሖዋ ታመን፣ መልካሙንም አድርግ።” (መዝ. 37:3) ባለፈው የአገልግሎት ዓመት በተደረገው የወረዳ ስብሰባ ላይ የቀረቡትን ዋና ዋና ነጥቦች በሚያጎሉት በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች በስብሰባው ላይ የተማሯቸውን ጠቃሚ ሐሳቦች በግልም ሆነ በቤተሰብ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደቻሉ እንዲናገሩ ጋብዝ። በሚከተሉት የስብሰባው ክፍሎች ላይ ተወያዩ:- (1) “በይሖዋ የምትታመኑ መሆናችሁን አሳዩ።” በሁሉም የሕይወት ዘርፎች በይሖዋ መታመናችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ጥራዝ 2 ገጽ 521) በዚህ ረገድ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው? (2) “ከንቱ የሕይወት ግቦችን ከማሳደድ ተጠበቁ።” (መክ. 2:4-8, 11) የትኞቹን ከንቱ የሆኑ ግቦች ከማሳደድ መጠበቅ ይኖርብናል? እንዲህ ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው? (3) “ክፉውን ተጸየፉ፣ መልካሙን የምታደርጉ ሁኑ።” የይሖዋን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች በጥብቅ መከተል አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ኢሳ. 5:20) በየትኞቹ መልካም ሥራዎች መጠመድ ይኖርብናል? (4) “በይሖዋ ላይ ያለንን ትምክህት ጠብቀን መኖር።” መከራዎችና ፈተናዎች ሲያጋጥሙን አቋማችንን ጠብቀን ለመኖር የሚረዳን ምንድን ነው? አንዳንድ ነገሮችን ለይሖዋ መተው የሚኖርብን ለምንድን ነው? (5) “ለአምላክ መንግሥት የምትገቡ ሆናችሁ ትቆጠሩ ይሆን?” (ቆላ. 1:10) ለይሖዋ እንደምንገባ ሆነን መመላለሳችንን እንድንቀጥል የሚያነሳሱን የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች የትኞቹ ናቸው? (6) “ይሖዋ በሰጣቸው ተስፋዎች ታመኑ።” ይሖዋ በሰጣቸው ተስፋዎች መታመናችን ሕይወታችንን የሚነካው እንዴት ነው?
መዝሙር 28 (58) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 83 (187)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎችና የአውራጃ ስብሰባን የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የነሐሴ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የነሐሴ 8, 2003 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አንድ የጉባኤ ሽማግሌና በአካላዊ ህመም ወይም በዕድሜ መግፋት የተነሳ ከቤት መውጣት የማይችል አንድ አስፋፊ በስልክ ምሥክርነት ሲሰጡ የሚያሳይ ይሁን።
15 ደቂቃ:- ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ጉባኤው በ2003 የአገልግሎት ዓመት ካደረገው እንቅስቃሴ ጎላ ያሉ ክንውኖችን ይከልሳል። ስላከናወኑት መልካም እንቅስቃሴ ሁሉንም አመስግን። የወረዳው የበላይ ተመልካች ባለፈው ጉብኝቱ ጉባኤውን አስመልክቶ ከሰጠው ሪፖርት አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን ጥቀስ። በያዝነው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ሊያተኩርባቸው የሚገቡ ሁለት ግቦችን ተናገር።
20 ደቂቃ:- ሁሉም ሃይማኖቶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አላቸው? በማመራመር መጽሐፍ ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። አንድን ሰው በዚህ ርዕስ እንዴት ማወያየት እንደሚቻል ተወያዩ። (ማመራመር ገጽ 321-2) ትክክለኛው ሃይማኖት ተለይቶ ከሚታወቅባቸው መንገዶች ውስጥ ጥቂቶቹን ተናገር። (ማመራመር ገጽ 327-29) የስብከት ሥራችን አምላክ የሚቀበለው አምልኮ የትኛው እንደሆነ ሌሎች እንዲያውቁ ይረዳቸዋል።—ቆላ. 1:9, 10
መዝሙር 11 (29) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 57 (136)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስከረም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በጥቅምት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
15 ደቂቃ:- በግንቦት 2003 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣውን “በዘመናችን መቶ ዓመት ባስቆጠረው ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት እየተካፈላችሁ ነውን?” የሚል ርዕስ ከልስ። ከጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ ምን ያህሉ እንደተሸፈነ ተናገር።
20 ደቂቃ:- “ትሕትናን ልበሱ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች በጥቅሶቹ ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።
መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 78 (175)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በዚህ ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ልዩ ጥረት እናደርጋለን። በግንቦት 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 አንቀጽ 1 ላይ የቀረበውን ሐሳብ በአጭሩ ከልስ።
15 ደቂቃ:- “ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ነገሮች ቅድሚያ ስጡ!” በመስከረም 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19 -21 ላይ ባለው ርዕስ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በቀጣዮቹ ወራት ጎላ ያሉ ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች የምናደርግባቸውን ቀናት ጥቀስ፤ ሁሉም እነዚህን ቀናት በቀን መቁጠሪያቸው ላይ ምልክት እንዲያደርጉባቸው አበረታታ። አድማጮች መንፈሳዊ ዝግጅቶች እንዳያመልጧቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
20 ደቂቃ:- የእኩዮችን ተጽዕኖ መቋቋም። በእውነት ቤት ላደገ አንድ ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ቃለ መጠይቅ አድርግለት። ከየካቲት 15, 2003 መጠበቂያ ግንብ ላይ አንዳንድ ነጥቦችን ጥቀስ። ወንድም በትምህርት ቤት ምን ተጽዕኖዎች አጋጥመውት ነበር? (ገጽ 24 አን. 3፤ ገጽ 25 አን. 4-5) ሌሎች አፍራሽ የሆነ አስተሳሰብ ሊያሳድሩበት ሞክረው ነበር? (ገጽ 26 አን. 4-6) አሁንስ የእኩዮች ተጽዕኖ ያጋጥመዋል? እኩዮቹ የእነርሱን አቋም እንዲከተል የሚያደርጉበትን ተጽዕኖ ለመቋቋም የረዳው ምንድን ነው? ከዚያም በነሐሴ 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 24-5 ላይ የተመሠረተ አጭር ንግግር አቅርብ። ጥሩ ወዳጅነት መመሥረት የሚያስገኘውን ጥቅም ጎላ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 9 (26) እና የመደምደሚያ ጸሎት።