ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 29, 2003 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከኅዳር 3 እስከ ታኅሣሥ 29, 2003 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርያት
1. በመስክ አገልግሎት ላይ በመጽሐፍ ቅዱስ መጠቀም በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 145 አን. 2, ሣጥን]
2. በአንድ ጥቅስ ዙሪያ ያለው ሐሳብ ጥቅሱን የምታስተዋውቅበትን መንገድ የሚወስነው እንዴት ነው? [be ገጽ 149]
3. አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በምታነብበት ጊዜ ትክክለኛዎቹን ቃላት ማጉላት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንን ችሎታ ማዳበር የሚቻለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 151 አን. 2, ሣጥን]
4. ሌሎችን በምናስተምርበት ጊዜ ‘የእውነትን ቃል በቅንነት እንድንናገር’ ጳውሎስ የሰጠንን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? እንደዚህ ማድረግ አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው? (2 ጢሞ. 2:15) [be ገጽ 153 አን. 2, ሣጥን]
5. ጳውሎስ ‘ከመጻሕፍት እየጠቀሰ ያስረዳ’ የነበረው እንዴት ነው? (ሥራ 17:2, 3) [be ገጽ 155 አን. 5, 6]
ክፍል ቁጥር 1
6. ዋነኛ የምርምር መጽሐፋችን በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመን ንግግር በምንዘጋጅበት ጊዜ (1) በጥቅሱ ዙሪያ ያለውን ሐሳብ መመልከት፣ (2) ማጣቀሻዎቹን ማየትና (3) የመጽሐፍ ቅዱስ ኮንኮርዳንስ መጠቀም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 34 አን. 3–ገጽ 35 አን. 2]
7. እውነተኛ ታማኝነት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ማሳየት ያለብንስ ለእነማን ነው? [w01 10/1 ገጽ 22-3]
8. ይሖዋ ነገሮችን የሚያከናውነው በትክክል ጊዜውን ጠብቆ እንደሆነ የሚያሳየው ምንድን ነው? (ዳን. 11:35-40፤ ሉቃስ 21:24) [si ገጽ 284 አን. 1]
9. አንድ ንግግር ለማቅረብ ምርምር ካደረግን በኋላ የምንጠቅሳቸውን ነጥቦች በምንመርጥበት ጊዜ ምን ነገሮች በአእምሯችን ልንይዝ ይገባል? [be ገጽ 38]
10. ኢየሱስ ስለ ‘ኖኅ ዘመን’ የሰጠው ሐሳብ በዛሬው ጊዜ ለእኛም ጠቃሚ ነው የምንለው ለምንድን ነው? (ማቴ. 24:37) [w01 11/15 ገጽ 31 አን. 3-4]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ጳውሎስ ለፊልሞና የጻፈው ደብዳቤ የክርስቲያኖች ተልእኮ ሰዎች ክርስትናን እንዲቀበሉ መርዳት እንጂ ማኅበራዊ ለውጥ ማራመድ እንዳልሆነ የሚያሳየው እንዴት ነው? (ፊል. 12)
12. ‘መወሰድ፣’ ‘መካድ’ እና ‘ከመንገድ መውጣት’ ልዩነታቸው ምንድን ነው? (ዕብ. 2:1፤ 3:12፤ 6:6 የ1980 ትርጉም) [w99 7/15 ገጽ 19 አን. 12፤ w86 6/1 ገጽ 14 አን. 16-17፤ w80 12/1 ገጽ 23 አን. 8]
13. በረባ ባልረባው ‘ይሖዋ ቢፈቅድ’ የሚለውን አባባል የመጠቀምን ልማድ ማስወገድ የምንችለው እንዴት ነው? (ያዕ. 4:15) [cj p. 171 አን. 1-2]
14. ‘የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት መጠበቅና ማስቸኰል’ ምን ማለት ነው? እንደዚህ ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው? (2 ጴጥ. 3:11, 12) [w97 9/1 ገጽ 19-20]
15. በራእይ ምዕራፍ 2 እና 3 ላይ ለተጠቀሱት ሰባት ጉባኤዎች ከተላከው መልእክት ዛሬ ላሉ ክርስቲያኖች የሚሆን ምን ጠቃሚ ምክር ይገኛል? (ራእይ 2:4, 5, 10, 14, 20፤ 3:3, 10, 11, 17, 19)