የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ታኅሣሥ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 99 (221)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥቅምት 2003 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል።
20 ደቂቃ:- “እውነተኛ ክርስቲያናዊ አንድነት—እንዴት?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 5ን ስትወያዩ አድማጮች በብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ሲካፈሉ፣ በቲኦክራሲያዊ የግንባታ ፕሮጄክቶች ሲሠሩ ወይም በተፈጥሮ አደጋዎች ለተጠቁ አካባቢዎች እርዳታ በማድረስ ሲሳተፉ ያገኟቸውን ክርስቲያናዊ አንድነታችንን የሚያጠነክሩ የግል ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።
15 ደቂቃ:- “የ2004 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት።” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ከጥቅምት 2003 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 21 (46) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 61 (144)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “እባካችሁ ወዲያውኑ ሄዳችሁ አነጋግሯቸው” የሚለውን ሣጥን ተወያዩበት። “እባክህ ይህንን ሰው ብቁ የሆነ አስፋፊ እንዲያነጋግረው አድርግ” (S-70) የተባለውን ቅጽ ማግኘት የምትችል ከሆነ ለአድማጮች አሳያቸው።
15 ደቂቃ:- የግል ጥናት የአምልኮታችን ክፍል ነው። በጥቅምት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14-15 አንቀጽ 6-10 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ:- “ትክክለኛ ዝንባሌ ያላቸውን እርዱ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ስትጀምር መስከረም 1, 2003 በሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የቀረበውን “ተመልሳችሁ እንደምትጠይቋቸው የገባችሁትን ቃል ትጠብቃላችሁ?” የሚለውን ርዕስ ጥቀስና በዚህ ረገድ ይበልጥ ጠንቃቃ መሆን እንደሚያስፈልገን የሚያሳዩ በርካታ ተሞክሮዎችን ተናገር። ከዚያም “ይህ ክፍል ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ በዚህ ረገድ መሻሻል አድርገናል?” በማለት ጠይቅ። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም ርዕሱን ተወያዩበት። በመጋቢት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግን በሚመለከት የቀረቡትን ዝርዝር ሐሳቦች ከልስ።
መዝሙር 18 (42) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 (10)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በገጽ 6 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የጥቅምት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የጥቅምት 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በሚቀጥለው ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሕክምና አሰጣጥን የሚመለከት ማሳሰቢያ/ባለሙያዎችን ከተጠያቂነት ነፃ የሚያደርግ ሰነድ እና ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም በተባሉት ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጎ ቅጾቹ ለአስፋፊዎች እንደሚከፋፈሉ አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
18 ደቂቃ:- “የሚገባቸውን ሰዎች መፈለግ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለጉባኤው እንደሚስማማ አድርገህ አቅርበው። ሰዎች በአብዛኛው በቤታቸው ሊገኙ የሚችሉት መቼ ነው? ከሰዓት በኋላ ወይም አመሻሹ ላይ በማገልገል ምን ውጤቶች ተገኝተዋል? እምብዛም በቤታቸው የማይገኙ ሰዎችን ለማግኘት የትኞቹን ዘዴዎች መጠቀም እንችላለን?
መዝሙር 92 (209) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 88 (200)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የታኅሣሥ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በጥር ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። በዓላት ለሚውሉባቸው ቀናት የተደረጉትን የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶች ተናገር።
17 ደቂቃ:- ድካማችሁ በከንቱ አይቀርም። (1 ቆሮ. 15:58) ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በቀድሞ ዓመታት ይካሄድ ስለነበረው የስብከት ሥራ የሚናገሩ ለብዙ ዓመታት በታማኝነት ያገለገሉ አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ። ጉባኤው ምን ያህል አባላት ነበሩት? የጉባኤው ክልል ምን ያህል ሰፊ ነበር? ሰዎች ለመንግሥቱ መልእክት ምን ምላሽ ይሰጡ ነበር? ምን ዓይነት ተቃውሞ ያጋጥማችሁ ነበር? ባለፉት ዓመታት በዚያ አካባቢ የመንግሥቱ ስብከት ሥራ ምን ያህል እድገት አሳይቷል?
23 ደቂቃ:- ከሕክምና ጋር በተያያዘ ለሚያጋጥሙን ችግሮች ዝግጁ መሆን። ከቅርንጫፍ ቢሮው የተላከውን አስተዋጽኦ በመጠቀም ጥሩ ችሎታ ያለው አንድ ሽማግሌ በንግግር ያቀርበዋል። “ከደም እንድንርቅ ለመርዳት የተደረገ ዝግጅት” ከሚለው ሣጥን ዋና ዋና ሐሳቦችን ከልስ።
መዝሙር 55 (133) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 20 (45)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የግንባታ ፕሮጄክት ዜና” የሚለውን ጨምረህ አቅርብ።
15 ደቂቃ:- በየካቲት 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 3, 4 ላይ በሚገኘው አመስጋኞች መሆን ያለብን ለምንድን ነው? በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ለጉባኤው እንደሚስማማ አድርገህ አቅርበው።
20 ደቂቃ:- ሌሎችን የማስተማር ችሎታችንን ማዳበር። በሰኔ 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16-17 አንቀጽ 9-13 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ውጤታማ አስተማሪዎች መሆን በአገልግሎታችን ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ግብ ነው። በግ መሰል ሰዎችን በመርዳት የምናገኘው ስኬት የመንግሥቱን መልእክት ግንዛቤን በሚያሰፋና ለተግባር በሚያነሳሳ መልኩ ማቅረብ በመቻላችን ላይ የተመካ ነው። በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ተወያዩባቸው:- (1) በመስበክና በማስተማር መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? (ጠለቅ ብሎ ማስተዋል-2 ገጽ 672 አን. 2) (2) አንዳንዶች የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጠናት የሚፈሩት ለምንድን ነው? (3) የማስተማር ችሎታችንን እንዴት ማሻሻል እንችላለን? (4) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስናስጠና ብዙ መናገር የሌለብን ለምንድን ነው? (5) ጥቅሶችን ተግባራዊ ከሆኑ ሁኔታዎች ጋር ማዛመዳችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (6) ተማሪያችን የተማረውን ነገር በሚገባ መረዳቱን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? (7) በጥናቱ መጀመሪያና መደምደሚያ ላይ ትምህርቱን መከለሱ ምን ጥቅም አለው? (8) ተማሪያችን የትኛው ግብ ላይ እንዲደርስ መርዳት ይኖርብናል? (9) አንዳንድ ጊዜ ተሞክሮ ያላቸውን ሽማግሌዎች በጥናቱ ላይ እንዲገኙ መጋበዙ ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው? (10) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስናስጠና ተራ በተራ መምራቱ አስፈላጊ ባይሆንም በአንዳንድ ሁኔታዎች በጥናቱ ላይ እንዲገኝ የተጋበዘው ሽማግሌ የምዕራፉን የተወሰነ ክፍል እንዲመራ ማድረጉ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።