ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 27, 2003 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመስከረም 1 እስከ ጥቅምት 27, 2003 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርያት
1. በ1 ጢሞቴዎስ 2:9 [NW ] ላይ በተሰጠው ምክር መሠረት ‘ሥርዓታማ አለባበስ’ ሲባል ምን ማለት ነው? ይህስ ከመድረክ ንግግር ስናቀርብም ሆነ ስናገለግል መልእክታችንን የሚነካው እንዴት ነው? [be ገጽ 132 አን. 4-5]
2. አለባበሳችንንና አበጣጠራችንን በተመለከተ 1 ዮሐንስ 2:15-17፣ ኤፌሶን 2:1, 2 እና ሮሜ 15:3 ላይ የሠፈሩት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ምን መመሪያ ይዘዋል? [be ገጽ 133 አን. 2-4]
3. መረጋጋት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በመድረክም ሆነ በአገልግሎት ላይ ተረጋግቶ መናገር የሚቻለው እንዴት ነው? [be ገጽ 135 ሣጥን፤ ገጽ 136 አን. 5, ሣጥን]
4. ኢየሱስ “የታመነውና እውነተኛው ምስክር” እንደመሆኑ መጠን በአገልግሎት ላይ መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ረገድ ምን ምሳሌ ትቶልናል? (ራእይ 3:14) [be ገጽ 143 አን. 2-3]
5. በመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃቀማችን የተዋጣልን መሆን የምንችለው እንዴት ነው? (ቲቶ 1:9) [be ገጽ 144 አን. 1, ሣጥን]
ክፍል ቁ. 1
6. ጥናት ምን ነገሮችን ያካትታል? የአምላክን ቃል አዘውትሮ ማጥናት ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? [be ገጽ 27 አን. 3፤ ገጽ 32 አን. 4]
7. ውሳኔ የሚጠይቅ ከባድ ጉዳይ ሲያጋጥመን በያዕቆብ 1:5, 6 ላይ በተሰጠው ምክር መሠረት ምን ብናደርግ እንጠቀማለን? [w 01 9/1 ገጽ 28 አን. 4]
8. ጠቋሚ ዓመታት ምንድን ናቸው? በጣም አስፈላጊ የሆኑትስ ለምንድን ነው? [si ገጽ 282 አን. 27]
9. ‘ሐሜትን የሚገልጥ ሰው’ ሰነፍ ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? (ምሳሌ 10:18) [w 01 9/15 ገጽ 25 አን. 3]
10. በአዲሱ ዓለም የሰው ልጆች ይሖዋ ስለ ጊዜ ያለውን አመለካከት በይበልጥ ወደ መገንዘብ ሊደርሱ የሚችሉት እንዴት ነው? [si ገጽ 283 አን. 32]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. እውነት ወይም ሐሰት:- ሐዋርያው ጳውሎስ በ1 ቆሮንቶስ 2:9 ላይ የተናገረው ይሖዋ ለሕዝቦቹ ውርሻ አድርጎ ስላዘጋጀላቸው ነገሮች ነው። አብራራ። [ip-2 ገጽ 366 ሣጥን]
12. አንደኛ ቆሮንቶስ 10:13 የሚናገረው ስለ ምን ዓይነት ፈተናዎች ነው? ይሖዋስ ‘መውጫውን የሚያደርገው’ እንዴት ነው? [w 91 10/1 ገጽ 10-11 አን. 11-14]
13. ኢየሱስ በልግስና ረገድ የተወው ምሳሌ ለክርስቲያኖች ምን ትምህርት ይዟል? (2 ቆሮ. 8:9) [w 92 1/15 ገጽ 16 አን. 10]
14. ሕጉ ‘ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚት’ የነበረው እንዴት ነው? (ገላ. 3:24) [w 02 6/1 ገጽ 15 አን. 11]
15. ከመታለል ለመጠበቅ ልናስወግዳቸው የሚገቡ “እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት” የሚቆጠሩ ነገሮች የትኞቹ ናቸው? (ቆላ. 2:8)